lørdag 5. oktober 2013

ወያኔን ለማስወገድ አስገዳጅ የትግል ስልት ወሳኝ ነው!!!
ከለምለም አንዳርጌ(ኖርዌይ)
ላለፉት ሁለት አስርተ አመታት ኢትዮጲያና ሕዝቦ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ ይህ ነው
የማይባል ግፍና ሰቆቃ ሲፈጽም የኖረው የዘረኛው የወያኔ ስርዓት የእድሜ ዘመኑ ማብቂያ
ጠርዝ ላይ ለመሆኑ ኢትዮጲያን ያህል ሃገርና ህዝብ ከሚመራ ስርዓት የማይጠበቁ የማፍያ
ተግባራቱ ስርዓቱ ያለበት የዝቅጠት ደረጃ ጠቋሚዎች ናችው፡፡ በእድሜ ዘመን መጀመሪያ በስም
እንጂ በተግባር ዴሞክራሲን የማያቀው የአንድ ጎጥ ቡድን ለይስሙላ ባስቀመጠው ህገ-መንግስት
የተካተቱትን የዜጎችን መብት በመሻር ሃገሪቱን የምድር ሲኦል አርገዋታል፡፡ በሃገሪቱ ህገ-
መንግስት መሰረት መብታቸውን አውቀው የተቋቋሙ የሞያ ማህበራትም ሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶች
በራሳቸውም ሆነ በስርዓቱ ተጽእኖ ይህ ነው የማይባል ተግባራት ሳይከውኑ በዘረኛው ስርዓት
እየተኮረኮሙ ይፈርሳሉ አልይም በሞኖፖል በተያዘው የፍትህ ስርዓት ተወንጅለው በግፍ በእስር
ይማቅቃሉ፡፡
ከአመታት በኋላ ፍርሃታቸውን አሸንፈው የወያኔ መናጆ መሆን ይበቃናል ብለው ህገ-
መንግስቱ የሚፈቅድላቸውን መብት ለመጠቀም ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ ወያኔን
እምቢኝ እያሉ ያሉት በአገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉት ጥቂት የፖለቲካ
ድርጅቶች መብታቸውን ተጠቅመው የሚያደርጉት የሰላማዊ ትግል መርህ የዚህን ዘረኛ
ስርዓት ማንነት ፍንትው አድርጎ ያሳየን አጋጣሚ ነው፡፡ ምንም እንኳን የኢትዮጲያ ሕዝብ
ስለወያኔ ማንነትና ምንነት የጠለቅ ግንዛቤ ቢኖረውም በዚህ ደረጃ በወረደና በዘቀጠ ማፊያ
ቡድን እንደምንመራ ማመን በእጅጉ ይክብዳል፡፡
አንድ የፖለቲካ ድርጅት እንደ ድርጅት ምልኡ የሚሆነው የተነሳለትን አላማና እቅድ
እንዲሁም የሕዝብን መሰረታዊ የመብት ጥያቄዎች ተግባራዊ ምላሽ እንዲያገኙ በፅናት
መታገል ሲችል ነው፡፡ እንደ ወያኔ ያለ አምባገነን ስርዓት አፍኖ ለያዘው የሕዝብ የመብት
ጥያቄ ምላሽ የሚሰጠው በተፅኖ እንጂ በችሮታ አይደለም፡፡ ለሚጠየቀው ህገ መንግስታዊ
የሕዝብ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጥ አይጠበቅም አምባገነን ነውና፡፡ ስለሆነም መብቱን
የሚያስከብር ለምን?! እንዴት?! በቃኝ፣! እምቢ! የሚል የሕዝብ አደረጃጀት እንዲኖር
የፖለቲካ ድርጅቶች በተገቢው ደረጃ ሕዝብን ማደራጀትና መርሆና፣ እቅዳቸውን ማስረፅ
እንዲሁም ለለውጥ የተዘጋጀ ትግሉን ከዳር ሊያደርስ የሚችል ፍርሃቱን የሰበረ የህብረተሰብ
ሃይል ሊገነቡ ግድ ይላቸዋል፡፡

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar