fredag 30. november 2012

Addisua Ethiopia :  ኢትዮጵያ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ምርት እድገት አሳየች! አቤ ቶኪቻው


ኢትዮጵያ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ምርት እድገት አሳየች!

አቤ ቶኪቻው
አቶ ሃይለማም ሲፈሩ ሲተቡ ቆይተው ዛሬ የካቢኔ ሹመት ለማደረግ ፓርላማ ብቅ ብለው ነበር አሉ። ይዘዋቸው ከመጡዋቸው ካቢኔዎቻቸው መካከል ሌላ ሁለት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮችን ይገኙበታል።ኢትዮጵያ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ምርት እድገት አሳየች!
አቶ ሃይለማሪያም ሲያስቡት ሲያስቡት ለአቶ ደመቀ ብቻ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነቱን መስጠት አይችሉትም ብለው ሰጉ መሰለኝ…(መሰለኝ ነው ያልኩት) ዛሬ አቶ ሙክታር ከድር እና አቶ ደብረ ፅዮን ገብረሚካኤልን ደጋፊ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አድርገው አሹመዋል። በጥቅሉ በአሁኑ ሰዓት ሀገራችን ሶስት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች አሏተው።
እኛ ሹመቱን ከላይ ከላይ የምናየው የመንግስታችን አድናቂዎች “እሰይ ሀገራችን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እድገት እመርታ አሳየች” ብለን ካገኘን ፅዋ ካጣን ደግሞ ግንባራችንን እያጋጨን ደስታችንን እንገልፃናል።
የምር ግን አቶ ሃይለማሪያም ያኔ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ይሰሩ የነበረ ጊዜ እንደው ሰውየው መለስ ሆነውባቸው “ተሸከሙ” ያሏቸውን ሁሉ “እሺ ጌታዬ” ይሏቸው ነበር እንጂ፤ የጫኑባቸው ሸክም በእጅጉ ከብዷቸው ነበር ማለት ነው!? አዎና ይኸው አቶ ደመቀ ሸክሙን አይችሉትም ብለው የጠረጠሯቸው ከራሳቸው ልምድ ተነስተው አይመስልዎትም!?
ሌላው ጥርጣሬ የኢህአዴግ “ፈላጭ ቆራጮች” (ይሄ “ፈላጭ ቆራጭ” የሚለው ቃል ኢህአዴግ ይፈልጣል ይቆርጣል ብሎ ለማሽሟጠጥ ታስቦ የገባ ቃል አለመሆኑን በቅንፍ አሰውቀን እንቀጥል) እና የኢህአዴግ ፈላጭ ቆራጮች አቶ ሃይለማሪያምን ለአንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ብቻ አምነው መተው ምቾት አልተሰማቸውም ይሆናል!
ለማንኛውም ዶክተር ቴውድሮስ አድሃኖምን ውጪ ጉዳይ ሚኒስትርነት ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል። ዶክተሩ ከጤና ጥበቃ የተነሱት ጤና ስለነሱ ይሁን ወይስ የውጭ ጉዳዩ ስራ ህክምና ስለሚያስፈልገው አልታወቀም። ሲታወቅ እናወጋዋለን!

torsdag 29. november 2012

 
Posted by Picasa

DAGMAWIE TEWQODERSOCH

 
Posted by Picasa

አንድ አድርገን: ተአምር

አንድ አድርገን: ተአምር: (ከደቂቀ ናቡቴ)፡-የካቲት 16/2004 ዓ.ም የቃል ኪዳኗ ታቦት ለእመቤታችን ቃል ኪዳን በተገባበት ቀን ለማክበር ከህናት ወደ ዋሻው ገብተው ታቦቷን ተሸክመው ወደ ድንኳን መጡ፡፡ እልልታው ቀለጠ ግማሹ በደስታ የለቅሳ...

አንድ አድርገን: ተአምር

አንድ አድርገን: ተአምር: (ከደቂቀ ናቡቴ)፡-የካቲት 16/2004 ዓ.ም የቃል ኪዳኗ ታቦት ለእመቤታችን ቃል ኪዳን በተገባበት ቀን ለማክበር ከህናት ወደ ዋሻው ገብተው ታቦቷን ተሸክመው ወደ ድንኳን መጡ፡፡ እልልታው ቀለጠ ግማሹ በደስታ የለቅሳ...
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት አርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ልዩ ስሙ ጃንሱማ በተባለው ቦታ ወታደራዊ ጥቃት ፈጸመ
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በወያኔ ቅጥረኛና ምንደኛ የልዩ ሃይል ታጣቂ ቡድን ላይ የጀመረውን የማጥቃት ዘመቻ አጠናክሮ በመቀጠል ሕዳር 15-2005 ዓ.ምEthiopian People Patriots Front - EPPF አርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ልዩ ስሙ ጃንሱማ በተባለ ቦታ ባደረገው ውጊያ 14 የጠላት ወታደሮችን በመግደልና 12 በማቁሰል ከፍተኛ ወታደራዊ ድሎችን በማስመዝገብ ግንባሩ የተሰማራበትን ግዳጅ በድል እየተወጣ መሆኑን የግንባሩ ወታደራዊ መምሪያ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዘራፊውና ከነፍሰ-ገዳዩ የወያኔ አምባገነናዊ ገዥ ቡድን ለማላቀቅ ያለው ብቸኛ አማራጭ መንገድ በትጥቅ ትግል ስርዓቱን ማንበርከክ መሆኑን ጠንቅቆ ያወቀው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ሀገርንና ወገንን ለመታደግ ቆርጦ በመነሳት በሰሜኑ የሐገራችን ክፍል ወታደራዊ ስትራቴጅውን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ ሰሞኑን አርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ልዩ ስሙ ጃንሱማ በተባለው ቦታ ባደረገው የማጥቃት ዘመቻ 26 የጠላት ወታደሮችን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ወታደራዊ የበላይነትን የተቀዳጀ ሲሆን፣ ከሞቱት 14 የልዩ ሃይል ታጣቂ ቡድን መካከል አበበ የሚባለው የቀራቅር ተወላጅና አለልኝ የሚባል የደባርቅ ተወላጅ የሆኑት ከፍተኛ አመራሮች መሞታቸውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ወታደራዊ መምሪያ ገልጿል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት አርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ልዩ ስሙ ጃንሱማ በተባለ ቦታ በፈፀመው ወታደራዊ የማጥቃት ዘመቻና በጠላት ላይ ባደረሰው ከፍተኛ ኪሳራ የተደናገጠው የወያኔ ቡድን ተጨማሪ ጦር ወደ አካባቢው እያጓጓዘ መሆኑንም ከአካባቢው የተሰራጩ የዜና ምንጮች አጋልጠዋል።
ይሁን እንጅ በዓላማቸው ፅናትና በሐገራዊ ፍቅር የተገነባው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በጀመረው ሕዝባዊና ሐገራዊ ተልዕኮ የፈረጠመ ክንዱን በጠላት ላይ በማሳረፍ አይበገሬነቱንና ቁርጠኝነቱን ሰሞኑን በተከታታይ ባደረጋቸው ውጊያዎች አስመስክሯል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል።
በመጨረሻም ውጊያው በተፈፀመባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት የጀመረውን ወታደራዊ የማጥቃት ዘመቻ አጠናክሮ እንዲገፋበትና እኛም የተለመደውን ሁለንተናዊ ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር ግንባሩን ለመቀላቀል የሚያስችል መነሳሳትን የፈጠረ አኩሪ የአርበኝነት ገድል መፈፀሙን ነዋሪዎች አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በበኩሉ በስልጣን ላይ ያለው ፀረ-ሕዝብና ፀረ-ኢትዮጵያ ወንጀለኛ የወያኔ ቡድን የመጨረሻ ግብዓተ-መሬቱ እስኪፈፀም ድረስ ወታደራዊ የማጥቃት ዘመቻውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፆ የአገዛዙን እድሜ ለማሳጠርም የተለመደው ሕዝባዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለመላው ነፃነት ናፋቂና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ሀገራዊ መልዕክቱን አስተላለፏል

የእስላም ኢትዮጵያውያን የትግል ስልት


የእስላም ኢትዮጵያውያን የትግል ስልት
/ መስፍን ወልደማርያም
በአለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ እስላም ኢትዮጵያውያን ማካሄድ የጀመሩት ትግል በዓይነቱም፣ በስፋቱም፣ በአስተሳሰቡም፣ በስሜቱም እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ውስጥ ከአገዛዙ ጋር ከተደረጉ ትግሎች በጣም የተለየ ነው፤ በመጀመሪያ ደረጃ ትግሉ ለሃይማኖት ነጻነት ነው፤ ስለዚህም በአገዛዙ በኩል የፖሊቲካ ዓላማና የፖሊቲካ መልክ እየተሰጠው ሲሆን በእስልምና ምእመኖቹ በኩል ግን ትግሉን ከፖሊቲካ የጸዳ ለማድረግ ግሩም የሆነና የተሳካ ጥረት እያደረጉ ነው፤ ሁለተኛ የትግሉ ስልት ፍጹም ሰላማዊ በመሆኑ የአገዛዙን የጉልበት ስልት እያከሸፈ ያጋለጠው ይመስላል፤ አንዱና ዋነኛው የትግሉ ሰላማዊነት መግለጫ በቤተ መስጊድ መወሰኑ ነው፤ ይህ ስልት አዲስ አይደለም፤ በብዙ የአረብ አገሮች የሚጠቀሙበት ነው።                                                         
ተፋላሚዎቹ ያልተገነዘቡዋቸው አንዳንድ ጉዳዮች ይታዩኛል፤ አንደኛ እስልምና በጎሣ የታጠረ ባለመሆኑ ከወያኔ/ኢሕአዴግ የአመራር መሠረት ጋር የመቃወም ዝንባሌ ያሳያል፤ እስልምና አብዛኛዎቹን፣ በተለይም ትልልቅ የሚባሉትን ጎሣዎች ሁሉ በተለያየ ደረጃ የሚያቅፍ ነው፤ ስለዚህም አንዳንዶች የእስልምና መሪዎች ሌሎች (ማለትክርስቲያኑ) አልተቀላቀሉንም እያሉ የሚያላዝኑበትን ቆም ብለው መመርመር ያሻቸዋል፤ ክርስቲያኑ በተለይ የኢትዮጵያ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታዮች ያሉበትን ሁኔታ በትክክል መረዳት ያስፈልጋል፤ እስላሞች ገና ቀደም ብለው ከብዙ ዓመታት በፊት በተደረገ ትልቅ ሰላማዊ ሰልፍ ‹‹እስላሞች በጎሣ አይከፋፈሉም›› በማለት የገለጹትን ቁም-ነገር አገዛዙ የረሳው ወይም እስላሞቹ ረስተውታል ብሎ ያሰበ ይመስላል፤ አለዚያ እንዲህ ያለ የከረረ እልህ ውስጥ የገባበትን ምክንያት ለመረዳት ያዳግታል፤ ይቺ ባቄላ ያደገች እንደሆን የሚያሰኝ ነገር ለብዙዎች ሰዎች ምንም አልታየም፤ በጉልበት የማይጨፈለቅ ምንም ነገር የለም ከሚል እምነት ተነሥተው ከሆነ ስሕተቱ እየታየ ነው።
በዚህ ጉዳይ ላይ የእስላሙ ኅብረተሰብ ገና በጠዋቱ በጎሣ የመከፋፈሉን አመራር እንደማይቀበለው በማያጠራጥር መንገድ የገለጠ ይመስለኛል፤ ነገር ግን ብዙ ቤተ ክርስቲያኖች የጎሣ ትግላቸውን ወደቤተ እግዚአብሔር አምጥተው የተከፋፈሉና የተዘጉም ቤተ ክርስቲያኖች ነበሩ፤ ይህ የሚያሳፍር ነው፤ ቤተ መስጊዶች እዚህ ደረጃ አልወረዱም፤ እስልምና በጎሣ አይቀደድም፤ እስላሞች ሁሉ የአላህ ልጆች ናቸው፤ በቤተ መስጊድ የሚሰበሰበው ሁሉ በአላህ ልጅነቱ ነው፤ ስለዚህም በመሀከላቸው ልዩነት የለም፤ ይህ የእስላሞች አቅዋም ሃያ ዓመት ተፈተነ፤ የማይበገር ሆነ፤ ስለዚህም ከጎሣ አስተሳሰብ ወጥቶ ሌላ ቀዳዳ መፈለግ ግዴታ ሆነ፤ አል-ሀበሽ አስፈላጊ የሆነው ለዚህ ነው።
እስቲ ጉዳዩ ለሁላችንም ግልጽ እንዲሆንልን ወደክርስትና ዞረን እንየው፤ የኢትዮጵያ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ከነገ ጀምሮ የሉተራን ቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት ተከተሉ ቢባል አንደኛ የኢትዮጵያ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን (ካለች) ምን ትላለች? ሁለተኛ የኢትዮጵያ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ምን ይላሉ? ሦስተኛ የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 11 ‹‹መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፤›› የሚለው በጤና አለ ወይ? ብሎ መጠየቅ የማይቀር ይሆናል፤ መልሶቹስ ምን ይሆናሉ?
ከጥቂት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን ስዒረ ሊቀ ጳጳስ እንደተደረገ አሁን ታወቀ፤ ቤተ ክርስቲያኒቱም፣ ምእመናኑም፣ ማንም ምንም ያለ የለም፤ የተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያንን ሊቀ ጳጳስ የሻረው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ታምራት ላይኔ ዛሬ እግዚአብሔር ተገለጠልኝ በማለት ሊቀ ጳጳስዋን የሻረባትን ቤተ ክርስቲያን ትቶ ወደሌላ ተገልብጦአል፤ የተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን አባል በነበረበት ጊዜ የሠራውን ኃጢአት ዛሬ የሌላ ቤተ ክርስቲያን አባል ሆኖ እውነቱን ገልጦልናል፤ ታምራት ላይኔ የኢትዮጵያ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያንን ከለቀቀ በኋላ የክርስቶስን ጸሐየ ጽድቅነት መረዳቱ ለቤተ ክርስቲያኒቱ የሚያሳፍር ነው፤ ከዚያም በላይ የኢትዮጵያ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን አሁንም እውነቱን አላወጣችም፤ አንድም ለሹመት ያኮበኮበ ጳጳስ የክርስቶስን ጸሐየ ጽድቅነት አምኖና ተቀብሎ እውነቱን ለመናገር የደፈረ አልተሰማም፤ ጴጥሮሳዊነት ከጴጥሮስ ጋር ተቀብሮአል አንበል? ይበልጥ ያሳፍራል፡፡
የኢትዮጵያ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያንን ለንጽጽር አመጣሁ እንጂ ዋናው ነገሬ በእስልምና ሃይማኖት ላይ ነው፤ ድርቅና ቁልጭ ያለው እውነት እስልምና አስፈላጊውን መስዋእት ከፍሎ በሰላማዊ መንገድ ጎሠኛነትን ተቃወመ፤ ተቋቋመ፤ አሁን ደግሞ አንደኛ በእስልምና ምእመናን ላይ እንዲጫን የታቀደውን አዲስ የእስልምና ዓይነት አንቀበልም በማለትና ሁለተኛም የእስልምና ካህናትን የምንመርጠው ራሳችን ምእመናኑ ነን፤ ሦስተኛም የእስልምና ካህናቱ ምርጫ የሚካሄደው በመንፈሳዊ ቦታ በቤተ መስጊድ ነው እንጂ በፖሊቲካ ቦታ በቀበሌ አይደረግም አሉ፤ በጎሣ አንከፋፈልም ብለው ጥንካሬያቸውን ያሳዩትን እስላሞች በሃይማኖት ለመከፋፈልና ካህናቶቻቸውን ራሳቸው በየመስጊዳቸው እንዳይመርጡ መከልከል በግልጽ ሕገ መንግሥቱን መዳፈር ነው።
ሁለተኛው ቁም-ነገር አገዛዙ በየቀበሌው ያካሄደው ከሕዝብ ፈቃድ ውጭ ለሆነ ምርጫ እስላሙ ኅብረተሰብ የሰጠው ሰላማዊ መልስ የማያዳግምና የሚያስደንቅ ነው፤ በአገዛዙ ስልት በተመረጡት ሰዎች በሚተዳደሩ ቤተ መስጊዶች ውስጥ አንሰግድም በማለት መስጊዶቹን ባዶ ማድረጋቸው አገዛዙን ራቁቱን አቁሞ ስሐተቱን ያጋለጠው እውነተኛ ሰላማዊ ትግል ነው፤ በቅርቡ ሦስት የአፍሪካ፣ አንድ የእስያ፣ ሁለት ዓለም-አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች ለአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለአቶ ኃይለ ማርያም ኢትዮጵያ ለዓለም-አቀፍ ሕጎች የገባችውን ቃል ኪዳኖች ሁሉ እንድትጠብቅ ከመቼውም የበለጠ ጥረት ማድረግ እንዳለባት የሚገልጽ ረጅም ደብዳቤ ተልኮላቸዋል፤ ለመብቶቻቸው የቆሙ ሁሉ፣ ጋዜጠኞችም ይሁኑ የሃይማኖት ሰዎች በሽብርተኛነት እየተከሰሱና እየተፈረደባቸው ወህኒ ቤት በመግባታቸው ፍርድ ቤቱንም ወህኒ ቤቱንም ጎብኝተው የሄዱት የስዊድን ጋዜጠኞች በሚያሳፍር ሁኔታ ለዓለም አጋልጠውታል።
የቤቴ መቃጠል ለትኋኑ በጀኝ ያለው ቂል ሰው ነው፤ ከኑግ ጋር የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ ያለው ሰው ሰነፍ ነው፤ ቂልነትም፣ ስንፍናም ለመሪዎች አይበጅምና እግዚአብሔር በጎ መንፈሱን ያሳድርባቸው፤ ያሳድርብን።
ተመሳሳይ ጦማሮችን ይመልከቱ


ተፋላሚዎቹ ያልተገነዘቡዋቸው አንዳንድ ጉዳዮች ይታዩኛል፤ አንደኛ እስልምና በጎሣ የታጠረ ባለመሆኑ ከወያኔ/ኢሕአዴግ የአመራር መሠረት ጋር የመቃወም ዝንባሌ ያሳያል፤ እስልምና አብዛኛዎቹን፣ በተለይም ትልልቅ የሚባሉትን ጎሣዎች ሁሉ በተለያየ ደረጃ የሚያቅፍ ነው፤ ስለዚህም አንዳንዶች የእስልምና መሪዎች ሌሎች (ማለትክርስቲያኑ) አልተቀላቀሉንም እያሉ የሚያላዝኑበትን ቆም ብለው መመርመር ያሻቸዋል፤ ክርስቲያኑ በተለይ የኢትዮጵያ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታዮች ያሉበትን ሁኔታ በትክክል መረዳት ያስፈልጋል፤ እስላሞች ገና ቀደም ብለው ከብዙ ዓመታት በፊት በተደረገ ትልቅ ሰላማዊ ሰልፍ ‹‹እስላሞች በጎሣ አይከፋፈሉም›› በማለት የገለጹትን ቁም-ነገር አገዛዙ የረሳው ወይም እስላሞቹ ረስተውታል ብሎ ያሰበ ይመስላል፤ አለዚያ እንዲህ ያለ የከረረ እልህ ውስጥ የገባበትን ምክንያት ለመረዳት ያዳግታል፤ ይቺ ባቄላ ያደገች እንደሆን የሚያሰኝ ነገር ለብዙዎች ሰዎች ምንም አልታየም፤ በጉልበት የማይጨፈለቅ ምንም ነገር የለም ከሚል እምነት ተነሥተው ከሆነ ስሕተቱ እየታየ ነው።

በዚህ ጉዳይ ላይ የእስላሙ ኅብረተሰብ ገና በጠዋቱ በጎሣ የመከፋፈሉን አመራር እንደማይቀበለው በማያጠራጥር መንገድ የገለጠ ይመስለኛል፤ ነገር ግን ብዙ ቤተ ክርስቲያኖች የጎሣ ትግላቸውን ወደቤተ እግዚአብሔር አምጥተው የተከፋፈሉና የተዘጉም ቤተ ክርስቲያኖች ነበሩ፤ ይህ የሚያሳፍር ነው፤ ቤተ መስጊዶች እዚህ ደረጃ አልወረዱም፤ እስልምና በጎሣ አይቀደድም፤ እስላሞች ሁሉ የአላህ ልጆች ናቸው፤ በቤተ መስጊድ የሚሰበሰበው ሁሉ በአላህ ልጅነቱ ነው፤ ስለዚህም በመሀከላቸው ልዩነት የለም፤ ይህ የእስላሞች አቅዋም ሃያ ዓመት ተፈተነ፤ የማይበገር ሆነ፤ ስለዚህም ከጎሣ አስተሳሰብ ወጥቶ ሌላ ቀዳዳ መፈለግ ግዴታ ሆነ፤ አል-ሀበሽ አስፈላጊ የሆነው ለዚህ ነው።

እስቲ ጉዳዩ ለሁላችንም ግልጽ እንዲሆንልን ወደክርስትና ዞረን እንየው፤ የኢትዮጵያ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ከነገ ጀምሮ የሉተራን ቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት ተከተሉ ቢባል አንደኛ የኢትዮጵያ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን (ካለች) ምን ትላለች? ሁለተኛ የኢትዮጵያ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ምን ይላሉ? ሦስተኛ የሻረባትን ቤተ ክርስቲያን ትቶ ወደሌላ ተገልብጦአል፤ የተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን አባል በነበረበት ጊዜ የሠራውን ኃጢአት ዛሬ የሌላ ቤተ ክርስቲያን አባል ሆኖ እውነቱን ገልጦልናል፤ ታምራት ላይኔ የኢትዮጵያ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያንን ከለቀቀ በኋላ የክርስቶስን ጸሐየ ጽድቅነት መረዳቱ ለቤተ ክርስቲያኒቱ የሚያሳፍር ነው፤