onsdag 18. desember 2013

እምዬ ምኒልክ!


(ተመስገን ደሳለኝ)

 ይህንን አጀንዳ ለማቅረብ ያሰብኩት ባለፈው ሳምንት ነበር፤ ይሁንና ‹‹የምስራቅ
ኢትዮጵያ ፖለቲካ 2›› የሚለው ፅሁፌ አንድም ወቅቱ ‹‹የብሔር ብሔረሰቦች ቀን››
ዋዜማ በመሆኑ፣ ሁለትም በይደር የተላለፈው የዚሁ ተከታይ ፅሁፍ መቋጨት ግድ
በማለቱ ነበር፡፡ እናም ‹ቦ ጊዜ ለኩሉ› እንዲል ጠቢቡ፣ የዘገየው አጀንዳችን የዕውቁ
ደቡብ አፍሪካዊው የፀረ አፓርታይድ ትግል መሪ ኒልሰን ማንዴላን ህልፈት ተከትሎ
ዓለም ‹በተሳሳተ የታሪክ ወንዝ› ከመፍሰሱ ጋር ተነፃፅሮ ይቀርብ ዘንድ ገፊ ምክንያት
ሆኗል፡፡ በርግጥ የአጀንዳው ተጠየቅ ማንዴላን አኮስሶ፣ ዳግማዊ አፄ ምኒልክን ማወደስ
አይደለም፤ ንጉሡን ያገለለውን ጨካኝ የታሪክ ፍርድ መሞገት እንጂ፤ በአናቱም ከውስጥ
ጉዳይ ጋር ተያይዞ ዘመን የተሻገረ ቂም የሀገር ባለውለታን ታሪክ ማደብዘዙን መተቸት
ነው፡፡

‹ምኒሊክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ›
 ከአማራና ኦሮሞ ፊውዳል ቤተሰብ እንደተወለደ በህይወት ታሪኩ ዙሪያ የተሰናዱ ድርሳናት የሚያወሱለት ምኒሊክ፣ ንጉሠ ነገሥት አፄ
ዮሐንስ 4ኛ በ1882 ዓ.ም. ከ‹ማሀዲስቶች› (ሱዳናውያን ያቀጣጠሉት የነፃነት ንቅናቄ መጠሪያ ነው) ጋር በተደረገ ጦርነት መሰዋቱን
ተከትሎ ነው ወደ ንግስናው የመጣው፤ ሆኖም ዘውድ ከመጫኑ በፊት፣ በአፄ ዮሐንስ ስር ሆኖ የሸዋና ወሎ አካባቢዎች ‹ንጉሥ› እንደነበረ
ይታወሳል፡፡ በነገራችን ላይ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ አካባቢ የተነሳው ጀርመናዊው ቢስማርክ የተከፋፈለች ሀገሩን ለማዋሀድ
‹‹ነፍጥና መስዋዕትነት›› (With blood and iron) ግድ መሆኑን እንደ አወጀው ሁሉ፣ ተመሳሳዩን መንገድ የመረጠው ምኒልክም፣
ዘግይቶ በአንዳንድ የሀገራችን አካባቢዎች እንደ ‹ወረራ› ያስቆጠረውንና ‹ግዛት ማስፋፋት› ተደርጎ የተወሰደውን ወሰን የማፅናት ዘመቻው
(በዚህ መሀል ‹ባይፈፀሙ ኖሮ› የሚያስብሉ ስህተቶች መሰራታቸው ሳይዘነጋ) በአፄ ዮሐንስ ዘመን መንግስት የተካሄደ እንደነበረ
ይታወቃል፡፡

 የሆነ ሆኖ በአፄ ዮሐንስ የመጨረሻ ዘመን አካባቢ (እ.ኤ.አ. በ1884/5) አውሮፓውያን ቅኝ ገዥዎች አፍሪካን ለመቀራመት ጀርመን
በርሊን ላይ ተሰባስበው ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር፡፡ ይህ ሁኔታ ኢትዮጵያንም ዒላማ ያደረገ ቢሆንም ንጉሠ ነገሥት አፄ ዮሐንስ
ተገቢውን ትኩረት የሰጠው አይመስልም፡፡ በወቅቱ ከአመታት በፊት ከደንከል ባላባቶች አሰብን በመግዛት የእግር መርገጫ ያገኘችው
ጣሊያን ኤርትራን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥራ ወደ ኢትዮጵያ ለመስፋፋት ኃይሏን እያደራጀች የነበረ ከመሆኑም በላይ፣ በአፄውና በምኒልክ
መካከል ቅራኔ እንዲፈጠር ሳትታክት ማሴሯ ለጊዜያዊ ድል እንዳበቃት ይነገራል (ዝርዝር ታሪኩ ሰፊ በመሆኑ አጀንዳችንን እንዳያስረሳን
እዚሁ ገታ እናድርገውና ወደ ጉዳያችን እንመለስ)

 ‹ጂኦ ፖለቲካው› ይህንን ይመስል በነበረበት በዛን ዘመን ‹ዳግማዊ ምኒሊክ› በሚል ስያሜ ዘውድ የደፋው ንጉሥ፣ የረቀቀውን
የጣሊያንን ፖለቲካዊ ሴራ ከመበጣጠስም አልፎ በወርሃ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም. ‹አድዋ› በተባለ የሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል
የተደራጀውንና ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን ሠራዊቷን ድል በመንሳት አለምን ጉድ አሰኝቷል፤ ይህ ሁኔታም ከባርነት በታደገው
በራሱ ህዝብ ዘንድ፡-

‹‹ምኒሊክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ
ግብሩ እንቁላል ነበር ይሄን ጊዜ አበሻ››

በሚል ሲያስወድሰው፣ በገዛ መሬታቸው ነፃነታቸውን ተነጥቀው በቅኝ ግዛት ስር ባደሩ በርካታ አፍሪካውያን ሀገራት ሰማይ ደግሞ
‹‹ኢትዮጵያኒዝም› የሚል መነቃቃት እንዲናኝ መግፍኤ ሊሆን በቃ፤ ዛሬም ድረስ ጥቂት የማይባሉ የምዕራብና መካከለኛው አፍሪካ
ሀገራት ሰንደቅ-አላማቸው ከአረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ቀለም ጋር የተያያዘበት ምክንያትም ይኸው ነው፡፡

እምዬ ምኒሊክ
 ዳግማዊ ምኒሊክ ከሰሜኑና ከመንግስቱ መቀመጫ የራቁትንና የተበታተኑትን ህዝብ ወደ አንድ በማምጣት የሀገሪቱን ግዛት ከቀድሞ
ነገስታት ይዞታ በእጅጉ በሰፋ መልኩ ካፀና በኋላ የተማከለ ስርዓት ለማንበርና ሀገር ለማዘመን መሰረታዊ የሆኑ አስተዋፅኦዎች አድርጓል፤
የአጼ ምኒልክ ሀወልት
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar