ኤፍሬም ማዴቦ
የኢትዮጵያ ህዝብና እናስተዳድረዋለን የሚሉት አምባገነን ገዢዎቹ ተስማምተዉና አንዱ ሌላዉን አክብሮ የኖረበት አንድም የታሪክ
አጋጣሚ የለም። የእስከዛሬዉ ታሪካችን ምዕራፍ በጥቅሉ ሲታይ ታሪካችን የሚቋጨዉ ህዝብ ተረገጠ፤ ተጋዘ፤ ገዢዎች ደግሞ
ረገጡ፤ገዙ፤ አሰሩ፤ አጋዙ እየተባለ ነዉ። አዎ! የኢትዮጵያ ህዝብ እስከዛሬ ባለዉ ታሪኩ ተግዟል፤ ተረግጧል፤ ተንቋል፤ ተንቋሿል።
የዘንድሮዉ በተለይ ባለፉት ሁለትና ሦስት ሳምንታት እየደረሰብን ያለዉ ብሄራዊ ዉርደትና ንቀት ግን ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ
ልዩ ከልዩም ልዩ ነዉ። በቀዳማዊ ኃ/ሥላሤ ዘመን የኢትዮጵያ ህዝብ ልክ እንደዛሬዉ ሰብዓዊ መብቱ ተረግጧል፤ ፍትህ ተነፍጓል፤
ነጻነቱን ተገፍፏል፤ ሆኖም አገር ዉስጥም ከአገር ዉጭም ፈላጊና ባለቤት አንደሌለዉ የቤት ዉስጥ እንስሳ የወገንም የባዳም እጅ
አልተረባረበበትም። አንገፍግፎን አንፈልግም በቃ ብለን ያስወገድነዉ የቀዳማዊ ኃ/ሥላሤ ስርዐት በስልጣን ላይ በነበረበት ግዜ
“ኢትዮጵያ” የሚለዉ ስምና “ኢትዮጵያዊነት” አገር ዉስጥም ሆነ አዉሮፓ፤ አሜሪካና አፍሪካ ዉስጥ እጅግ በጣም የተወደደና የተከበረ
ስም ነበር። ዛሬ ወያኔ ነጻ አወጣኋችሁ፤ እኩልነት አመጣሁላችሁ እያለ በሚሰብክበት ዘመን ግን የኢትዮጵያ ሀዝብ አገር ዉስጥም
በዉጭ አገሮችም ባለቤት አንደሌለዉ ፈረስ ማንም የሚጋልብበት ፈላጊ እንደሌለዉ ዕቃ ያገኘ ሁሉ እንዳሰኘዉ እጁን የሚያሳርፍበት
የተናቀ ሀዝብ ሆኗል። ለመሆኑ ለምንድነዉ ኢትዮጵያዊነት እንደዚህ እንደ ተራ ዕቃ የቀለለዉ? ኢትዮጵያዉያንስ ለምንድነዉ
በየሄዱበት እንዲህ አይነት ዉርደትና ስቃይ የሚደርስባቸዉ? መልሱ ቀላል ነዉ። “ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ” ወይም
“ባለቤቱ ያቀለለዉን አሞሌ ባለዕዳ አይቀበለዉም” ነዉ።
የወያኔ አገዛዝ እኛ ኢትዮጵያዉያን “ኢትዮጵያዊነት” እያልን ስለምንሳሳለትና ስለምንከባከብለት ትልቅና ክቡር ሀሳብ በፍጹም ግድ
የለዉም። እንዲያዉም ወያኔ ሽንጡን ገትሮ ከሚታገላቸዉ ዋና ዋና ብሄራዊ እሴቶቻችን ዉስጥ “ኢትዮጵያዊነት” የመጀመሪያዉ ነዉ።
ስለዚህም ነዉ ባለፉት ሃያ ሁለት አመታት በግልጽ እንደተመለከትነዉ “ኢትዮጵያዊነት” ብለዉ የተጣሩ፤የጮሁ፤ ህዝብን ያስተማሩና
የታገሉ ግለሰቦች በወያኔ እየተለቀሙ የታሰሩትና የተገደሉት። ከአገር ዉጭም ቢሆን በየዉጭ አገሩ የሚገኙት የወያኔ ኤምባሲዎች
ኢትዮጵያዉያን ከአገራቸዉ ዉጭ ማግኘት የሚገባቸዉን የዜግነት አገልግሎት የሚሰጡት ዜግነታቸዉን እያዩ ሳይሆን ቦንድ የገዛ
ያልገዛ፤ “ልማታዊዉን መንግስት” የደገፈ ያልደገፈ እያሉ ወይም “የወርቃማዉ ዘር” አባልነቱን እያጣሩ ነዉ። እነዚህንና ሌሎችም
እነዚህን የመሳሰሉ ሰንካላ የወያኔ መስፈርቶች ያላሟሉ ኢትዮጵያዉያን አገር ዉስጥም ከአገር ዉጭም ወያኔ በዜግነት ሳይሆነ
በጠላትነት የሚመለከታቸዉ ሁለተኛና ሦስተኛ ደረጃ ዜጎች ናቸዉ። ዛሬ ከአፍሪካ፤ ከኢሲያና ከላቲን አሜሪካ አገሮች ስራ ፍለጋ ሳዑዲ
አረቢያ ከሄዱ ዜጎች ዉስጥ እንደ ኢትዮጵዉያን እጁንና እግሩን ታስሮ የተገረፈ፤ እንደሴቶቻችን በሳዑዲ ጎረምሶች የተደፈረና እንደ
ኢትዮጵዉያን በየአደባባዩ የተገደለ የሌላ አገር ዜጋ የለም። ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ የሚገኙ የሌሎች አገሮች ኤምባሲዎች የዜጎቻቸዉ
መብት በሳዑዲ መንግስትና ህዝብ ሲደፈር ለምን ብለዉ ይጠይቃሉ ወይም ለዜጎቻቸዉ ግዜያዊ መጠለያ፤ የህክምና እርዳታና የህግ
ሽፋን ይሰጣሉ እንጂ ኤምባሲያቸዉ በራፍ ላይ “ዝግ ነዉ” የሚል ጽሁፍ አይለጥፉም።
የወያኔ ኤምባሲ ግን ከስረ መሠረቱ የተቋቋመዉ የወያኔን የራሱን እንጂ የኢትዮጵያን ህዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ ስላልሆነ ይህንን
የሌሎች አገሮች ኤምባሲዎች ለዜጎቻቸዉ የሚያደርጉትን ጥበቃና እንክብካቤ ለወገኖቹ ለማድረግ አልታደለም፤ ፍላጎቱም የለዉም።
ይህንን ቅሌትና ዉርደት ደግሞ ባለፉት ሁለትና ሦስት ሳምንታት በግልጽ ተመልክተናል። ጂዳና ሪያድ ዉስጥ በዜጎቻችን ላይ
የሚደርሰዉን መከራና በደል ተቃዉመዉ ሠልፍ የወጡ ኢትዮጵያዉያን በሳዑዲ ፖሊሶች ታድነዉ እንደታሰሩ ሁሉ አዲስ አበባ
ዉስጥም በወንድሞቻችንና እህቶቻች ላይ እንዴት እንዲህ አይነት በደል ይፈፀማል ብለዉ ሳዑዲ ኤምባሲ ፊት ለፊት ሠላማዊ ሠልፍ
የወጡ ኢትዮጵያዉያን በአረመኔዎቹ የወያኔ ፖሊሶች ታድነዉ ታስረዋል፤ተደብድበዋል። አዎ! ኢትዮጵያዉያን ሳዑዲ ዉስጥም
ኢትዮጵያ ዉስጥም ለምን የሳዑዲን መንግስት ተቃወማችሁ ተብለዉ በሁለቱም አገር ፖሊሶች እየታደኑ ታስረዋል ተደብድበዋል።
ከወያኔና ከጥቂት ሆድ አምላኪ ደጋፊዎቹ ዉጭ በአገር ዉስጥና በመላዉ ዓለም የሚገኘዉ ኢትዮጵያዊ በአንድ አላማ ዙሪያ
የተሰባሰበበትና አንድ ሳምንት ሙሉ አንድ ቃል በአንድ ትንፋሽ የተነፈሰበት ግዜ ቢኖር ወርሃ ህዳር 2006 የመጀመረያዉ ነዉ ማለት
ይቻላል። የአንድ አገር ህዝብ በአንድ አላማ ስር ሲሰባሰብና በአንድነት ሲቆም ከማንም ከምንም በላይ በዚህ አንድነት መጠቀምም
መደሰትም ያለበት መንግስት ነዉ። ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ የወያኔ አገዛዝ ግን ዕቅዱና ስራዉ ሁሉ የኢትዮጵያን ህዝብ ማስጨነቅና
ማበሳጨት ነዉ እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ በሚሰራዉ ስራ ተደስቶ አያዉቅም፤ ለወደፊትም የሚደሰት አይመስልም። ከሰሞኑ ሳዑዲ
አረቢያ ዉስጥ በኢትዮጵያዉያን ወገኖቻችን ላይ የደረሰዉ ልክ የሌለዉ ስቃይና መከራ መላዉን የኢትዮጵያ ህዝብ ቀፎዉ እንደተነካ
ንብ ከዳር ዳር ሲያስቆጣ ወያኔና ሞራለ ብልሹ ሹማምንቶቹ ግን ከዚህ ወገኖቻችንን በባዕድ አገር ለከፍተኛ ጥቃት ካጋለጠና ብሄራዊ
ዉርደት ካከናነበን ክስተት ትርፍ ለማግኘት የፖለቲካ ቁማር እየተጫወቱ ነዉ። ኢትዮጵያዉያን ሳዑዲ ዉስጥ በአሰሪዎቻቸዉ፤
በመንደር ዉስጥ ጎረምሶችና በፖሊስ ከፍተኛ ድብደባ፤ እንግልትና ዉርደት ሲደርስባቸዉ ኤምባሲዉ በራፍ ላይ “ኤምባሲዉ ዝግ ነዉ”
የሚል ጽሁፍ በመለጠፍ ይበላችሁ እያለ አፉን ዘግቶ የተመለከተዉ የወያኔ አገዛዝ ዛሬ የወገን አሳቢና ተቆርቋሪ ለመመሰል የጭቃ
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar