fredag 24. mai 2013

ከባሕር ዳሩ ግድያ ጋር በተያያዘ 22 የፖሊስ አባላት ተይዘዋል (audio)

ከአንድ ሣምንት በፊት በባህር ዳር ከተማ የተፈፀመው ግድያ የብሔር ልዩነት ጋር ግንኙነት እንደሌለው የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት መሪ ምክትል ኮማንደር ዋለልኝ ዳኘው አስታውቀዋል።ፈቃዱ ናሻ የተባለ የፌዴራል ፖሊስ አባል ባለፈው ግንቦት አራት “ፍቅረኛው” የተባለች ሴት ቤትና ፖሊስ እንደገለፀው ”ከፊቱ ያገኘው ሁሉ” ላይ በከፈተው ተኩስ ከራሱ ጭምር አሥራ ሦስት ሰዎችን መግደሉና ሌሎች ሁለት ማቁሰሉ መገለፁ ይታወሳል።አንዳንድ የከተማው ነዋሪዎች የግድያው መንስዔ የብሔር ልዩነት ነው ቢሉም ፖሊስ ምክንያቱ ”በግል ያለመግባባት እንጂ ከዘር ጋር ግንኙነት የለውም” ብሏል። ፖሊሱን  ምን እንዳነሣሣውና በግድያው የየቤተሰባቸውን አባላት ላጡ ቤተሰቦች ስለሚደረግ ካሣ መንግሥት ጥናት እያካሄደ መሆኑን ምክትል ኮማንደር ዋለልኝ ገልፀዋል።“የፌደራል ፖሊስ አባል ፈቃደ ናሻ ከነትጥቁ ከምድቡ ሲወጣና ግድያውን ሲፈፅምም አላስቆሙትም የተባሉ 22 የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን” ምክትል ኮማንደሩ አረጋግጠዋል።ለዝርዝርና ለተጨማሪ ጉዳዮን ለመከታተል ባህር ዳር የሚገኘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፤ ፋይሉ ተያይዟል፡፡  click the link

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar