አዲስ አበባ ፣ግንቦት 5 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በባህር ዳር ከተማ ልዩ ስሙ አባይ ማዶ በተባለ አከባቢ ፥ አንድ ግለሰብ 12 ሰዎችን ገደለ ፡፡
ከስፍራው የደረሰን መረጃ ግለሰቡ ሰክሮ እንደነበር ነው የሚያመለክተው ።
የባህር ዳር ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን መምሪያ ሀላፊ ኮማንደር ደረጀ አቻምየለህ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት ፥ ግለሰቡ በውል ባልታወቀ ምክንያት በመንገድ ላይ በከፈተው ተኩስ ከሞቱት 12 ሰዎች በተጨማሪ ሌሎች ሁለት ሰዎች ክፉኛ ቆስለዋል ።
በሰዓቱም ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ ክትትል ሲያደርግ እንደነበርና በመጨረሻም ራሱን በወንዝ ውስጥ በመወርወር ህይወቱን እንዳጠፋ ነው ያመለከቱት ።
ድርጊቱን የፈፀመው ግለሰብ የፌደራል ፖሊስ አባል መሆኑን የገለፁት ኮማንደሩ ፥ ድርጊቱን የፈፀመበት ምክንያት ግለሰባዊ እንደሆነ አመልክተዋል ።
Source: FBC
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar