søndag 10. november 2013

ጎጅ ባህሎቻችን


በተክሉ አባተ
ባህል ብዙ ትርጉም ይኖረዋል:: ለእኔ ግን የአንድ ኅብረተሰብ የአስተሳሰብ: የጠባይና: የባህርይ መገለጫ ወይም ምልክት ነው::
በተፈጥሮ (በዘር ውርስ) የማይገኝና በሰው ብርቱ ጥረት የሚፈጠር ስለሆነ እያንዳንዱ አገር የራሱ የሆነ ልዩ ባህል አለው::
ለልጅ ልጅም በትምህርትና በተሞክሮ ያስተላልፋል:: በጊዜ ብዛትና በተለያዩ ብሄራዊ: ክልላዊና: ዓለም አቀፋዊ ጫናዎች
የተነሳ ባህል ሊከለስ ሊዳብር ሊለወጥም ይችላል:: ያም ቢሆን ግን አገራት በባህላቸው ልዩ የሆኑ ናቸው (የዓለም ህዝቦች
የሚጋሩትም ባህል እንዳለ ሳንረሳ):: በአጠቃላይ ባህል የኅብረተሰብን ምንነትንና ማንነትን ገላጭ ነው ቢባል የተጋነነ
አይሆንም::
ዳሩ ግን ሁሉም ባህሎች ጠቃሚ ወይም ገንቢ ላይሆኑ ይችላሉ:: እንዲያውም በባህል ስም ‘ገዳይ’ የሆኑ አስተሳሰቦችና
ምግባራት ሊስተዋሉ ይችላሉ አሉም:: ለግለሰብ እድገት ጤናና ሰላም እንዲሁም ለአገር መሻሻል ልዩ አስተዋጽዖ የሚያደርጉ
ባህሎች እንዳሉ ሁሉ ባለንበት እንድንሄድ እንዲያውም ባላንስ እንዳጣ መኪና ወደኋላ እንድንሸራተት የሚያደርጉ ባህሎችም
አሉ:: እነዚህን ወደፊት እንድንሄድ የማያግዙ ወይም ወደኋላ የሚጎትቱንን ጎጅ ባህሎች ብያቸዋለሁ:: ቆም ብለን ማሰብና
መገንዘብ መመርመር ከፈለግንና ከቻልን ጎጅ ባህሎችን መለየት እንችላለን:: እንዲህ ማድረግ ከቻልን ደግሞ ጠቃሚ ባህል
ግንባታ ላይ እናተኩራለን:: ለግል ህይወታችንና ለአገራችንም ጠቀም ያለ ለውጥ ባጭር ጊዜ ማምጣት እንችላለን:: በመሆኑም
በዚህና በቀጣይ ጽሁፎች ለኛ ለኢትዮጵያውያን ጎጅ ናቸው ብዬ የማስባቸውን የምንነታችንንና የማንነታችንን መገለጫ የሆኑ
ባህሎቻችንን ለመለየት እሞክራለሁ::
ጎጅ ባህል ስል ግን ሁሌ አሰልቺ በሆነ መልኩ በሚዲያ የሚለፈፉትን አይነት ማለቴ አይደለም:: ለእኔ ጎጅ ባህል ግግ
ማውጣትን: እንጥል መቁረጥን: የሴት ልጅ ግርዛትን: ያለእድሜ ጋብቻን: ያለአቅም ድግስን: እጅ ሳይታጠቡ መመገብን:
ወዘተረፈ አይመለከትም:: ምንም እንኳን እነዚህ ተግባራት ጎጅነታቸው የማያነጋግር ቢሆንም ለእኔ ግን በአሁኑ ጊዜ አሳሳቢ
ሆነው አይታዩኝም:: ትኩረቴ የሚሆነው አስተሳሰባችንን ጠባያችንንና ምግባራችንን ማእከል ባደረጉ ደካማ ባህሎቻችን ላይ
ነው:: እነዚህ ባህሎች ላለፉት በርካታ ዓሥርት ዓመታት ባለንበት እንድንረግጥ እንዲሁም በአንዳንድ የህይወት ዘርፎች
ወደኋላ በፍጥነት እንድንጓዝ ያደረጉን ናቸው ብዬ አምናለሁ:: ለብሄራዊ ድቀታችን ግንባር ቀደም ተጠሪውና ተጠያቂው
መንግስት ቢሆንም እንደህጻን ልጅ ተንከባክበን የያዝናቸው አንዳንድ ባህሎቻችንም ቀላል ያልሆነ አስተዋጽዖ አድርገዋል::
በግል ህይወት በቤተሰብ በጎረቤት በጓደኛ በመስሪያ ቤትና በብሄራዊ ደረጃ እንቅስቃሴያችን ጥራትና ዋጋ እንዳይኖረው
የሚያደርጉ ብዙ ጎታቾች አሉን::
በተከታታይ የምዘረዝራቸው ባህሎች በተወሰነ መልኩ ደካማ ጎኖች ተብለውም ለፈረጁ ይችላሉ:: ለእኔ ግን ደካማ ጎን
የግለሰብን ችግር አመላካች ስለሚሆን ቃሉን በዚህ ጽሁፍ እምብዛም አልጠቀመውም:: ጽሁፌን በደንብ እንድትረዱልኝ ግን
በቅድሚያ ማሳሰቢያዎቼን ልጥቀስ:: አንድ: በጅምላ የኢትዮጵያ ባህል ገዳይ ወይም ጎጅ ነው እያልኩ አይደለም:: ለቁጥር
የሚያዳግቱ የትም አገር የማይገኙ ወርቅ ባህሎች ሞልተውናል:: ለመሻሻል እንዲረዳን በጎጅዎች ላይ ብቻ ማተኮሬ እንጅ::
ሁለት: ቀጥዬ የምጠቅሳቸው ጎጅ ባህሎች ሁሉም ሰው ጋር አሉ የሚባል ባይሆንም ብዙዎቻችን ግን የምንጋራቸው
ይመስላሉ:: ለማንኛውም እያንዳንዱ አንባቢ የየትኛው ጎጅ ባህል ሰለባ እንደሆነ ራሱ ይመርምር:: ሥስት: ይህ ጽሁፍ
ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ በተሰበሰበ መረጃና ማስረጃ ላይ የተመረኮዘ ሳይሆን ከማህበራዊ ሚዲያዎች የተመለከትኩትንና

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar