lørdag 5. januar 2013
ከመለስ ወደ “መለሶች”
(በተመስገን ደሳለኝ)
እንደ መነሻ
በ1983 ዓ.ም. ወርሃ ግንቦት መንግስታዊ ስልጣን በሃይል የተቆጣጠረው ኢህአዴግ፣ ከጥቂት ወራት በኋላ ሃያ
ሁለተኛ ዓመቱን ይደፍናል:፡ በእነዚህ አመታት አገዛዙ ያነበረውን ስርዓት በሶስት የዘመን ክፍፍሎች (Historical
Periodization) ወይም ገፅታዎች ከፍለን (በጊዜ እና በግለሰቦች ላይ በተመሰረተ መስፈርት) ማየት እንችላለን፡፡
ከ1983 እስከ 1993 ዓ.ም-‹‹ቡድናዊ››፣ ከ1993-2004 ዓ.ም-‹‹ግለሰባዊ›› እና ከ2005…? ዓ.ም-
‹‹ቡድናዊ›› በሚል፡፡
ከ1983-93
በእነዚህ አመታት ስርዓቱ በኢትዮጵያ ሰማይ ስር የፖለቲካ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል የሚል ተስፋ ከውስጥም
ከውጭም ተጥሎበት ነበር፡፡ ይህንን ተስፋ ያጠናከረው በኃይል የወደቁት ቀደምት ስርዓታት በአዋጅ
ያገዷቸውን፤ ማንኛውም ሰው በመረጠው የፖለቲካ አመለካከት መደራጀት እና ሀሳብን በነፃነት የመግለጽን
መብቶች በአዋጅ በመፍቀዱ ነው፡፡ ከዚህ ክልከላ መሻር በኋላም በርካታ የፖለቲካ ድርጅቶች መፈጠራቸው እና
ነፃነታቸው ገደብ አልባ የነበረ ለቁጥር የሚያታክቱ የግል ፕሬሶች እንደ አሸን መፍላታቸው፣ እንዲሁም ለትችት
ከተጋለጡት ጥቂት አንቀጾቹ በቀር የተወደሰለት ህገ-መንግስት መጽደቅ እና የመጀመሪያው ምርጫ መካሄድ በለውጡ ላይ የተጣለውን
ተስፋ ያጠናከሩ አዎንታዊ ክስተቶች ነበሩ፡፡
በአናቱም ምንም እንኳ የመጀመሪያዎቹ አስር አመታት በህወሓት የበላይነት ላይ የተመሰረተ አስተዳደር የነበረ ቢሆንም፣ ስርዓቱ የጋርዮሽ
አመራርን (Collective leadership) የሚከተል መሆኑ በበጎ እንዲታይ አድርጎት ነበር (ይህ የሆነው ድርጅቱ በትጥቅ ትግሉ ዘመን በዚህ
መልኩ በተቃኘ መተዳደሪያ ደንብ ይመራ ስለነበረ ነው)፡፡ በዚህ የፖለቲካ ጨዋታ ህግ መሰረትም ለሁሉም የሀገሪቱ ጉዳይ (ለኦሮሚያ፣
ለአማራ፣ ለደቡብና ለሌሎችም ክልሎች) የህወሓት አመራር በጋራ ያቅድ፤ በጋራ ይወስንም ነበር፡፡ በተለይ አቦይ ስብሃት ነጋ፣ መለስ
ዜናዊ፣ ተወልደ ወ/ማርያም፣ ስዬ አብርሃ፣ አለምሰገድ ገ/አምላክ፣ አባይ ፀሐዬን የመሳሰሉ በርዕዮተ-ዓለም ትንተና የተራቀቁ የድርጅቱ
ከፍተኛ አመራር አባላት በውሳኔዎች እና በሚወጡ አዳዲስ አዋጆች ላይ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ነበሩ፡፡ የተቀረው የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴም
ቢሆን ‹‹ተናግሮ የሚሰማ›› ከመሆኑም ባሻገር በስብሰባዎች ላይ ሳይቀር ያላመነበትን ሃሳብ በግልፅ የመተቸትና የመቃወም አቅም ነበረው፡
፡ በእርግጥ ይህ በህወሓት የአመራር አባል የተያዘው ቡድናዊ አስተዳደር አክራሪ ብሄርተኛ ከመሆኑ በተጨማሪ ‹‹የተዘጋች ቤተ-መቅደስ››
ተብላ በፖለቲካ ተንታኞች የምትተቸው የአልባንያ ሶሻሊስታዊ አስተዳደር አቀንቃኝ መሆኑ ስርዓቱ ወደ ስልጣን በመጣበት
የመጀመሪያዎቹ ዓመት ተስፋ ተጥሎባቸው ለነበሩ የፖለቲካ ማሻሻያዎች መምከን ዋነኛ ምክንያት ነበር፡፡
ከ1993-2004
ይህ ዘመን ህወሓት/ኢህአዴግ ወደ መለስ፤ የማዕከላዊ መንግስት መዋቅርም ወደ አንድ ግለሰብ የበላይነት የተቀየረበት ተብሎ ሊመደብ
የሚችል ነው፡፡ በዚህ ወቅት የነበረው የስርዓቱ ገፅታ በአንድ ‹‹ጠንካራ ሰው›› (Strong man) ላይ የተመሰረተ ቢሆንም በጥቅሉ
ዓመታዊው የሀገሪቱ ገቢ እድገት ያሳየበት፣ የመንግስት መቀመጫ አዲስ አበባም የተሻለ መሰረተ-ልማት የተካሄደባት ወቅት ነው፡፡
በተለይም የምርጫ 97 ‹‹ሱናሚ›› የፈጠረው ድንጋጤ ገዥውን ፓርቲ ህዝብን ለማዳመጥ (ምንም እንኳ በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ የተገደበ
ቢሆንም) የመሞከር ፍላጎት አሳይቷል፡፡
አቶ መለስ ለፒ.ኤች.ዲ ማሟያ ባዘጋጁት ጥናት ላይ ከማንችስተር እስከ ኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲዎች ድረስ የተከራከሩበትን የ‹‹ልማታዊ
መንግስት›› ፅንሰ ሀሳብን ወደ መሬት ለማውረድ ፍላጐት ያሳዩበትም ወቅት ነበር፡፡ ሃሳቡን ይበልጥ ለማስረፅ ከህልፈታቸው በኋላ
በእርሳቸው እንደሚዘጋጅ በተነገረለት የፓርቲያቸው የንድፈ ሃሳብ መተንተኛ በሆነው ‹‹አዲስ ራዕይ›› መጽሔት ላይ የምዕራቡ ዓለም
መሪ ሃሳብ በሆነው የሌብራል ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ላይ የተመሰረተውን የነፃ ገበያ ፍልስፍና ‹‹ቆሞ ቀር›› ሲሉ ተችተው፤ በተቃራኒው
‹‹ከየትኛውም መብት በፊት ዳቦን ያስቀድማል›› የሚሉትን የእስያን በተለይም የቻይናን ገዥ ሃሳብ ‹‹ሩቅ አዳሪው የእስያ ኢኮኖሚ››
በማለት ከማቆለጳጰስ አልፈው፣ መንግስታቸው በዚህ መስመር የሚጓዝ በመሆኑ የዴሞክራሲው ጥያቄ ብዙም እንደማያሳስባቸው፤
እንዲሁም ‹‹ሀገሬን ማተራመስ ይፈልጋሉ›› ያሏቸውን የኒዮ-ሊበራሊስቶች ክፉ ስራ እንደሆነ በመጥቀስ በአደባባይ ተከራክረዋል፡፡
ተመስገን ደሳለኝ
Abonner på:
Legg inn kommentarer (Atom)
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar