fredag 4. oktober 2013

ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ አላደርግም አለች


ኢ.ኤም.ኤፍ – ከአፍሪካ ለአለም ዋንጫ ካለፉት አስር አገሮች መካከል፤ ኢትዮጵያ እና ግብጽ ይገኙበታል። እሁድ ኦክቶበር 13 ኢትዮጵያ እና ናይጄርያ – ኦክቶበር 19 ግብጽ ከጋና ጋር ይጫወታሉ። ኢትዮጵያ ከናይጄሪያ ጋር ለምታደርገው ግጥሚያ ከወዲሁ ዝግጅት ላይ መሆናቸው ባለፈ፤ ከሌላ አገር ጋር የወዳጅነት ጨዋታ አላደረጉም። ሱፐር ስፖርት ድረ ገጽ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽንን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ ግን፤ ግብጽ ለኢትዮጵያ ያቀረበችውን የወዳጅነት ጨዋታ ውድቅ አድርጋዋለች።
Ethiopian-National-Team
ፌዴሬሽኑ በዚህ ጉዳይ ምላሽ ሲሰጥ፤ “አዎ ከግብጽ በኩል የወዳጅነት ጥያቄ ቀርቦልናል። ሆኖም በግብጽ አገር መረጋጋት የለም። በ እንዲህ አይነቱ አለመረጋጋት በሌለበት አገር ጨዋታ ማድረግ አንችልም። ለነገሩ ከዚህ በፊት እኛ የወዳጅነት ጨዋታ እንዲያደርጉ ጠይቀናቸው ፈቃደኛ አልሆኑም። የአሁኑ የኛ ውሳኔ ለተጨዋቾቻችን ደህንነት ሲባል የተደረገ እንጂ፤ ግብጽን ካለማክበር የመጣ አይደለም።” ብለዋል።
በ እርግጥም በግብጽ አገር ባለው አለመረጋጋት ምክንያት ኦክቶበር 19 ቀን ከጋና ጋር የሚደረገው ጨዋታ በዝግ ስቴዲየም ውስጥ እንዲሆን በፊፋ በኩል ተወስኗል። የት ሊሆን እንደሚችል ገና አልታወቀም። ቀኑ ሲደርስ ደግሞ ተመልካች በሌለበት ይጋጠማሉ ማለት ነው። ለጋና ተጫዋቾች ደህንነት ሲባል እስካሁን የትኛው ስቴዲየም እንደሚጫወቱ ይፋ አልተደረገም።
EMF

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar