søndag 16. desember 2012

ከዳር ቆሞ ለዉጥን መጠበቅ የህልም እንጀራ


ከዳር ቆሞ ለዉጥን መጠበቅ የህልም እንጀራ

ፍስሀ እሸቱ (ዶ/ር)
በሀገራችን ያለዉን ሁኔታ ስንመለከተዉ በጥቂት ቃላት ማጠቃለል የቻላል። ይህም
ከድጡ ወደ ማጡ የሚለዉ በጥሩ ሁኔታ የሚገልጸዉ ይመስለኛል። አበዉ ጉልቻ
ቢለዋወጥ እንደሚሉ አፈናዉ፤ ስለላዉ፤ እስሩ፤ ግድያዉ፤ ስደቱ፤ ዘረፋዉና፤ ማናለብኝነቱ
ሳይቋረጥ ቀጥሏል። አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትርና አጋሮቻቸዉም ደግመዉ ደጋግመዉ
አስረግጠዉ እንደተናገሩት ለዉጥ የሚባል ነገር እንደማይታሰብና የነበረዉ ሁኔታ ባለበት
እንደሚቀጥል ነዉ። ከዚህ አንጻር የለዉጥ የተስፋ ጭላንጭል እንደሌለ በወሬ ብቻ
ሳይሆን በተግባራቸዉም አሳይተዉናል። ምንም መራር ቢሆንም እዉነታዉ ግን ስርአቱ
መሪዉን ቢያጣ እንኳን፤ በአላማ፤ በአቅም፤ በድርጅትና፤ በስነልቦና፤ ፍጹም የበላይነቱን
ተጎናጽፎ ይገኛል።
አበዉ እንደሚሉት አቅሙን የማያዉቅ ሞቱን አፋጠነ እንደሚሉት በተቃዋሚዉ ባንጻሩ
የሚታዉ ደሞ፡
1ኛ.  እኛ ከወኔ ወኔ የለን፤ መስእዋትነት ለመክፈል ዝግጁነት የለንም
2ኛ.  ከአንድነት አንድነት የለን
3ኛ.  ከአቅም አቅም የለን
4ኛ.  ነጻነትን በምጽዋት ለማግኘት እንፈልጋለን (በዉጭ ሃይሎች)፤ ሌሎች በታገሉትና
መስእዋትነት በከፈሉት ተጠቃሚ መሆን እንፈልጋለን
5ኛ.  የስርአቱ አራማጆች ወድቆ መነሳትን ሲችሉበት እኛ ግን የወደቅንበት ቀርተናል፤
ከዚህ በፊት በደረሱብን ሽንፈቶች ለምሳሌ በቅንጅት ሽንፈት ተስፋ ቆርጠን
ተበታትነናል
6ኛ.  ጠላታችን ማን እንደሆነ ማወቅ ተስኖናል፤ ከስርአቱ ይልቅ እርስ በራሳችን ጦር
መማዘዙን መርጠናል
7ኛ.  በጭንቅላታችን ሳይሆን በስሜታዊነት የምንመራ ሆነናል፤ በአላማ ሳይሆን በጥላቻ
ምንመራ ሆነናል
8ኛ.  የረዥም ግዜ ዉጤት ሳይሆን አጭር ዉጤት እንፈልጋለን፤ በዚህም ምክንያት ቶሎ
ተስፋ እንቆርጣለን
9ኛ.  ሁሉም ፈላስፋ፤ አዋቂ፤ መፍትሄ ሰጪ ሆኖ፤ መደማመጥ ጠፍቷል፤ ሁሉም አዋቂ፤
ተናጋሪ፤ ሆኖ የሚታገለዉ ግን ጥቂት ሆኗል - ወሬ ወሬ ወሬ -ሀሜት ሀሜት
ሀሜት - ኩነና ኩነና ኩነና - ተናጋኔ ተናጋሪ ተናጋሪ - አድራጊ ጠፋ (የኢንተርኔት፡
ፓልቶክና ሬድዮ፤ ስብሰባ ታጋዮች ሆነናል)

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar