mandag 25. februar 2013
ደህንነቶች አራምባና ቆቦ፡- (ሲጀመር ኢትዮጵያ ውስጥ ደህንነት ሳይሆን ድህነት ነው ያለው)
ደህንነት ማለት እኔ እንደማውቀው ድሮ ስንማር ከራስ አልፎ ለሌሎች ህይወት መረጋጋትና ሰላም መጨነቅ ወይንም ማሰብ ነው፡፡ ለጤንነትም ሆነ ለሰላም ከመጨነቅ አልፈው ቀን ማታ የሚደክሙ አካላቶች ትክክለኛ ደህንነቶች እንላቸዋለን፡፡ ለሀገር ህዝብም ሆነ ለአንድ ግለሰብ ከተጨነቁና ከሰሩ እነዚህን ደህንነቶች እንላቸዋለን፡፡
በአሁን ሰዓት ግን ደህንነቶች እነማን ናቸው? ስራቸውስ
ምንድን ነው?
አሁን ላይ ደህንነቶች የሚለው ስሙና ተግባሩ አራምባና ቆቦ ሁኗል፡፡ ለህዝብ ደህንነት ከማሰብ ይልቅ ለመንግስት እድሜ መርዘምን መርጠዋል፡፡ አንድ ሰው ለሀገሩ ፍቅር ስሜት አድሮበት መንግስት ሲያጠፋ ‹ተው› የሚል ቃን ካነሳ መሄጃና መቀመጫ ያሳጡታል፤ የራሱን ህይወት መኖር ትቶ በጭንቀትና በስጋት እንዲኖር ያደርጉታል፤ ያሸማቅቁታል! ደህንነቶች ስማቸውን ረስተው ለመንግስት ሰራተኛ ሁነዋል፡፡ በፈለገ ሰዓት የሚያጠልቃቸው፣ ሲያሻው ደግሞ የሚወረውራቸው
የመንግስት ጫማ ሁነዋል፡፡ ትምህርት የሚወስዱትም
መንግስትን ለማገልገል እንጂ ህዝብን ለመጠበቅና ለህዝብ ደህንነት እንዲሰሩ አይደለም፡፡ ስራቸው በህዝብ መሀከል ገብተው ሰው ስለ መንግስት የሚያወራውንና በመንግስት ላይ ያለውን አመለካከት ማጥናት ነው፡፡ የሚጠናው ሰውዬ የመንግስትን ጥፋት ካወቀና ለመንግስት ጥሩ ሁኖ ካላገኙት ያሳፍኑታል ወይ ያሳስሩታል ወይንም ……..!
እና እነዚህ ደህንነቶች ናቸው ወይንስ ምን?
እኔ በበኩሌ ደህንነቶች ሳይሆን ጃሱሶች(ጆሮ ጠቢዎች)
ብያቸዋለሁ፡፡
Abonner på:
Legg inn kommentarer (Atom)
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar