søndag 17. mars 2013

ስለአንድነት የሚቆሙ በሠላም ይክረሙ "መሪዎቻንን የት አሉ?"

"እኔ ምን አገባኝ የምትለው ሐረግ፣
እሱ ነው ሃገሬን ያረዳት እንደበግ፣
የሚል ግጥም ልጽፍ፣
ስሜት አንዘርዝሮኝ ብድግ አልኩኝና፣
ምን አገባኝ ብዬ ቁጭ አልኩ እንደገና።"  ኑረዲን ዒሣ
ጀርመን ፍራንክፈርት በታማኝ በየነ ስብሰባ ታምሳ ከረመች። ከብዙ ጊዜ በኋላ እንደገና ብዙ የፍራንክፈርት አካባባቢ ነዋሪዎች ተገናኝን። አልፎም ተርፎም ችግራችንን ተወያየን። በዚሁ አጋጣሚ ይህንን ዝግጅት ላዘጋጁት ለወ/ሮ አሳየሽኝና ለአቶ ጥላሁን ምስጋናየን በግሌ አቀርባለሁ።

ብዙ ተናጋሪዎች፣ ብዙ ምርጥ ዝግጅቶች ስለነበሩ በደስታ ስንከታተል ቆየን። በመጨረሻም ታማኝ ንግግሩን ጀመረ። እኔ ማነኝ? በሚል ነበር የጀመረው። ራሱን ዝቅ አድርጎ ሃገራችን የመሪ እጦትን እንደደረሰባት አስረዳን። እሱ ስለመሪ እጦት ሲያስረዳን እኔ በሃሳብ ፍራንክፈረት ያስተናገደቻቸውን "መሪዎቻችን" አስባቸው ነበር። የመጀመሪው ስብሰባ የኢንጅነር ኃይሉ ሻውል ነበር። ከዛ በኋላ ብዙ ስብሰባዎች አድርገናል። ከብዙ አድካሚ ጉዞ በኋላ ነው ዛሬ በታናሽ ወንድም ታማኝ ስብሰባ ላይ የተገኘነው።

ዛሬ እነዛ ፍራንክፈርት ያስተናገደቻቸው "መሪዎቻችን" ሁሉ የት አሉ? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል። ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ልብ ድካም የሌለበት ሰው መሆን ያስፈልጋል። "የፍራንክፈርት የስብሰባ ታሪክ ከኃይሉ ሻውል እስከ ታማኝ ድረስ" ብዙ ነው። ወያኔን ለመዋጋት ሠራዊት አስፈልገናል ብለው የፎቶግራፍ መረጃ ይዘው ከመጡት ጀምሮ፤ እስከ ወያኔን በቅርብ እንጥለዋለን የሚል መፈክር ያነገቡ ብዙ "መሪዎችን" አይተናል። ይመሩናል፣ ለድልም ያበቁናል ብለን አጨብጭበን፣ የቻልነውን አድርገን የሸኘናቸው፣ እንኳን ሁላችንን አንድ አድርገው ሊመሩን የራሳቸውን ድርጅት ሲበትኑና ሲከፋፍሉ ያየናቸው ብዙ ናቸው። ከዚህም አልፈው ወያኔን የተቀላቀሉ ትንሽ አይደሉም። ፍራንክፈርት ብዙ አይታለች። ብዙም ታዝባለች።

ከኤርትራውያን ጋር ጥርስ የተናከስንበት፣ ሁላችንም ዘብ የቆምንበት የጎሹ ወልዴ ስብሰባ ትዝ ይለኛል። ፍራንክፈርት ውስጥ መድህን ጠንካራ ከሚባሉት ድርጅቶች አንዱ ነበር። የፍራንክፈርትን የፀረ ወያኔ ትግል የመድህን መፈረካከስና ብሎም መፍረስ አዳከመው ብል ስህተት ላይ አልወድቅም። በታማኝ ስብሰባ ላይ ላገኘኋቸው የመድህን አባሎች ፊት ለፊት ስለሞገትኳቸውም አሁን ሃሜት አይሆንብኝም። አዎ ዛሬ ያ ድርጅት የለም። ቢኖርም እንዳለ አይቆጠርም። ግን አባሎቹ አሁንም ለኢትዮጵያዊነት እንደቆሙ አሉ።

ሌላው ድርጅት የቀድሞው መላው ዐማራ (መዐአድ) የአሁን መኢአድ ነበር። በአባላትም በጥንካሬም ሰፋ ያለ ነበር። ይህ ድርጅት በፀረ ወያኔ ትግል በጀርመን ውስጥ የማይካድ አስተዋጽኦ አድርጎ አልፏል። ከዚህ ድርጅት ብዙ አመራሮች ተጋብዘው ተጠርተው ነበር። ዛሬ የዚህ ድርጅት መሪዎች ማለት የመኢአድ መሪዎች ከአባላቶቻቸው ጋር እንደማይገናኙ የታወቀ ነው። ፍራንክፈርት የሚገኙ የዚህ ድርጅት አባላት አሁንም ኢትዮጵያዊነትን እንዳነገቡ ነው።

ሌላው ድርጅት ደግሞ ኢሕአፓ ነበር። ፍራንክፈርት የተለያዩ የኢሕአፓ አመራሮችን ጋብዛ አስተናግዳለች። ኢሕአፓ በጀርመን በዛ ያሉ አባሎች የነበሩት ድርጅት ነበር። በዘመኑ ፖለቲካ በሁለት ተከፍሎ አብዛኛው አባላት ድርጅቱን ጥለው ከመሄዳቸው በፊት ጠንካራ ነበር ማለት ይቻላል። ሁለቱም ድርጅቶች በጣት የሚቆጠር አባላት ይዘው አንዱ ሌላውን ለመጣል ፍልሚያ ከገጠሙ ዓመታት ተቆጥረዋል።

ፍራንክፈርት የድርጅት መሪዎችንም ብቻ ሳይሆን የሕብረት መሪዎችንም አስተናግዳለች። ከኢደኃቅ እስከ ሕብረትና ቅንጅት ድረስ የተደረገው ጉዞ መራራ ነበር። ለተፈጠሩት ሕብረቶች በሙሉ ድጋፋችንን ሰጥተናል። ሲፈርሱም አዝነናል። ከበየነ ጴጥሮስ እስከ ብርሃኑ ነጋ፣ ከመርሻ ዮሴፍ እስከ ኃይሉ ሻውል መሪ ፍለጋ ባዝነናል። እንደ ሕዝብ ምሩን ብለናል። ግን መሪ አላገኘንም። የሚከፋፍል፣ የሚበታትን መሪ እንጂ የሚያስተባብር መሪ አላየንም።

ዛሬ ከዚህ ሁሉ ጥረት በኋላ ለምን መሪ አጣን? ብለን ብንጠይቅ ስህተት አይሆንም። "መሪዎቻችንም" "እኛ እያለን!" ብለው እንደማይፎክሩ ተስፋ አለኝ። የታናሽ ወንድም ታማኝ ጥያቄም ዲፕሎማሲያዊ ሆኖ እኔ ማነኝ? የሚለው ይሁን እንጂ ጥያቄው መሪዎቻችን የታሉ? ነው።

መሪዎችንን ሊመሩን እንዳልቻሉ ግልጽ ነው። ከመከፋፈል ፖለቲካ አልፈው ወደ አንድነት መምጣት አልቻሉም። ራዕይ የላቸውም። ሊያስተባብሩን አልቻሉም። እንኳን ሁላችንን፣ እንመራዋለን የሚሉትንም ድርጅት አንድ አድርገው ለመቀጠል አዳግቷቸዋል።

ሕዝብ ከመሪዎቹ የሚጠብቀውን ባለማግኘቱ ለመሪዎች የሚገባውን ክብር ነፍጓቸዋል ብንል ስህተት አይሆንም። ለመሆኑ የማንኛው የፖለቲካ መሪ ነው ዛሬ ሕዝባዊ ስብሰባ ቢጠራ የታማኝን ያህል ሕዝብ የሚሰበሰብለት? አንወሻሽ ማንም የለም። ግን ምክንያት አለው።

ከዚህ በፊት ደጋግሜ እንደጻፍኩት ስለ ድርጅቶች ወይም ሕብረቶች መከፋፈል ግልጽ የሚታይ እውነት አለ። ይህ እውነት ግን "መሪዎቻንን" አያሳስባቸውም። ድርጅት ወይም ሕብረት ሲከፋፈል አባላት አብረው ይከፈሉ። ጥያቄው ግን ስንት ያህሉ አባላት ናቸው በተከፋፈሉት ድርጅት ውስጥ የሚቀሩት? የሚለው ነው።

በልምድ እንዳየነው ብዙኃኑ ድርጅት ሲከፋፈል ከማንኛውም ወገን ላለመወገን ከትግሉ ይወጣል ወይም ራሱን ያስወግዳል። ዛሬ የግንቦት 7 ሆነ የመኢአድ፣ የመድረክም ሆነ የአንድነት አባላት ቢሰበሰቡ ቁጥራቸው የቅንጅትን ደጋፊ ያህል ሊሆን አይችልም። ዛሬ ኢሕአፓም ሆነ ኢሕአፓ ዴ ከክፍፍሉ በፊት የነበራቸውን የደጋፊ ቁጥር ያህል የላቸውም። ዛሬ መድህን በስም እንጂ በተግባር የለም። ወዘተ ...

ምን አገባን ብለን ካልተውነው በስተቀር እውነቱን ከተናገርን 70 በመቶ የሚሆነው በእንቶ ፈንቶው ጭቅጭቅ ውስጥ ላለመግባት ከትግሉ ራሱን ያገላል። እዚህ ላይ ነው "መሪዎቻችን" 70 በመቶውን ጥለው ለሁለት የተከፈለውን 30 በመቶ ከሆነው ውስጥ ብዙኃኑ ከእኛ ጋር ነው ብለው ሲሟገቱ የምናያቸው። እዚህ ላይ ነው "መሪዎቻችን" ለብዙኃኑ ግድ የሌላቸው። እዚህ ላይ ነው "መሪዎቻችን" የሚሠሩትን አይውቁም እንዴ? ብለን ለመጠየቅ የምንገደደው። "መሪዎቻችን" ሲከፋፈሉ 70 በመቶ ለሚሆኑት አባላት ደንታ የላቸውም። ትኩረታቸው 15 በመቶው አባል ላይ ነው። ለዚህም ነው "መሪዎቻችን" ራዕይ የላቸውም ብንል ስህተት ላይ የማንወድቀው። ብዙኃኑ አንድነታቸውን እየፈለገ እነሱ ግን አናሳም ቢሆኑ ታማኝ አገልጋያቸውን ይዘው፣ "ድርጅት ነን" ብለው ሲኮፈሱ የምናያቸው።

ድርጅት ሲከፋፈል ካለን ልምድ ስንመለከተው የብዙኃኑ ከትግሉ መሸሽ ብቻ ሳይሆን ብዙ አብረው የሚፈጠሩ ችግሮች አሉ። ቅንጅትን ለማፍረስ በተደረገው ትግል ኪስና ኪል የሚባሉ ተቋቁመው ነበር። በእነዚህ በሁለቱ ድርጅቶች ማህል ስንት መናቆር ተደርጓል። ስንት ስም ማጥፋት፣ ስንት ቅስም ሰባሪ ንግግር ተደርጓል። ይህን የርስ በእርስ ትግል ደግሞ ወያኔን እያጠናከረው ተቃዋሚውን ክፍል በሰፊው አዳከመው። ብዙኃኑ ለፖለቲካ መሪዎች ያለውን ክብር አሳጣው። ያ ሁሉ የቅንጅት አባል ሜዳ ላይ ተደፋ። በተለይ በአውሮፓ ስንት ተዓምር የሚሰሩ ዜጎቻችን ተበተኑ። የማይታመኑት ከድርጅት እንዲወገዱ ተደረገ። ይህ ራዕይ ካላቸው መሪዎች የማይጠበቅ ነበር። ግን ተደረገ።

በኢሕአፓ እና በኢሕአፓ-ዴ መካካል ያለው እንዲሁ ነው። ብዙኃኑ አባል ትግሉን ትቶ የኢሕፓን አንድነት መጠየቅ ከጀመረ ሰንብቷል። ግን "መሪዎቻችን" ለዛ ብቁ አይደሉም። ከተነከሩበት የክፍፍል አባዜ ወጥተው ወደ አንድነት ከመምጣትና ለሃገር ጠቃሚ ነገርን ከመሥራት፣ በጥቂት ደጋፊዎቻቸው እየተጨበጨበላቸው አንቱ መባልን ከመረጡ ሰንበትበት ብለዋል።

ዛሬ ጠንካራው መኢአድ በተደጋጋሚ በተደረገው መከፋፈል ተዳክሞ ይገኛል። ዛሬ የግንቦት 7 ምሥጢር የወያኔን ድረ ገጾች ሞልተውታል። ዛሬ የኢሕአፓ አመራሮች የብዙኃኑን ድምጽ መስማት ተስኗቸው የ40 ዓመት ፓርቲያቸውን ወደ ከርሰ መቃብር ለመክተት የቁም ተዝካር አውጥተው አዝጋሚውን ጉዞ ጀምረውታል።

ድርጅት ሲከፋፈል ደግሞ በድርጅት ውስጥ ያለ ዴሞክራሲ እየሞተ ይመጣል። "መሪዎቻችንን" የተቃወማቸውን በሙሉ የሌላው ቡድን አባል አድርገው ይፈርጃሉ። በዚህም ምክንያት ካለተቃዋሚ የፈለጉትን እያደረጉ ስለሚቀጥሉ ተመልሰው ወደ አንድነት ለመምጣት ፍርሃት ያድርባቸዋል። የክፍፍሉ ዋና ምስጢሩ እዚህ ላይ ያለ ይመስለኛል።

መሪዎቻችን የታሉ? ለሚለው የታማኝ ጥያቄ መልሱ አንድ ነው። "መሪዎቻችን" በሠሩት ደሳሳ የድርጅት ጎጆ ውስጥ ተቀምጠው ድርጅታቸውን አቃጥለው እየሞቁ ናቸው ብለን ብንመልስ ስህተት አይሆንም። ለዚህ ነው ሕዝብ ራዕይ ለሌላቸው መሪዎች ከመሰብሰብ ይልቅ በጽናት የሃገራችንን ሰንደቅ ዓላማ ይዞ ለ20 ለታገለው ለታማኝ ክብሩን የሠጠው።

"መሪዎቻችን" ከታማኝ አንድ ነገር መማር ይችላሉ። ለአንድነትና ለሕብረት መቆም እንደሚያስከብር ሊማሩ ይገባል። አለበለዛ ግን "ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ፤ ካለዚያ ድንጋይ መሆንህ ነውና" የሚለውን ማስታወስ ይገባል።

ዛሬ ሕዝብ የሚጠብቀው ከክፍፍል አባዜ ወጥቶ የሠራነው ስህተት ነውና ድርጅታችንን አንድ እናድርግ ብሎ በቆራጥነት የሚነሣን መሪ ነው። ቅንጅትን ማፍረሳችን ስህተት ነበር ብሎ አምኖ ለዳግማዊ ቅንጅት የሚነሳን መሪ ነው። ኢሕአፓን መከፋፈላችን ትክክል አይደለምና ኢሕአፓን አንድ እናድርግ ብሎ የሚነሳ መሪ ነው። መኢአድን አንድ አድርጎ ቀድም የነበረበት ደረጃ፣ ብሎም ከዛ የተሻለ የሚደርስ መሪ ነው። እሱ ለሚደግፋቸው የፖለቲካ እስረኞች ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ድርጅቶች የፖለቲካ እስረኞች የሚቆም መሪ ነው። ሕዝብ የሚፈልገው መሪ መስዋዕትነትን ለመክፈል የተዘጋጀን መሪ ነው። ሕዝብ የሚፈልገው በውጭ ሆኖ የሚታገልን መሪ ሳይሆን ከሕዝብ ውስጥ ሆኖ የሚሞትለትን ነው።

ጥያቄው የጨውና የድንጋዩ ጉዳይ ነው። ጨው መሆን ለፈለገ መንገዱ ቀላል ነው።

ስለአንድነት የሚቆሙ በሠላም ይክረሙ

ሰው ወደ አንድነት ለመምጣት ፍርሃት ያድርባቸዋል። የክፍፍሉ ዋና ምስጢሩ እዚህ ላይ ያለ ይመስለኛል።

ጥያቄው የጨውና የድንጋዩ 

ጥያቄው የጨውና የድንጋዩ ጉዳይ ነው። ጨው መሆን ለፈለገ መንገ

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar