October 17, 2013
ገለታው ዘለቀ
በዚህች ኣጭር ጽሁፍ ውስጥ ኤርትራን ለነጻነት ትግሉ በመጠቀሙ ዙሪያ በሚነሱ ክርክሮች ላይ የግል ኣስተያየት ለማከል እፈልጋለሁ። እንደሚታወቀው ኣመጸኛው ህወሃት ያስመረራቸው እና ለለውጥ የሚታገሉ ሃይሎች በሰላማዊ መንገድ በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ ማምጣት ዘበት ነው ብለው ኣምርረው በማመናቸው ነፍጥ ማንገባቸው ከታወቀ ውሎ ኣድሯል።
እነዚህ ሃይሎች ኤርትራን እንጠቀማለን ኤርትራ የኢትዮጵያን ህዝብ ትግል ለማገዝ ከፍተኛ ፍላጎት ኣሳይታለች እያሉ ነው። ታዲያ ይሁን እንጂ ኣንዳንድ ዜጎችና የተደራጁ ሃይላት በዚህ ላይ ስጋት ኣለን በማለታቸው ሁለት ክንፍ ተፈጥሯል ማለት ይቻላል።
በመጀመሪያ እነ
ዚህ “በኤርትራ በኩል የሚደረግ እንቃስቃሴ ለውጥ ኣያመጣም” የሚሉ ወገኖች ከሚያነሷቸው ጉዳዩች መካከል ቀዳሚው ነገር ሻእቢያ በኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራት የሆኑ ድርጅቶች እንዲያብቡና ኢትዮጵያ ዴሞክራት ኣገር እንድትሆን የሚፈልግ ልብ ከየት ሊያመጣ ይችላል? ዛሬ ኤርትራና ኢትዮጵያ መጣላታቸው ብቻውን ኤርትራ የኢትዮጵያን እውነተኛ ተቃዋሚዎች ዴሞክራትና የኣንድነት ሃይሎች ለመደገፍ ሊያበቃት ይችላል ወይ? ኤርትራ ወያኔን የምር ከጠላችም ልትደግፍ የምትችለው በብሄር ላይ የተመሰረቱትን የመገንጠል ኣላማ ያላቸውን እንጂ የኢትዮጵያን ኣንድነት የሚፈልጉትን ወይም ለዚህ የሚታገሉትን ኣይሆንም:: ደሞ ሁሉም ይቅርና ኣሁን ያለው የኤርትራ ሁኔት ተቀይሩዋል ከተባለ እየታገልን እያለ መሃል ላይ ድንገት ሃሳቧን ብትቀይርስ? ወይም ከወያኔ ጋር ቢታረቁስ? በትግል ላይ እያለን ሳንዱች መሆናችን ኣይደለም ወይ? ሪስኩ በዛ:: ሌላው ቀርቶ ኣሁን በቅርቡ እንኳን የኤርትራው ፕሬዚዳንት ከኢትዮጵያ መብራት ልንገዛ እንችላለን ኣሉ ሲባል በቃ ታረቁ ማለት ነው? ብሎ የደነገጠ ኣለ። እነዚህን የመሳሰሉ ስጋቶች ባንድ ጎራ ሰፍሯል።
በሌላ ጎራ ያለው ወገን ደግሞ መሬት ላይ ያለው ነገር ተቀይሯል:: ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ ኣይታደርም:: ሪስክ መውሰድ ኣለብን:: ኤርትራ እኛን ልትደግፍ የሚያስችላት መሰረታዊ ነገር ብዙ ኣለ። ከነዚህም ውስጥ ለራሷ ሪጂናል ሰኪዩሪቲ የኢትዮጵያ ህልውና ወሳኝ ነው። የኣሰብ ጉዳይም ቢሆን ወያኔ በፈጠረው ችግር ምክንያት የግመል ማጠጫ ነው የሆነው። ከዚህም በላይ እነዚህ ህዝቦች ከጊዜው ፖለቲካ በላይ የሆነ ትስስር ያላቸው ህዝቦች በመሆናቸው ኢትዮጵያ የኤርትራን ፈጽሞ መጥፋት ኤርትራ የኢትዮጵያን ፈጽሞ መጥፋት የሚመኛኙ ኣይደሉም። ሌላው ደግሞ የኛ የተቃዋሚዎች በዚህ ኣካባቢ መኖር ከወያኔ መጥፋት በሁዋላ ለሚኖረው የኢትዮጵያና የኤርትራ ግንኙነት ከፍተኛ የሆነ ኣዎንታዊ ሚና ይጫወታል የሚሉት ዋና ዋናዎቹ መከራከሪያዎች ናቸው።
እነዚህ ወገኖች ከሌላው ጎራ የሚቀርብባቸውን ፍርሃትም የሚከላከሉበት ኣንዱ ነገር ደሞ እስከዛሬ ድረስ በኤርትራ በኩል የነበሩ ተቃዋሚዎች ፍሬ ያላፈሩት በራሳቸው ችግር እንጂ በኤርትራ በኩል ባለ ችግር ኣይደለም ይላሉ። ኤርትራ ተቃዋሚዎችን እያስጠጋች እዚያው እንዲያረጁ ታደርጋለች እንጂ ለውጤት እንድንበቃ ኣትፈልግም የሚሉትን ወገኖች ለማሳመን።
ኣስተያየት
በሃገራችን ውስጥ ሃይማኖታዊ ጽንፈኝነት ኣለ ብየ ኣላምንም። በርግጥ ግን
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar