November 2, 2013
አባ ግርማ ከበደ ቤተ ክርስቲያንን ከነ ሕዝቧ ለመሸጥ የተዋዋሉበትን የክፍያ ቼክ ለመረከብ ይመስላል ለንደንን በስውር በመልቀቅ በዛሬው ዕለት (31/10/2013) አዲስ አበባ መግባታቸው ተረጋገጠ።
ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በስደት ሃገር በስደተኛው ሕዝብ ከተመሠረተች 40 ዓመታትን ያስቆጠረች ሲሆን ከሁሉም በላይ ግን በተለይ ባለፉት 5 ዓመታት አባላቷ ባደረጉት ከፍተኛ ጥረትና ርብርቦሽ ገንዘብና ጉልበታቸውን አስተባብረው ከፍተኛ ዋጋ ያለው ህንፃ ቤተ ክርስቲያን ከነ መኖሪያ ቤቱ (Vicarage) በመግዛት ቤተ ክርስቲያኗ በእንግሊዝ ሃገር ለትውልድ የሚተላለፍ የህንፃ ቤተ ክርስቲያን ቅርስ ባለቤት ለመሆን አብቅተዋታል።
ይህንን ህንፃ ቤተ ክርስቲያንና የመኖሪያ ቤቱ (Vicarage) ለመግዛት የሚያስችል £1.700.000 (አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሺህ ፓውንድ) ወይም ደግሞ በኢትዮጵያ ብር ሲሰላ 51 ሚሊዮን ብር ለማዋጣት የተቻለው የቤተ ክርስቲያኑ አባላት፤ ደምወዝተኛው ከደምወዙ ቀንሶና ከልጆቹ አፍ ነጥቆ፤ እንዲሁም ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚረዳው ዘመዱ ጋር አብቃቅቶ ሲሆን ስራ የሌለውም ሆነ ለመሥራት አቅም የለለው የአካል ጉዳተኛ ደግሞ ከመንግሥት ከሚሰጠው ድጎማ ላይ ከዕለት ጉርሱ በመቀነስ፤ ተጧሪውም ከጡረታ አበሉ በመቀነስ ወገቡን አስሮ ለሃይማኖቴና ለቤተ ክርስቲያኔ ካልሆነ ለምን ሊሆን ነው በማለት በመለገሱና ከልቡ በመሥራቱ ነው።
በመጀመሪያ የግዢ ውል ሲፈረምና የቤተ ክርስቲያኑ Leasehold ዝውውር ሲደረግ በUK የመሬትና የንብረት ይዞታ ህግ መሠረት ንብረቱ ሊያዝ ከሚችልባቸው ሁለት መንገዶች አንዱ ከ1-4 በሚደርስ ሰው በመሆኑ ሁለት ካህናትና ሁለት ምእመናን እንዲሆኑ ተደረገ። እነሱም አባ ግርማ ከበደ፤ ቄስ ዳዊት አበበ፤ ወ/ት ትዕግሥት ታደስ እና አቶ ታዬ ኃይሉ ይባላሉ።
የቤተ ክርስቲያኑ ግዢ ዕዳው ተከፍሎ እንዳለቀም እነዚሁ አራት ሰዎች Free hold ሰነድ ላይ ንብረቱን በስማቸው በአደራ ይዘውት እንዲቀጥሉ ተደረገ፡፡ ዕዳው ተከፍሎ ባለቀ ማግሥት ግን አባ ግርማ ከበደ በውስጥ መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ ረቂቁ ምክንያት ስማቸው ከቤተ ክርስቲያን ንብረት ባለቤትነት መዝገብ ላይ የሚነሳበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላላ በሚል ስጋት ሕዝቡ በረቂቁ ላይ እንዳይወያይና እንዳይወስን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሁከትና ብጥብጥ እንዲነሳ አስደረጉ።
ይህ ቪዲዮ በሎንደን የኢትዮጵያ ኢምባሲ አደራጅቶ ያሰማራቸው ጋጠወጦች ቤተክርስቲያኗን የመሰረቱትን አዛውንቶች ሲዘልፉና ሲያዋክቡ ያሳያል፣
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar