tirsdag 11. desember 2012

                             






                                       

እራስን መጠየቅ – ከኣያና ከበደ

                                                           

  • digg
  • 0
     
    Share

ከኣያና ከበደ ኖ

እርሱ ማነው ከቶ ሠላምን የነሳን ፍቅርን የደበቀ ፣
በመጥፎ ተግባሩ በዓለም .የታወቀ፣
አገር አስደፍሮ ጥቅሙን የጠበቀ፣
ሁልጊዜ ተግባሩ ከእውነት የራቀ።
በ፳ኛው ዘመን ታምርን የሰራ፣
በዘር የተካነ አምላክን ያልፈራ፣
አብሮ የሚበላው ከባዕድ አገር ጋራ፣
መተማመን ያጣ በሚሰራው ሥራ።
መሬትን የሸጠ ቆራርጦ ቆራርጦ፣
ሕዝቦችን የገዛ እንደባሪያ እረግጦ ,
ወገን ያሰደተ ሙህራኑን መርጦ፣
ውሸት የሚያወራ ውእነትን ገልብጦ፣
ሰውችን የጎዳ ደማቸውን መጦ።
እር ሱ ማነው ከቶ ንገርኝ ወገኔ ፣
ሠዉነት የሌለዉ ጨካኝ አርመኔ።
ለስደት ያበቃን ኢትዮዽያን አራቁቶ፣
ሰላምን የነሳን መሃላችን ገብቶ፣
ወገኔ ተጠየቅ ዕርሱ ማነውከቶ።
ደደቢት ተወልዶ ደደቢት ያደገው፣
የጭፍሮች መሪ ነው ይህን የሚያረገው።
እሱነው ወያኔ ልንገርህ ወገኔ፣
አንተም ፊት አትሥጠው ውቀሰው እንደኔ፣
ወገንህ አይደልም ጨካኝ አረመኔ።
እሱነው ወያኔ የባንዳውች ጭፍራ፣
ምክ ር አለው ልበል ከዳብሎስ ጋራ፣
ይመርመር ምሥጥሩ መልሦ ይጣራ፣
ተገዝቷል ልብል መልካም እንዳይሰራ
ምንጊዜም ድርጊቱ የዳብሎሥ ሥራ።
በትረ ንጉሥ ይዞ አገርን የሸጠ፣
የህጻ ናት አንገት በሰይፍ የቆረጠ፣
መደሰትን ነስቶ ችግርን የሰጠ፣
ምንትጠብ ቃለህ ከዚህ የበለጠ ።
ከፋን በቃህ በሉት እጃን አንሱ ፣
ይቀጥል ይሆናል ልብ የለውም እሱ፣
ባለደማችንነው አስራት ወልደየስን ሽርብሬን አስታውሱ፣
የወያኔን በደል በጭራሽ አትርሱ፣
ወገን ለንጻነት በህብረት ተነሱ .::
መሰረቱ ይጥፋ ዳግሚያ እንዳይነሱ ።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar