tirsdag 11. desember 2012
የአባይ ጥያቄ - ፩
ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣ ሃያ አንድ ዓመታቶች አልፈዋል፡፡ በእነዚህ ዓመታት አቅዶ ከተገበራቸውም ሆነ የውሃ ሽታ ሆነው ከጠፉ
ፕሮጀክቶች ሁሉ በአባይ ውሃ ላይ እገነባዋለሁ ያለው የ‹‹ህዳሴ ግድብ›› ግዙፍና የተለየ ነው፡፡ ይህንን በመንተራስ ተመስገን ደሳለኝ፣
ሙሉነህ አያሌው እና ኃይለመስቀል በሸዋምየለህ የግድቡን ግንባታ ተከትሎ ከግብፅ ለሚነሳ ተቃውሞ፣ ለዓለም አቀፍ መድረኮች
መከራከሪያ እና የኢትዮጵያ አቋም ምን መሆን እንዳለበት እንዲህ ይመክራሉ፡፡
‹‹…ታላቁ አባይ መነሻው ከጣና ሃይቅ በስተደቡብ 167 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው ከግሽ ተራራ ስር ያለች የጠበል ምንጭ ናት፡፡
ቦታው ግሽ አባይ ምንጭ የሚባል ሲሆን፣ በምዕራብ ጎጃም ሰቀላ አውራጃ ውስጥ ይገኛል፡፡ ይህች ምንጭ አነስተኛ ብትሆንም ኩልል ያለ
ውሃ ያላት፣ በቀርከሃ ተክል አጥር የተከበበች ናት፡፡ በአቅራቢያዋም የቅዱስ ሚካኤልና የዘርዓብሩክ ቤተክርስቲያናት ይገኛሉ፡፡
የቤተክርስቲያናቱ ካህናት እና ምዕመናን መንፈሳዊ ኃይልን ለማግኘት ወደ ተቀደሰችዋ የአባይ ምንጭ የሚመጡ ጠባቂዎቹ ናቸው›› ሲል
የአባይ ወንዝን መገኛ የሚተርከው እ.ኤ.አ. በ2003 ዓ.ም “The Nile: Historical‚ legal and developmental perspectives”
በሚል ርዕስ የታተመው የገብርፃዲቅ ደገፉ መፅሐፍ ነው፡፡
ለግብፃውያን የተቀማጠለ ኑሮ እና ጠንካራ ኢኮኖሚ ዋስትና መሆን የቻለው ናይል ዋና ገባሪው ምንጭ ኢትዮጵያ ቢሆንም ‹‹ለኢትዮጵያ
ካለው አበርክቶ ይልቅ ‹ዕዳው› ይበዛል›› ይላሉ የውሃ ፖለቲካ ምሁራን፡፡ በእርግጥም አባይን የህልውናዋ መሰረት ያደረገችው ግብፅ
ለኢትዮጵያ ታሪካዊ ባላንጣ መሆኗን ጠቅሰው የሚከራከሩ ተንታኞች፤ በዋናነት የሚያነሱት አባይን ኢላማ በማድረግ ሠራዊቷን በቀጥታ
ካሳተፈችበት የ‹‹ጉንዲት›› እና ‹‹ጉራ›› ጦርነት በተጨማሪ፤ በዘወርዋራ ለኤርትራ መገንጠል፣ ለኦነግ፣ ለኦብነግ፣ ለኦሮሞ እስላሚክ
ድርጅት፣ ለአል-ኢትሀድ እና ለመሳሰሉት ተቃዋሚዎች መጠናከር ምክንያት ያደርጓታል፡፡ የዚህ ሁሉ መግፍኤ ‹‹የግብፅ መስራች አባት››
እየተባለ የሚነገርለት ከኸዲቭ ኢስማኤል ‹‹ኢትዮጵያ ለግብፅ አደጋ በመሆኗ በኃይል ወረን ወደ እስልምና መንግስትነት መቀየር፤ አሊያም
በማሸበር እና በማሳቀቅ ህልውናዋ እንዳይረጋጋ በማድረግ ይዘናት መቀጠል ብቻ ነው አማራጫችን›› ከሚለው ታሪካዊ ፖሊሲው ጋር
ይያያዛል፡፡
ግብፅ ዛሬም ድረስ ኢትዮጵያ እና አባይን በተመለከተ የምታራምደው አቋም ከኸዲቭ ኢስማኤል መጽሐፍ የተገለበጠ ነው፡፡ በዋና ከተማዋ
ካይሮ የሚገኙት የውጭ ጉዳይ እና የደህንነት መስሪያ ቤቶች ቀዳሚ ተግባር የአዲስ አበባን መንግስት ሰላም ማወክ፣ ተቀናቃኞቹን
ማጠናከር እና የመላ ሀገሪቱን የልብ ትርታ ማድመጥ ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ግብፃውያን የቀድሞ ፕሬዝዳንት የሆስኒ ሙባረክን
ከስልጣን መነሳትን ያህል ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የጀመረችው ‹‹የህዳሴ ግድብ›› ትኩረት የሳበ አጀንዳ ሆኖአል፡፡ ይህንንም ተከትሎ
ስልጣን በያዘው በ‹‹ሙስሊም ወንድማማች›› እና ‹‹አብዮታችን ተቀለበሰ›› በሚሉ ግብፃውያን መካከል የተፈጠሩ ክፍተቶች ሳይቀሩ ቸል
ተብለው በአባይ ጉዳይ ላይ ከዚህ ቀደም እንዳደርጉት ሁሉ አሁንም ከነልዩነታቸው በጋራ ተሰልፈዋል፡፡
ኢትዮጵያም ከ1990ዎቹ መጀመሪያ ጀምሮ በአባይ ላይ የመጠቀም መብቷን የማስከበር እንቅስቃሴዋን በገቢር ለማሳየት እየሞከረች ነው፡፡
ኢህአዴግ ከ1995 ዓ.ም እስከ 2016 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ በአባይ ውሃ ላይ የልማት ዕቅድ እንዳዘጋጀ ይፋ ሲያደርግ፣ የካይሮ መንግስት
ዕለቱኑ የማስፈራሪያ መግለጫ አውጥቷል፡፡
ሆኖም ኢትዮጵያ ‹‹አዘጋጅቼዋለሁ›› ያለችውን ዕቅድ ለመተግበር ሳትሞክር፣ ግብፅም የ24 ሰአት ክትትሏን ሳታቋርጥ ጉዳዩ ቢወይብም
በተለይ በ1997 ዓ.ም. አጋማሽ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በአባይ ለመጠቀም ማንንም እንደማያስፈቅዱ ለቢቢሲ ከተናገሩ
ከሰባት አመት በኋላ መሰረተ ድንጋይ የተቀመጠለት ‹‹የህዳሴ ግድብ›› በሁለቱ ሀገራት መካከል ውጥረት ፈጥሮአል፡፡ የግብፅ ጦር ሰራዊት
አዛዦች ተደጋጋሚ ጊዜ ዛቻ መሰል አስተያየቶችን በካይሮ ለሚታተሙ ጋዜጦች ሰጥተዋል፡፡ እነዚህ የጦር አዛዦች መልዕክቱ ለኢትዮጵያ
እንደሆነ በሚያሳብቅ መልኩ የሰራዊታቸውን ብቃት፣ የታጠቀውን መሳሪያ ብዛት እና ዘመናዊነት የትርክታቸው ማጣፈጫ እያደረጉት
ነው፡፡
እሰጣ-ገባው በእንዲህ አይነት ሁናቴ የቀጠለ ቢሆንም የኢትዮጵያ መንግስት የፖለቲካ ተንታኞች ‹‹ማህበረሰባዊ ዲፕሎማሲ›› /Public
diplomacy/ የሚሉትን የማግባቢያ መንገድ በመከተል ከማህበረሰቡ የተውጣጣ አንድ ቡድን አዘጋጅቶ ወደ ግብፅ በመላክ ከዚህ ቀደም
ከተደረጉ ስምምነቶች ውጭ ኢትዮጵያ የተለየ ነገር እያደረገች እንዳልሆነ እንዲያስረዱላት መወሰኑ እንደበጎ ተግባር ቢወሰድለትም፣ ግብፅ
ከያዘችው ፅንፈኛ አቋም ግን የመለዘብ ምልክት አላሳየችም፡፡
የውሃ ፖለቲካ
በተለያዩ አህጉራት ውስጥ የሚገኙ ድንበር-ዘለል ተፋሰስ ወንዞችን በሚመለከት የተለያዩ ዓለም-ዓቀፍ ህግጋትን የሚደግፉ መርሆች
ከ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ወዲህ ተፈጥረዋል፡፡ እነዚህ መርሆች በዋናነት ውሃን ማዕከል ያደረጉ ግጭቶችን ለማስቀረት በተለያዩ
Abonner på:
Legg inn kommentarer (Atom)
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar