ብፁዕ አቡነ ገብርኤል፡- ደብዳቤ ማረጋገጫ ሊኾን አይችልም፡፡ ደርግን አልፈልግም ብለው ዜግነትዎን ቀየሩ፡፡ አሁን ደግሞ አሜሪካዊ ዜግነቴን መልሻለኹ፤ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚሉ ከኾነ ማረጋገጫው ፓስፖርቱ ነው፤ ፓስፖርቱን ያምጡ?
ብፁዕ አቡነ አብርሃም፡- የውጭ ጉዳዩ ደብዳቤ ዜግነቱ እንደተመለሰ ይገልጻል፤ ሊመልስ አይችልም፤ ጉዳዩ ሊፈጸም የሚችለው በአሜሪካው እንጂ በዚህ አይደለም፤ ስለዚህ የውጭ ጉዳይ ደብዳቤ ማስረጃ ሊኾን አይችልም፤ ሰርቲፊኬቱን ያምጡ፡፡
ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ፡- እንዴት ሊሰጥ አይችልም፤ ከዚህ በላይ ምን ይምጣ? ሌላ ተልእኮ አላችኹ?
ብፁዕ አቡነ ገብርኤል፡- እኔ ያን እስካላየሁ አልመርጥዎትም፣ ብፁዕ አባታችን፤ ይህን ይወቁት፡፡
ብፁዕ አቡነ ማትያስ፡- ቤተ ክርስቲያን ስትጠራኝ እምቢ እላለኹ ወይ?
ብፁዕ አቡነ ገብርኤል፡- ገና ዕጩ ነዎት፤ እርሱም ቢኾን በአበው ሥርዐት ሹመት ሲሰጥ አልኾንም፤ አይገባኝም ነው የሚባለው፡፡ ለኅሊናችንና ለቤተ ክርስቲያናችን መኖር መቻል አለብን፡፡ አለበለዚያ ቀድሞ በደርግ ጳጳሳቱና ካህናቱ እየተጠሩ አቡነ መርቆሬዎስን ምረጡ ብሎ እንዳደረገው የእርስዎም ሹመት እንደዚያ ነው የሚኾነው፡፡ ፓትርያሪክ በመንግሥት ተሾመ ተብሎ በሕዝቡ ዘንድ ጥላቻ መታየቱ በአራተኛው ፓትርያሪክም ያየነው ነው፡፡ ይህ ተቀባይነት የለውም፤ መደገምም የለበትም፤ ነገ የሚወገዝ፣ ነገ በታሪክ የሚጠየቅ አባትና ሲኖዶስ መኖር የለበትም፡፡ በሕገ መንግሥቱ መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ እንደማይገባ ተደንግጓል፤ ስለዚህ ገብቶ ከኾነ እጁን እንዲያነሣ እንጠይቃለን፡፡
ነስብሃትና መሰሎቹ አገርና ወገን ሆዳቸው ነው፤ ሃይማኖታቸው ወሲብና መጠጥ ነው፡፡ የሚሉት ሁሉ ለማደናገሪያነት እንጂ የአንጀታቸውን አይደለም፡፡ ትዳርን የማያከብር ዘልዛላ፣ የክፉ ቀንን የትዳር ጓደኛና የልጆቹን እናት ሲያልፍለት አስወጥቶ የሚጥል ጉደኛ፣ ልጆቹን የማይሰበስብ የሌሊት አውሬ ዳንኪረኛ፣ በሽምግልና ዕድሜው ከልጅ ልጆቹ ጋር የሚማግጥ ሠካራም ነውረኛ… በምን ሒሳብ ለሀገር ጠቃሚና ለወገን ተቆርቋሪ ሊሆን እንደሚችል አስቡት፡፡ ይቅርታ – ባደጉ ሀገሮች ከሕጻንነት ጀምሮ የሚመዘገብ የግል ሕይወት ይዞታ ለሥልጣን ዕጩነት ታላቁ መለኪያ በመሆኑ ይህን ስለባለሥልጣኖቻችን ዋልጌነትና እንስሳነት የምላችሁን ነገር በምን አገባህ አናንቃችሁ አትመልከቱት – በኛ ሀገር ደግሞ በተገላቢጦሹ ባለጌ ባለጌው እየተመረጠ ይመስላል ለሥልጣን የሚበቃው – አልጋውና ወንበሩ የሚወደው ጥፍራሞችንና መደዴዎችን መሆን አለበት፡፡
ሀገር ወዳድነት ላግጣ አይደለም – ሀገርን የመምራት ጠንካራ ጎን ደግሞ ከቤተሰብና ከራስ ጤናማ ኑሮ ይመነጫል፤ በሽተኛ ሰው እንኳንስ ሀገርን ራሱንም መምራት አይችልም፤ ሠካራምና እንደልቡ ተናጋሪ ሰው ደግሞ ከዕብድ ተለይቶ አይታይም፡፡ አሁንም ከዚህ ከምለው ነጥብ አኳያ እነስብሃትን ‹ለማያውቋችሁ ታጠኑ!› በሉልኝ፡፡ መቆሚያቸውን ለማደላደል የትግራይን ሕዝብ ‹ያንተዎቹ ነን፤ ከኛ ወዲያ ላንተ የተሻለ አማራጭ የለም፤ አማሮች ከመጡ ሥጋህን ዘልዝለው ይበሉሃል…› በማለት ሊያስፈራሩበት እንጂ በውነት የትግራይነት ስሜት ኖሯቸው አይደለም፡፡ ቀደም ካለ የትግላቸው ወቅት ጀምሮ እስካሁን ድረስ በትግራይ ሕዝብ ላይ የሠሯቸው ወንጀሎች ይህን የሚሉትን ነገር አያረጋግጡላቸውም፡፡ ብሎም ቢሆን ለትግራይ ምድርና ሕዝብ የሠሩት የልማትና የዕድገት እመርታ የለም ለማለት እንዳልሆነ በትህትና ላስታውስ እወዳለሁ፡፡ ሀገራችን ለሚሉት ብዙ ሠርተዋል – ይሁን፡፡ ጥጃ ጠባ እሆድ ገባ ነው፡፡ ቦዕ ጊዜ ለኩሉ ፤ ሌሎቹም በጊዜያቸው ይለማሉ፡፡
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar