lørdag 16. februar 2013

በደመ ነፍስ የምትነዳ ሀገር ወልደማርያምበደመ ነፍስ የምትነዳ ሀገር ወልደማርያም ዘገዬ ዘገዬ



አንድ  ምራቅ መዋጥ የጀመረ የ28 ዓመት ወጣት የኑሮ አጉራ ቢጠናው ጊዜ ወደ ጠንቋይ ቤተ
ይሄዳል፡፡ ለአጋፋሪው ሣንቲም ቢቴ ቦጨቅ ያደርግና ወረፋውን አፋጥኖ በተሎ ይደርሰዋል፡፡ በሁሉም
ቦታ መቼም ይቺ ሙስና ተንሰራፍታለችና በዚህ አይግረማችሁ፡፡ ሀገራችን በተለይ በዚህ አንደኛ ሳትሆን
የምትቀር አይመስለኝም፡፡
ጠንቋይ፤  ምን ፈልገህ መጣህ? አውሊያው ምን እንዲያደርግልህ ትፈልጋለህ አንተ ብላቴና?
አስጠንቋይ፤ የኑሮ ችር ነው ወደዚህ ያመጣኝ፡፡ ሕይወቴ ልፋት ብቻ ሆነ፤ ቀን ከሌት ብለፋ ድካም
እንጂ     ውጤት የለም፡፡ ጓደኞቼ የትና የት ሲደርሱ እኔ በድህነት እየማቀቅሁ ቀረሁ፡፡…
ጠንቋይ፤ አይዞህ፤ ገና ወጣት እኮ ነህ፡፡ ተስፋ አትቁረጥ…
አስጠንቋይ፤ እሺ! በርስዎው መጀን አባቴ፡፡ ያለርስዎ ማን አለኝ፡፡ እስካሁንም ወደርስዎ ያልመጣሁት
        በሞኝነቴ ነው፡፡

ጠንቋይ፤ ዋሪዳዬ እንደሚነግረኝ ያንተ ችግር እስከ 30 ዓመት ዕድሜህ ብቻ ነው፤ አይዞህ፡፡
አስጠንቋይ፤ መጀን በእናንተ! ከዚያስ በኋላ አባቴ?
ጠንቋይ፤ ከዚያ በኋላማ ችግሩን ትለምደዋለህ!
የዛሬ 22  ዓመታት ገደማ መለስ ዜናዊና የጭራቅ መንጋው የወያኔ ጉጅሌ አዲስ አበባን
እንደተቆጣጠረና የቁምና የሞት ሟቹ መለስ የችግሩ መንግሥት ፕሬዚደንት እንደሆነ አካባቢ በምናቤ
ቃለ ምልልስ አድርጌለት ነበር፡፡ ቀንጭቤ ላስታውሳችሁ፡፡
እኔ፤ ክቡር የሽብርተኛው የአፍሪካ ማፊያ ቡድን የሽግግር ፕሬዚደንት መለስ ዜናዊ - የኢትዮጵያ
ሕዝብ በእርስዎ ዘረኛ አገዛዝ እንደተሰቃዬ ለስንት ዓመታት የሚቆይ ይመስልዎታል?  ችግራችን
እስከመቼ ነው? ባጭሩ እስኪ ይግለጹልኝ፡፡
መለስ  ዜናዊ፤ እንደምታውቀው የቲምቡክቱና የሆኖሉሉ ሕዝቦች ለዘመናት በደረሰባቸው የብሔር
ጭቆና…
እኔ፤ የለም፣ እኔ እምልዎት የኛ የኢትዮጵያውያን ወያኔ ወለድ ሰቆቃ እስከመቼ ይቆያል ነው… ወደዚያ
ቢገቡና ቢመልሱልኝ፡፡
መለስ ዜናዊ፤ አልባኒያ በነበርኩበት ጊዜ የዚያች ሀገር ሕዝቦች መሪ ኤንቨር ሆዣ እንደነገረኝ …
እኔ፤ እንዴ? ምን ነካዎት አቶ መለስ - ወደጉዳዩ በቀጥታ ለምን አይገቡልኝም?
መለስ ዜናዊ፤ ጥሩ! የኢትዮጵያ ሕዝቦች ችግር እኛ ሥልጣን ከያዝንበት ዓመት ጀምሮ የሚሰላ እስከ 18
ዓመት ብቻ ነው፡፡
እኔ፤ (በጉጉት) ከዚያስ በኋላ ክቡር ፕሬዚደንት!
መለስ ዜናዊ፤ ከዚያ በኋላማ ትለምዱታላችሁ፡፡
ሁሉንም ለመድነው፡፡ እንዲያውም ከወያኔ ሌላ፣ ሌላ አማራጭ የሌለ እስኪመስለን ድረስ ይህን
ዘረኛና ከፋፋይ ሥርዓት ለመድነው፡፡ ሕዝቡ በጥቅም፣ በዘረኝነት፣ በወንዘኝነት፣ በሃይማኖትና
በመሳሰሉት ወያኔዊ የመከፋፈያ ሥልቶች ተንበርክኮ ራሱን በራሱ በመብላት ላይ ይገኛል፡፡ ወደኅሊናው
ተመልሶ ቆም ብሎ ለሚያስበው ሰው የኢትዮጵያ ሁኔታ በእጅጉ ያስደነግጣል፤ ሀገሪቱና ሕዝቧ
ተመልሰው ሀገርና ሕዝብ ይሆናሉ ተብሎ መጠበቅ እስከማይቻልበት ድረስ ወርደዋል፡፡ አንድ ሕዝብ
ከሃይማኖትና ከባህል ወጥቶ ማተቡን በገንዘብ ከለወጠና እስትንፋሱ ሁሉ በቁሣዊ ነገር ከተቃኘ፣ አንዲት
ሀገር በምስጦችና በመዥገሮች ከተገዛችና ሙስና በዐዋጅ የፀደቀ እስኪመስል ሁሉም ነገር ያለሙስና
የማይንቀሳቀስ ከሆነ ልዩ ኹነት ተከስቶ ሀገርና ሕዝብ ከነዚህ ወጥመዶች እስካልወጡ ድረስ ሀገርም
ሕዝብም የሉም፡፡ የሕዝብ ብዛት መቶ ቀርቶ ሺህ ሚሊዮን ቢደርስ፣ የሀገር የድንበር ግዛት
እንደውቅያኖስ የተንጣለለ ቢሆን የሀገርና የሕዝብ ኅልውና መሥፈርቶች እስካልተሟሉ ድረስ ሕዝብም
ሀገርም አሉ ማለት አንችልም፡፡ ከሞላ ጎደል ሁሉም ከመሥፈርቱ ተንሸራትቶ ተንቀሳቃሽ ሰው መሳይ
አሻንጉሊት እየሆነ ነው፡፡ ይህን ስል አዝናለሁ፡፡ ግን አለማለት ደግሞ አልችልም - ምርጫም የለኝም፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ወቅት የሕዝብ አሃዛዊ ብዛት እንጂ ሌላው ቀርቶ ቅጥ ያለው ሰላምታ

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar