torsdag 31. oktober 2013

በወያኔ ሎሌነት ከመማቀቅ አንድ ቀን ነፃ ሆኖ መኖር ይሻላል October 31, 2013 | Filed underG7 Editorial,Slider Post | Posted by admin


በወያኔ ግፈኛ ስርአት መከራቸውን ከሚያዩ ዜጎች ውስጥ ራሱ ሥርአቱ ለራሱ መገልገያ የሰበሰባቸውና ያሰማራቸው ዜጎች ይገኙበታል። ከእጅ ወደ አፍ እንኳን ለማትሆን ደመዎዝ በሰራዊቱ ውስጥ በተራ ወታደርነትና በበታች ሹማምንት የሲኦልና የጉስቅልና ኖሮ እንደሚኖሩ እናውቃለን።
በየዞኑና በየወረዳው በካድሬነት ወያኔ ለገላጋይነት ያሰማራቸው ሰራተኞችና የድርጅቱ አባሎች ከህዝቡ የጥላቻ ሰለባነት ባልተናነሰ በኑሮአቸው ለራሳቸውም ለቤተሰቦቻቸውም ሳያልፍላቸው እንደሚኖሩ እናውቃለን።
ይልቁንስ የወያኔው የአመራር ጉጅሌ ነገ የት እንደሚያደርሳቸው በማያውቁት ጨለማ ውስጥ ነው የሚዳክሩት ሚስጥርና የዳጎሰ ጥቅም ከነሱ ዘንድ አይደርስም። በቀድሞ ጊዜ የነበሩት የባላባት ሎሌዎች እንኳን ክብር አላቸው።
በዚህ ላይ ሁሉም አስተማማኝ ሎሌ መሆኑን ወያኔ ለማረጋገጫ የሚጠቀምበት ግምገማ አለ። የወያኔ ግምገማ የበታች አባላትና ደጋፊዎቹን በማስፈራራት ያላቋረጠ ድጋፍ እንዲሰጡት የሚያደርግበት በመሰረቱ ከውሻ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የማይለይ ተቋም ነው። የትምህርት እድል የስራ እድገትና የደመወዝ ጭማሪ የወያኔው ጉጅሌ የባርነት መደለያዎች ናቸው።
ግንቦት 7 ከጥቂት ከመንገዳቸው እያወጡ ህዝብ ከሚያሰቃዩት የወያኔ ታዛዥ ሎሌዎች በቀር የሀገርና የወገን ጠላት ናቸው ብሎ አያምንም። ትግላችን ለነሱም ነጻነት ነው። እነዚህ ወገኖቻችን ባገኙት አጋጣሚና እድል ሁሉ ትግሉን ያግዛሉ ብሎም ያምናል። የሚያግዙም አሉ። እርግጥ ነው ባሽከርነት ኑሮ የተንገፈገፉ የሰራዊቱ አባላትና ለህሊናቸው ክብር ያላቸው በርካታ የስርአቱ አገልጋዮች ትግላችንን እየተቀላቀሉ ነው።
ግንቦት 7 ንቅናቄ ዛሬም እንደሁሌው ለነዚህ ወገኖች ኑ ተቀላቀሉን የሚል ጥሪውን ያቀርባል። ሁላችንም ከነክብራችን ሆነን ሰዎችን ሳይሆን ውዲቱን ሀገራችንና ህዝባችንን በፈቃደኝነት በነጻነት የምናገለግልበት ጊዜ እየቀረበ ነው፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

1 kommentar:

  1. የመድኃኒት ንግድ ሥራዬን ለማስፋፋት በተጠቀምኩበት ብድር ለመርዳት ሚስተር ቤንጃን ከሚያስፈልጓቸው በላይ አልፈዋል ፡፡
    እነሱ ለመስራት ወዳጃዊ ፣ ባለሙያ እና ፍጹም ዕንቁዎች ነበሩ ፡፡ እኔ ለማነጋገር ብድር የሚፈልግን ማንኛውንም ሰው እመክራለሁ ፡፡ Lfdsloans@outlook.com.WhatsApp ... +19893943740.

    SvarSlett