SUNDAY, 31 MARCH 2013
ውጡ መባላቸው አሳፋሪ ነው!
(የ“አንድነት” ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ)
ነዋሪዎች ሲፈናቀሉ በህይወት የመኖር
ህልውናቸውም አደጋ ላይ ይወድቃል
( ኢትዮጵያዊ ምሁር)
የኢትዮጵያ ህገ መንግሥት ካስቀመጣቸው የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች መካከል፤የዜጐች ከቦታ ቦታ የመዘዋወር ነፃነት አንዱ ሲሆን በህገ መንግሥቱ አንቀፅ 32 ንዑስ አንቀፅ 1 ላይ “ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወይም በህጋዊ መንገድ ሀገሪቱ ውስጥ የሚገኝ የውጭ ዜጋ በመረጠው የሀገሪቱ አካባቢ የመዘዋወርና የመኖሪያ ቦታ የመመስረት እንዲሁም በፈለገው ጊዜ ከሀገር የመውጣት ነፃነት”እንዳለው ተደንግጓል፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሰረት ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው ብቻ ሳይሆን የሌላም ሀገር ዜጋ በሀገሪቱ ሉአላዊ ግዛት ውስጥ በማንኛውም አካባቢ መኖር ይችላል - ሃብትና ንብረት አፍርቶና ቤተሰብ መሥርቶ፡፡ በህገ-መንግስቱ ላይ በግልፅ የሰፈረው ሀቅ ይሄ ቢሆንም በየጊዜው ግን ድንጋጌውን የሚጥሱ ተግባራት እየተፈፀሙ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
በተለይ ከሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ከአማራ አካባቢ ወደተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች በመሄድ ለአመታት ሀብትና ንብረት አፍርተው የኖሩ ዜጎች፣በየጊዜው የመፈናቀል አደጋ እየገጠማቸው ነው - መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፡፡ ከአመት በፊት በደቡብ ክልል ጉራፈርዳ የተባለ ቦታ ላይ ለረጅም አመታት ኑሮ መስርተው ሲኖሩ የቆዩ የአማራ ተወላጆች “ቦታው የእናንተ አይደለም” በሚል በሃይል መባረራቸው የሚታወስ ነው፡፡ ይህን ዜጐችን የማፈናቀል ድርጊት በወቅቱ በርካታ ወገኖች ቢያወግዙትም ሰሚ ባለማግኘቱ፤ገበሬዎቹ ያፈሩትን ሃብትና ንብረት ትተው ወደየትውልድ ቀዬአቸው እንዲመለሱ ተገደዋል፡፡
በዚያው በደቡብ አካባቢ በቤንች ማጂ ዞን ሸካ ወረዳ በርካታ የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች በተመሳሳይ ሁኔታ መሬታቸውን ተነጥቀው መባረራቸው ይታወቃል፡፡ በጋምቤላ፣ በአፋር እና በሌሎች አካባቢዎችም ከህገመንግስቱ ጋር በማይጣጣም መልኩ ዜጎች ከመኖርያ አካባቢያቸው መፈናቀላቸውን የተለያዩ ሚዲያዎች መዘገባቸው ይታወሳል፡፡ ከሰሞኑ ደግሞ በተፈጥሮ ሀብቱ በሚታወቀው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኑሮአቸውን ያደረጉ የሰሜን ኢትዮጵያ ተወላጆች ለአመታት ያፈሩትን ሀብትና ንብረት ትተው በግፍ ከአካባቢው እንዲሰናበቱ መደረጉ በዚሁ ጋዜጣ ላይ ዜጎች አገራችሁ አይደለም፣ ልቀቁና ውጡ መባላቸው አሳፋሪ ነው! (የ“አንድነት” ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ)ነዋሪዎች ሲፈናቀሉ በህይወት የመኖር ህልውናቸውም አደጋ ላይ ይወድቃል( ኢትዮጵያዊ ምሁር)ተዘግቧል፡፡ እነዚህ ገበሬዎች በትውልድ ቀዬአቸው የእርሻ መሬት ባለማግኘታቸው፤ ወደክልሉ በመሄድ የሰፈሩ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ የያሶ ወረዳ አስተዳደር “በህገወጥ መንገድ ስለገቡ ወደመጡበት መመለስ አለባቸው” በማለት ባለፈው ሳምንት ከአካባቢው እንዳፈናቀላቸው ይታወቃል፡፡ ከስድስት ሺህ እንደሚልቁ የተገመቱት እነዚህ ተፈናቃይ ዜጐች፤ በገዛ ሀገራቸው ለዳግም ስደት መዳረጋቸውን ምንጮች ይናገራሉ፡፡
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar