mandag 25. mars 2013
ዝክረ ድክተር ተስፋዬ ዯበሳይ
በሀገራችን ኢትዮጵያ ሰሜን ምሥራቅ ትግራይ ክፍሇ ሀገር፤ በአጋሜ አውራጃ፤
በኢሮብ ወረዲ እምትገኝ፤ ዓሉተና እምትባሌ መንዯር በጣም ዯሀ ከሚባለ ቤተሰብ
ክፍሌ ከአባቱ ከአቶ ዯበሳይ ካሕሳይና ከእናቱ ከወ/ሮ ምህረታ ዓድዐማር በ1933
ዓ.ም. ሕፃን ተስፋዬ ተወሇዯ።
ሇአባትና ሇእናቱ ብቸኛ የበኩር ወንዴ ሌጃቸው ሲሆን ከሱ በኋሊ የተውሇደት
ስዴስቱም ሴቶች ሲሆኑ አባትና አምስቱ እህቶቹ በሕይወት አለ።
ተስፋዬ ዯበሳይ ዕዴሜው ሇትምህርት በዯረሰ ጊዜ በተወሇዯባት መንዯር ዓሉተና ትምህርት ቤት
ባሇመኖሩ ሇመማር የነበረው ዕዴሌ እጅጉን የጨሇመ ነበር። ቀረብ ያሇ ትምህርት ቤት በጊዜው
የነበረው ከዓሉተና 35 ኪል ሜትር ገዯማ እርቀት ሊይ አዱግራት ከተማ ውስጥ ነበር። በዚህ
ምክንያት ሕፃኑ ተሰፋዬ ዕዴሜው ሇትምህርት እንዯዯረሰ ትምህርት ሉያገኝ ባሇመቻለ ወሊጆቹን
ትምህርት ወዯሚገኝበት ቦታ ወስዯው ወዯ ት/ቤት እንዱያሰገቡት ላት ተቀን ይጨቀጭቃቸው
እንዯነበር ወሊጆቹና ጎሮቤቶቻቸው ይመሰክራለ። ወዯ ላሊ ቦታ ወስዯው ት/ቤት እንዲያስገቡት ግና
በጣም ዴሆች ነበሩ። ስሇዚህ ተሰፋዬ ሇመማር የነበረው ዕዴሌ በጣም የተወሰነ፤ የመነመነ ነበር።
ተስፋዬ ገና በሌጅነቱ ሇመማር ከነበረው ጉጉት የተነሳ ውትወታውን ሳያቋርጥ ሉገኝ የሚችሇውን
አማራጭ ሁሊ ያሰሊስሌ ነበር። ተስፋዬ ዕዴሜው አሥር ዓመት ገዯማ ሲሆነው በላሊ አከባቢ ይኖሩ
የነበሩ፤ ከወሊጆቹ ሻሌ ያሇ ኑሮ የነበራቸውና የራሳቸው ሌጆች ወዲሌነበራቸው አክስቱ ሄድ
ሇትምህርት ያሇውን ፍሊጎት ገሌጾ፤ ወሊጆቹ ግና ከዴህነታቸው የተነሳ ሇት/ቤት ሉከፍለሇት
እንዯማይችለ በማስረዲት ያስተምሩት ዘንዴ ተማጸናቸው። የተስፋዬን የትምህርት ፍሊጎትና ጉጉት
የተገነዘቡት አክስቱ ያሇምንም ማመናታት የሚከፈሇውን ከፍሇው በዓዱግራት ከተማ በሚገኝ የካቶሉክ
ት/ቤት አስገቡት።
በተፈጥሮው ሇየት ያሇ ባህርይ እንዯነበረው የሚነገርሇት ተስፋዬ በአገኘው ዕዴሌ ሇመጠቀም እርሳስና
ዯብተሩን ታጥቆ ተነሳ። ጊዜም ሳይወስዴ በገባበት የካቶሉክ ት/ቤት የሚመሰገን ጎበዝና ምርጥ ተማሪ
ሆነ። በዓመት አንዴ ሳይሆን ሁሇት ክፍልችን መዝሇሌ ሇተስፋዬ የተሇመዯ ነበር። ተስፋዬና
ትምህርት፣ ትምህርትና ተስፋዬ ገና በሇጋ ዕዴሜው የተዋሃደ መሆናቸውን በችልታውና በጉብዝናው
አስመሰከረ። ተስፋዬ የመጀመርያና የሁሇተኛ ዯረጃ ትምህርቱን እዛው በካቶሉክ ት/ቤት እጅግ በጣም
ጥሩ ውጤት በማምጣት ጨረሰ።
በዓዱግራት የምትገኘው የካቶሉክ ት/ቤት የተመሠረተችበት ዋና ዓሊማ ተማሪዎቹዋን ሇመንፈሳዊ
ትምህርት ማዘጋጀት ስሇነበረ የትምህርት ሥርዓትዋ ረዘም ሊሇ ጊዜ ከመንግሥት ትምህርት ቤቶች
ሥርዓት ጋር ሳይስተካከሌ ቆይቶ ነበር። ስሇዚህ ሇመጀመርያ ጊዜ ተማሪዎቿ በመንግሥት በሚሰጡ
ብሔራዊ ፈተናዎች እንዱሳተፉ የፈቀዯችው በአጋጣሚ ተስፋዬ በ8ኛ ክፍሌ በነበረበት ጊዜ ነበር።
ይህም ቀዯም ብል የታሰበበት ጉዲይ ሳይሆን ውሳኔው የተዯረገው እነ ተስፈዬ 8ኛ ሇመጨረስ ጥቂት
ወራት ሲቀራቸው ነበር። ስሇዚህ ያኔ በዛች ት/ቤት በስምንተኛ ክፍሌ የነበሩ ተማሪዎች ሇብሔራዊ
ፈተና በሚገባ ሳይዘጋጁ ነበር በከተማዋ ወዯ ሚገኝ የመንግሥት ትምህርት ቤት (አግአዚ) ተወስዯውዝክረ ዶክተር ተስፋዬ ደበሳይ……………………በ «ያ ትውልድ ተቋም» የተዘጋጀ………………መጋቢት 15 ቀን 2005 ዓ.ም………… 2
በፈተናው የተሳተፉት። ተማሪዎቹ በፈተናው የተሳተፉት በዴንገት በቂ ዝግጅት ሳያዯርጉ በመሆኑ
ላልች በሙለ ሲወዴቁ ወጣቱ ተስፈዬ ግን ብቻውን አመርቂ ውጤት በማምጣት አሇፈ፤ ሇዚህም
አመርቂ ውጤት ያበቃው ከሌጅነት ጊዜ ጀምሮ ጥሩ አንባቢና አጥኚ ስሇነበረ ነው።
ታዲጊ ወጣቱ ተስፋዬ በትምህርት ቤቱ የሚታወቀውና የሚዯነቀው በፈተናዎች በሚያመጣው ነጥብ
ወይም የክፍሌ ውጤት ብቻ አይዯሇም፤ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎችና አስተማሪዎች በተሰፋዬ
የሚዯነቁት ወዯር የላሇው አንባቢ በመሆኑ ነበር። ትምህርት ቤቱ መጻህፍት ቤት (ሊይብረሪ)
አሌነበረውም። በዛን ጊዜ ሊይብረሪ የሚባሌ ነገር በከተማዋ ፈጽሞ አይገኝም። ሆኖም ድር ተስፋዬ
ከአስተማሪዎችና ከላልች ምሁራን እየተዋሰ ሁሌ ጊዜ መጻሕፍትና መጽሔቶችን ሲያነብ ይታያሌ።
ይስተዋሊሌ። አንዲንዴ ሥነ ጽሑፍ ከየት እንዯሚመጣሇት እኛ ተማሪዎች ብቻ ሳንሆን መምህራን
ሁለ ሳይቀሩ ይገርማቸው ነበር። በወቅቱ፤ በ1950ዎች አከባቢ የማይገኙና ያሌተሇመደ ‘ታይም
መጋዚን’ (Times) እና ‘ንዩስ-ዊክ’ (News Week) መጽሄቶችን ይዞ ይታይ ነበር።
‚አንዴ አቶ አሰፋ ሱባ የሚባለ በዛ ትምህርት ቤት የአማርኛ ቋንቋ አስተማሪ የነበሩ በጣም አዋቂ
ሰው ‚ይህ ብርቅ ተማሪ (ተስፋዬ) የት እንዯሚዯርስና ሇወዯፊቱ ምን እንዯሚሆን ሇማየት ያሇኝን
ጉጉት ሌቆጣጠረው አሌችሌም‛ ሲለ አስታውሳሇሁ።‛ አቶ ግርማይ ተስፋ ጊዮርጊስ የድክተር ተስፋዬ
አብሮ አዯግ ጓዯኛ
‚አንዲንዴ በዛን ጊዜ፤ ምንም ዓይነት መገናኘ ብዙሃን የማይዯርሱበት አከባቢ ከመጀመርያ ዯረጃ
ተማሪ የማይጠበቁ ጠባዮች ይታዩበት ነበር። ጊዜው ብዙ የአፍሪካ ሀገሮች ከባዕዴ አገዛዝ ነፃ
የሚወጡበት ጊዜ ስሇነበረ ዜናውን እየተከታተሇ ላልች ተማሪዎች እንዱያውቁት ያዯርግ ነበር።
ከትምህርት ነፃ ስንሆን እሱ ወዲሇበት እየሄዴን ከበብ አዴርገነው ጥያቄዎች ስናቀርብሇት ትዝ
ይሇኛሌ። ስሇ ጋናና ላልች አዱስ ነፃ የወጡ የአፍሪካ አገሮች፣ በተሇይ ስሇ አሌጀርያ ህዘብ የነፃነት
ትግሌ ወዘተ ቆሞ በማራኪ አንዯበቱ ሲገሌፅሌን የነበርንበትን ቦታ ሳይቀር አስካሁን አስታውሳሇሁ።
ስሇ አሌጀርያ ህዝብ ትግሌ ሲገሌጽ በዛ አጋጣሚ የፈረንሳይ አብዮትን በሚመሇከትም መግሇጫ
ሰጠን። እኔ ሇመጀመርያ ጊዜ ስሇ ፈረንሳይ አብዮት የሰማሁት ያኔ ከሱ ነበር። ገና የስምንተኛ ክፍሌ
ተማሪ እያሇ የተስፋዬ ሁኔታ አስተማሪ እንጂ ተማሪም አይመስሌም ነበር።‛ አቶ ግርማይ ተስፋ
ጊዮርጊስ
ተስፋዬ በስምነተኛ ክፍሌ የሚሰጠውን ብሔራዊ ፈተና እንዲሇፈ ሇሁሇተኛ ዯረጃ ትምህርት መቀላ
ውሰጥ ወዯ ሚገኝው ዮሐንስ አራተኛ ሄድ የዘጠነኛ ክፍሌ ያጠናቀቀው እዛ ነበር። ያኔ የሁሇተኛ
ዯረጃ ትምህርት ቤት መቀላ በስተቀር በላልች የትግራይ ከተሞች አሌነበረም። ከዝግ ካቶሉካዊ
ትምህርት ቤት ወጥቶ በመቀላ የተማረበት ጊዜ ታዲጊው ተሰፋዬ ከብዙዎች ሇህዝባቸውና ሇሀገራቸው
ከሚቆረቆሩ መምህራንና ተማሪዎች የመተዋወቅ ዕዴሌ እንዲገኘ ይናገር ነበር። ከተሇያየ ገጠር የመጡ
ዴሃ ተማሪዎች ሇቤት ኪራይና ኑሮ አየከፈለ የሁሇተኛ ዯረጃ ትምህርት ሇመቀጠሌ የነበረባቸው
ችግር ምን ያህሌ አስቸጋሪና አሳዛኝ መሆኑን በዚሁ የመቀላ አንዴ ዓመት ቆይታው ግንዛቤ ሉያገኝ
አስችልታሌ። ተስፋዬ ዯበሳይ በመቀላ ያሇውን የሕይወት ውጣ ውረዴና ችግር ከተገንዘበና
የወዯፊት ዕዴለንም በውጭ አገር ሇመማር ከአሇው ፍሊጎት በመነሳት፤ አማራጩ በፊት ወዯ ነበረበት
የካቶሉክ ትምህርት ቤት መመሇሰ ሇትምህርት ወዯ ውጭ አገር የመሊክ ዕዴለን ከፍ ሉያዯርገው
እንዯሚችሌ በመረዲት ካቶሉካዊቷ ትምህርት ቤት፡ ዓዱግራት ተመሇሰ
Abonner på:
Legg inn kommentarer (Atom)
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar