mandag 16. september 2013
መውጫ አብጅቶ መግቢያ የከሇከሇን አሰዲጁ ማን ነው?
ከግርማ ሠይፈ ማሩ
ሀገራቸን ኢትዮጵያን ሇቀው ሇስዯት የተዘጋጁት ዜጎችን ቁጥር መገመት አስቸጋሪ ቢሆንም በአንዴ ወይም በላሊ ምክንያት
መውጣት የቻለት ግን ሊሇመመሇስ ብዙ ምክንያቶች አለዋቸው፡፡ ይህን የዜጎች (በተሇይ የተማሩና ወጣቶች) ስዯት ሀገራችንን
ከፍተኛ ዋጋ እያስከፇሊት እንዯሆነ እና ወዯፉትም ከፍተኛ ጉዲት እንዯሚያስከትሌ ሇማወቅ ሉቅ መሆን የሚያስፇሌግ
አይመሰሇኝም፡፡ አሜሪካኖች በዱቪ እንኳን ሉወስደት የሚፇሌጉት ፉዯሌ ቆጥሮ አንዴ ነገር ሉያዯርግሊቸው የሚችሇውን
እንዯሆነ እናውቃሇን፡፡ ሇዜጎች ስዯት ምክንያቱ መንግሰት እንዯሚሇው ህገወጥ ዯሊልች አይዯለም ይሌቁንም የመንግሰት
የተሇያየ ፖሉሲ ውጤቶች ናቸው ብዬ ማሳየት ፇሇኩኝ እና ይህን ፅሁፍ ጀመርኩ፡፡
የስራ ዋስትና በሀገራችን የተረጋገጠ አይዯሇም፡፡ ቀዯም ሲሌ የመንግሰት ስራ ያሌተመቸው ኢትዮጵያዊ መንግስታዊ ያሌሆነ
ዴርጅት ገብቶ በሞያው ማገሌገሌ አንዴ የሚታይ ጠባብ አማራጭ ነበር፡፡ ይህ ጠባብ አማራጭ እንዯሚታወቀው ከ1997
ምርጫ በኋሊ ይህ “የኪራይ ሰብሳቢዎች ምሽግ እንዱፇርስ” በሚሌ በወጣ አዋጅ ጠባብ አማራጭነቱ ቀርቶዋሌ፡፡ የዚህ
አማራጭ የተዘጋው ህጋዊ በሚመስሌ እና ሇዴሆች በማሰብ በሚሌ ነው፡፡ አዋጅ ቁጥር 621/2001 የበጎ አዴራጎትና ማህበራት
ምዝገባ አዋጅ እና ተከትሇው የወጡትን መመሪያዎች ማየት በቂ ነው፡፡ ውጤቱ ግን ኢህአዳግ እንዯሚያስበው የመንግሰት
ተቀጣሪነት የሰሇቻቸው ሰዎች ፀጥ ሇጥ ብሇው እንዱገዙ፣ መንግስታዊ ያሌሆኑ ተቋሞች ውስጥም አንፃራዊ ነፃነት አግኝተው
ይሰሩበት ከነበረበት ወዯ መንገስት ተቋም በመምጣት የመንግሰትን ተቋምን አሊሳዯጉም፡፡ በተቃራኒው የተገኘው ውጤት
አቅም ያሇው ሁለ በአገኘው አጋጣሚ ሁለ ሀገሩን ጥል ነፃነት ወዯአሇበት ምዴር ሁለ እየተሰዯደ ነው፡፡
የኪራይ ሰብሳቢ ምሽግ ሇመናዴ የተዘረጋው ወጥመዴ በሀገራችን የሚገኙትን የመንግሰትም ሆነ መንግሰታዊ ያሌሆኑ
ዴርጅቶችን በሰሇጠነ የሰው ሀይሌ ከማሳጣት የዘሇሇ ፊይዲ አሊመጣም፡፡ ያመጣው ጥቅም ግን ሳይጠቀስ መታሇፍ የሇበትም፡፡
መንግሰታዊ ባሌሆኑ ተቋሞች የሚሰሩ ዜጎችም አንዴ ቀን ውጭ የሚሄደበት ዕዴሌ እሰኪያገኙ ሌኑርበት በሚሌ ባለበት ዝም
ብሇዋሌ፡፡ አንዴ በቅርቡ ያገኘኋት በቅርብ የማውቃት ሌጅ ሇምን ወዯ ሀገር እንዯማትመሇስ ስጠይቃት አሁን የምትስራበት
መሰሪያ ቤት አሌተመቻትም፣ ከዚያ ወጥታ ላሊ ተመሳሳይ ቦታ ሇመግባት ዯግሞ አሁን ባሇው ፖሉስ ሰራተኛ መቀነስ እንጂ
መጨመር የብዙ መንግሰታዊ ያሌሆኑ ዴርጅቶች ፕሮግራም አካሌ አይዯሇም፡፡ ሰሇዚህ አሁን ከምትኖርበት የባሰ ኑሮ ሇመኖር
ፇቃዯኛ ስሊሌሆነች፤ “የሀገር ፍቅር የትም አይሄዴም ነፃነት እና የስራ ዕዴሌ ባሇበት ብቆይ ይሻሊሌ” ነው ያሇችኝ፡፡ ሁሇተኛ
ዱግሪ በያዘችበት ሙያ ስራ ባታገኝም፤ አሁን የምትሰራው ስራ እንዯተመቻት አጫውታኛሇች፡፡ ይህ እንግዱህ አወጅ ቁጥር
621/2001 ያስገኘው ዴሌ ነው፡፡ ይህችን ሌጅ በፍፁም ህገወጥ ዯሊሊ አሊሳሳታትም፡፡ እርሷን እና መስልቿን ያሳሳትው
የመነግሰት የተሳሳተ የፖሉሲ አቅጣጫ ነው፡፡ የስራ ዋስትናን ማረጋገጥ የማይችሌ መንግስት ትክክሇኛ የህዝብ ዴምፅ
የሚቆጠርበት የፖሇቲካ ምዕዲር ቢኖር እንኳን ሇተከታታይ አራት አይዯሇም አንዴ ተጨማሪ ዙር ምርጫ ማሸነፍ የሚችሌበት
ዕዴሌ አይሰጠውም፡፡ አሁንም መንግሰት ከጊዚያዊ የስሌጣን ጥቅምና ፍሊጎት ይሌቅ ሇዘሊቂ ሀገራዊ ጥቅም ሲባሌ በዚህ
ምክንያት ሀገር ጥሇው የሚሰዯደትን ዜጎች ሇመታዯግ ይህን አዋጅ ሉያሻሽሇው ይገባሌ፡፡ መንግሰታዊ ያሌሆኑ ተቋማትም እሺ
እያለ ነፃነትን ሸጦ ከመኖር በቃን ብሇው ዴርጅት በመዝጋት ጭምር ተቃውሞ ሉያሰሙ ይገባሌ፡፡ ካሊጎነበሳችሁ አትጫኑም
ነው ያሇው ማርቲን ለተር ኪንግ፡፡በሀገራችን የባሇሞያ ስዯት ሌሊው ምክንያት በቂ ክፍያ አሇማግኘት እንዯሆነ ይታመናሌ፡፡ በዚህ ምክንያት ከሚሰዯደት ዜጎች
አብዛኞቹ የህክምና ባሇሞያዎች እንዯሆኑ ቢታወቅም በላልች መስኮቸም ይህ ችግር ጎሌቶ ይታያሌ፡፡ እነዚህንም ዜጎች
መንግሰት እንዯሚሇው ህገወጥ ዯሊልች ያሳሳታቸው ሳይሆኑ መንግስት በሚከተሇው ፖሉሲ ምክንያት በሞያቸው
የዴካማቸውን ያህሌ ስሇማያገኙ፣ እንዱሁም በያዙት ሙያ በላሊ ቦታ የተሻሇ ዕዴሌ ስሇሚያገኙ ጭምር ነው፡፡ ዘወትር የእኛ
ሀገር የባሇስሌጣናት ዯሞዝ ትንሽ ሰሇሆነ እውነት የሚመስሇው ብዙ ሰው አሇ፡፡ ባሇስሌጣኖች ጠቅሊይ ሚኒስትሩን ጨምሮ
የሚያገኙት ዯሞዝ (እዚህ አካባቢ ወ/ሮ አዜብ ትዝ እንዯምትሊችሁ ገመትኩ) በእርግጥ ትንሽ ነው፡፡ ዯሞዝ የሚባሇው ማሇት
ነው፡፡ ከዚህ ውጭ በተሇያየ መንገዴ የሚያገኙት ምንዲ ግን በጣም ብዙ መሆኑ ይታወቃሌ፡፡ ሇዚህም ዋነኛው ምሳላ በቦርዴ
ሰብሳቢነት እና በውጭ ጉዞ የሚያገኙትን መጥቀስ ይቻሊሌ፡፡ በውጭ ሄድ መታከም፣ ነዲጅ፣ የመኖሪያ ቤት እና ላልች ብዙ
ጥቅማ ጥቅሞችንም ማንሳት ይቻሊሌ፡፡ ከዚህ አንፃር አንዴ ባሇሞያ ይህ ዕዴሌ ሳይኖረው በወር ዯሞዝ እንዱኖር ሲጠየቅ
ጥያቄው የሀገር ፍቅር ሳይሆን የምንኩስና ይሆን እና ስዯት አንዴ አማራጭ ይሆናሌ፡፡ ከፍተኛ ሀብት ፇሶባቸው የሰሇጠኑ
ባሇሞያዎች የተወሰነ የማጣሪያ ፇተና በማሇፍ ብቻ ላልች ሀገሮችን ማገሌገሌ አማራጭ እየሆነ ነው፡፡ አንዴ በጥቁር አንበሳ
የሚሰራ ሀኪም የነገረኝ ከካርዴ ብቻ የሚሰበሰበው ገንዘብ ሇሀኪሞች ዯሞዝ ቢመዯብ ሀኪሞች በዯሞዝ ማነስ ምክንያት
ከመሌቀቅ ይዴናለ ነው የሚሇው፡፡ በእውነት ሇመናገር በየጤና ተቋሙ የሚመዯቡ ካዴሬዎች የሚፇጥሩት ጫና በዝቅተኛ
ዯሞዝ መቋቋም ግዳታ አይዯሇም፡፡
በነፃነት ሇመስራት ያሇመቻሌ በሀገራችን በመንግሰት መስሪያ ቤት ብቻ ሳይሆን በግሌ ተቋምም ቢሆን ዜጎች በነፃነት የሚሰሩበት
የስራ ዴባብ ባሇመኖሩ አማራጭ ያሇው ሁለ ከሀገር ተሰድ መኖርን አማራጭ ካዯረገ ውል ሰንብቶዋሌ፡፡ ሇኢህአዳግ ዲኝነት
ቢሆን ህክምና ወይም ምሕንዴስና አብዮታዊ ዱሞክራሲ አመሇካከት ካሌገባው ትርጉም ያሇው ዕውቀት አይዯሇም፡፡ ሇዚህ ነው
ሇኢህአዳግ አዴረናሌ ብሇው የነበሩ በአጋጣሚ ሁለ የውጭ ሀገር ዕዴሌ ሲያገኙ እየተንጠባጠቡ የሚቀሩት፡፡ በነገራችን ሊይ
በተዯጋጋሚ ውጭ የሚመሊሇሱ እና ስሌጣን ሊይ ያለ የገዢው ፓርቲ አባሊት በጣት ከሚቆጠሩት በስተቀር አንዴም ሌጅ
በቤታቸው የሇም፡፡ ሌጆቻቸው በሙለ ውጭ ሀገር ሊይመሇሱ ሄዯዋሌ፡፡ ይህ የባሇስሌጣኑ የነፃነት እጦት መገሇጫ ነው፡፡ አንዴ
ቀን ምን እንዯሚመጣ ያሇማወቅ፡፡ ሁላ በሀገራችን ይመጣሌ እያለ የሚያሰቡት ሟርት ከመጣ ሌጆቻቸውን እንዲይነካ
በማሰብ የተዯረገ ነው፡፡ አሁን በሌማት ሌናስመነዴገው ነው የሚለት ሀገር ሇእነርሱ ሌጆች ሳይሆን ሇዴሆች ሌጆች ነው፡፡ ይህ
በእውነት ዯግነት ነው፡፡ ይህ ሁለ ዴካም ሇሰው ሌጅ ብል ስሇሆነ፡፡ እኔ የምር የምሊችሁ እነዚህ ባሇስሌጣናት በህይወት እያለ
ሌጆቻቸው እንዯሚያዝኑባቸው ጥርጥር የሇኝም፡፡ የመንግሰቱ ኃይሇማሪያም ሌጆች ከሀገር ተሰዯው በመኖራቸው ዯስተኞች
ሉሆኑ ይችሊለ ብዬ አሊስብም፡፡ የማንም ባሇስሌጣን ሌጅ ሀገሩን የሚናፍቅ እንዱሆን እኔ ፍሊጎት የሇኝም፡፡ ባሇሀገር ሌጆች
እንዱኖሩን ሁሊችንም ሌጆቻችንን ሇስዯት ሳይሆን በሀገራችን በሚፇጠር ሀገራዊ ዕርቅ በነፃነት ሀገራቸው እንዱኖሩ ማበረታታ
ያሇብን ይመስሇኛሌ፡፡ እባካችሁ ሇንግግር እና ሀገራዊ መግባባት ሇመፍጠር ጊዜ እንመዴብ፤ ግንብና ግንባታ ይዯረስበታሌ፡፡
“የሰሊም እጆች ይዘርጉ የአዱስ ዓመት መሌዕክቴ ነው”፡፡ የሶሪያ ዱሞክራሲና ሠሊም ዕጦት ግንቡን ሁለ ነው የበሊው፣
እየበሊውም ያሇው፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ ሀገር ሇቆ ሇመውጣት ብቻ ሳይሆን ሇመግባት ፍሊጎት ያሇቸው እጅግ ብዙ ዜጎች አለዋት፡፡ ዲሩ ምን
ያዯርጋሌ አሁን ያሇው መንግስት እነዚህ በአንዴ ወይም በላሊ መሌክ ከሀገር ወጥተው የነበሩ ዜጎች (ዜግነትም ቀይረውም
ቢሆን) አሁን እንዱመጡ የሚፇሌገው ኪሳቸውን በድሊር ሞሌተው ነፃነት ሲፇሌጉ ዯግሞ እዛው በሇመደበት ብቻ የሚሌ አቋም
ይዞ ነው፡፡ ነፃነት በሇመደበት ሀገር ሆነውም ቢሆን ግን ገዢውን ፓርቲ በነፃነት መተቸት አይቻሌም ከእነርሱ የሚጠበቀውየሚጠይቀውን ገንዘብ ሲጠየቁ መስጠት ብቻ ነው፡፡ የማያምኑበት ፖሉሲ እንዱፇፀም የእነርሱ ገንዘብ ማዋጣት ግዴ ብቻ
ሳይሆን ካሊዋጡ ፀረ ሌማት እና ሇሀገር ጠሊቶች የሚሌ ቅፅሌ ስም ሀቃቸው ይመስሊሌ፡፡
በሰሇጠኑበት ሙያ ሇማገሌገሌ የሚችለበት ምቹ ሁኔታ ያሇመኖር አንደ ነው፡፡ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን
በሰሇጠኑበት ሞያ አገሌግልት መስጠት ቢፇሌጉ አብዮታዊ ዱሞክራሲ መቀበሌ ይኖርባቸዋሌ፡፡ ይህም በቀጥታ የሚጠየቅ
ሳይሆን የፇሇጉ ሳይንቲስት ቢሆን መንግስትን መቃወም አይቻሌም፡፡ ሞያቸውን ሇሀገር ካሇው ፊይዲ አንፃር ሳይሆን
የሚመዘነው ሇገዢው ፓርቲ ካሇው የፕሮፓጋንዲ ጠቀሜታ አንፃር ነው፡፡ አንዴ አንዴ ባሇሞያዎች ከዚህ አንፃር ትንሽ ቀዯዲ
ሳይኖር አይቀርም ብሇው ወዯ ሀገር ሲመጡ የመጀመሪያ ሰሇባ የሚሆኑት በኢትዮጵያ ሬዱዮና ቴላቪዥን ወይም ኢቢኤስ
ሇሚባሌ የቴላቪዥን ጣቢያ ነው (ይህ ጣቢያ በኢትዮጵያ የብሮዴካስት ህግ መሰረት ህገ ወጥ ነው)፡፡ እነዚህ ዜጎች መስጠት
የሚፇሌጉትን ከመሰጠታቸው በተጨማሪ ገና እንዯገቡ በሚከቧቸው አጫፊሪዎች ታጅበው ስሇ ሀገሪቱ ዕዴገት፣ ሰሇ አሇው
ዱሞክራሲያዊ ስርዓት፣ ወዘተ ዱስኩር እንዱሰጡ በማዴረግ ቅርቃር ውስጥ ይከቷቸዋሌ፡፡ ሇዚህ ሁነኛ ምሳላ የሚሆነው
ኤርሚያስ አመሌጋ ይመስሇኛሌ፡፡ ላልችም ብዙ አለ፡፡
አሁን በሀገራችን ያሇውን ሁኔታ በተግባር ሇመፇተን ብሇው የፖሇቲካ ብቻ ሳይሆን የኤኮኖሚ ምዕዲሩም ጠባብ እንዯሆነ ብቻ
ሳይሆን በፍፁም እንዯማያንቀሳቅስ ተረዴተው ከጫወታ የወጡትን ዜጎች ቤቱ ይቁጠራቸው በማሇት የሚታሇፍ አይዯሇም፡፡
እነዚህ ዜጎች በውጭ ዯክመው ያገኙት ገንዘብ እንዯዋዛ ከስረው ከጫወታ ሲወጡ ላልች መምጣት ሇሚፇሌጉት ምን
መሌዕክት እንዲሇው መረዲት ተገቢ ነው፡፡ ይህን ፅሁፍ ስፅፍ ኤርሚያስ አመሌጋ ወዯ ሀገር የመኖሪያ ፇቃዴ መሌሶ ሲመጣ እና
ዛሬ ምን እንዯሚሰማው ጥያቄ ማቅረብ ተገቢ ይመስሇኛሌ፡፡ በዚህ ጉዲይ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እንዱሁም በሀገር
ውስጥ ያለ ዜጎች በዯረሰባቸው ጉዲት የኤርሚያስን ስም መስማት የሚያስጠሊቸው ቢሆንም ይህ ሇምን ሆነ ብሇው ከስሜት
በወጣ እርጋታ ሉያስቡት እንዯሚገባ ይሰማኛሌ፡፡ የኦሊንዴ ካር ባሇቤት የነበረው ኢንጂነር ታዯሰም ቢሆን ሇዚህ ጥሩ ምሳላ
የሚሆን ይመስሇኛሌ፡፡ እሲኪ ዴምፃችሁን አሰሙና መንግሰት ምን ዯገፊችሁ ምንስ አዯረጋችሁ፡፡ እንግዱ የበሰበሰ ዝናብ
አይፇራም ይባሌ የሇ፡፡
ዯቡቡ ሱዲን የምትባሌ አዱስ ጎረቤታችን ብዙ ኢትዮጵያዊያ ሇስራ እንዯሚሄደ አውቃሇሁ፡፡ አዱሷ ሀገር እንኳን አሁን
ኢትዮጵያዊያ ወዯ ሀገሯ ሲገቡ እንዯማይቀሩ ሇማረጋገጥ የባንክ አካውንት መጠየቅ ጀምራሇች፡፡ እንዯ አጋጣሚ እኔም ሄጄ
ይህችን ጎስቋሊ ሀገር አይቻታሇሁ፡፡ ብዙ ኢትዮጵያዊያ እዚህች ሀገር ሇምን ተሰዯው ይሄዲለ? ሇሚሇው ጥያቄ ሁላ የምሰጠው
መሌስ ምንም ነገር ስሇላሇ ሁለ ነገር ስራ ነው በማሇት ነው፡፡ ብዙ ትርፍ በአጭር ጊዜ ሇማግኘት የፇሇገ ከነስጋቱ ሄድ በአጭር
ጊዜ ሉከብር ይችሊሌ፡፡ ይህ በኢህአዳግ ሰፇር “ኪራይ ሰብሰቢ” ያሰብሊሌና ማንም ብቅ አይሌም፡፡
ላልች ሀገሮችን በተሇይ አሜሪካን እና አውሮፓን ሳይ ቅናት ያዴርብኛሌ ብዙ ስራ እንዯሚቀረን ይስማኛሌ፡፡ በተነፃፃሪም ያሇው
ነፃነትና ዕዴሌ ብዙ ሰው ሉያማሌሌ እንዯሚችሌ ይገባኛሌ፡፡ በተሇይ ብራዚሉያ የምትባሌ ከተማ እና ብራዚሌ የሚባሌ ሀገር
ካየሁ በኋሊ ኢህአዳግ 22 ዓመት እንዲባከነ እና የብራዚሉያን ያህሌ 5 በመቶ እንዲሌሰራ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ብራዚሉያ
የምትባሇው የብራዚሌ ዋና ከተማ ከተመሰረተች ከ50 ዓመት ብዙ አትዘሌም፡፡ ኢህአዳግ ባሇፈት 22 ዓመት ግማሹን መስራት
ይኖርበት ነበር፡፡ ሇዚህም በውጭ የሚኖረ ኢትዮጵያዊያን እውቀትና ገንዘብ ብዙ ሚና ሉኖረው ይችሌ ነበር የሚሌ እምነት
አሇኝ፡፡ ማስተባበር የሚችሌ የፖሇቲካ ሰርዓት መዘርጋት ቢቻሌ፡፡ በቅርቡ የአሜሪካው ፕሬዝዲን ባራክ ኦባማ ብራዚሌን
እንዱህ ብሇው ገሌፀዋታሌ “ከአንባገነን ስርዓት፣ በሰሊም ወዯ ዱሞክራቲክ ስርዓት የተሸጋገረች” እውነት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህገ
መንግሰት በተወሰነ ማሻሻያ የብራዚሌ ዓይነት ዱሞክራሲ ሉያመጣ እንዯሚችሌ እኔም ይሰማኛሌ፡፡ የብራዚሌ ህገ መንግሰትእንዯ እኛው ህገ መንግሰት ፓርሊሜንተሪ ነበር፡፡ መሪያቸውን በቀጥታ አይመርጡም ነበር፡፡ ህገ መንግስቱን አሻሽሇው
ብራዚሊዊያን ዛሬ ማን እንዯሚመራቸው በቀጥታ ይመርጣለ፡፡ እኛም ሲናፍቀን ይኖራሌ ማሇት አይዯሇም፡፡ አንዴ ቀን
ዘሩ/ጎሳው ማን ነው? ሳንሌ ሇኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊያን ባሇው ራዕይ መሪያችንን እንመርጣሇን፡፡ ተሰፊ አሇኝ፡፡
የተነሳሁበት ሀገር ሇቆ የመሰዯዴ ምንጭ የሚያማሌሌ ነፃነትና ዕዴሌ ያሇባቸው የአሜሪካና አውሮፓ ከተሞች ብቻ ሳይሆኑ
ጎሰቋሊዋ ዯቡብ ሱዲን ጭምር ነች እያሌኩ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊያን በዚህም በዚያም ሀገራቸው ስትገፊቸው ሇምቾት ብቻ ሳይሆን
ችግርም ሇመጋፇጥ በመወሰኝ በረሃና ውቅያኖስ አቋርጠው ይሰዯዲለ፡፡ መንግሰት ግን የችግሩ ምንጭ ህገ ወጥ ዯሊልች ናቸው
እያሇ ትክክሇኛ መፍተሔ ሇመሻት ዝግጁ የሆነ አይመስሌም፡፡ አሁንም ችግሩን ከስሩ ማየት ተገቢ ነው የሚሌ መሌዕክት
ሇማስተሊሇፍ ነው ጊዜ ወስዯን ሃሳባችንን የምናካፍሇው፡፡
አንዴ እናት ሇፆም መፇሰጊያ ምግብ እያዘገጁ ሳሇ መፇሰጊያ ሠዓት ሳይዯርስ ጨው ሇመቅመስ ብሇው ቀመሱ፣ ፆም ሲያዝም
እንዱሁ የተረፇው እንዲይዯፊ ብሇው ፆም ገዯፈ፡፡ ዯግነቱ ይህን ሇንስሀ አባታቸው በሀቅ ሲናገሩ አንቺ ሴት ፆሙን እንዲይገባ
እንዲይወጣ ከሇከሌሽው አሎቸው ይባሊሌ፡፡ የእኛም መንግሰት ዜጎች በሀገር እንዲይቆዮ እና ወዯ ሀገር እንዲይመሇሱ ተግቶ
እየሰራ ነው፡፡ ችግሩ ይህን ግሌፅ አዴርጎ የሚነግረው የንሰሃ አባት ያጣ ይመስሇኛሌ፡፡ በእኔ እምነት የዚህ ዴርጊት ጥቅም ጊዚያዊ
የስሌጣን ፍሊጎት ብልም ሇግሌ ዯህንንት ካሇ ሰጋት ብቻ የሚመነጭ ነው፡፡ የቀዴሞ ጠቅሊይ ሚኒስትር (እርሳቸው ከሌባቸው
ከሆነ የአሁኖቹም ላጋሲ ማሰቀጠሌ ከፇሇጉ) ይለ እንዯ ነበረው ሀገር ማሇት ሰዉ እንጂ ጋራና ሽንተረር ብቻ አይዯሇም፡፡
ባሇሀገር ሉሆን የሚገባውን ትውሌዴ እያባረሩ (የእራሳቸውን ሌጆች ጨምሮ)፣ ላልች ያባረሯቸውም እንዲይገቡ በሩን ጥርቅም
አርገው ዘግተው ሀገር ማሇት ሰው ነው የሚሇው አይገባኝም፡፡ በቅርቡ እንዴነት ሇፍትህና ሇዱሞክራሲ ፓርቲ በመብራት ሀይሌ
አዲራሽ በጠራው የህዝብዊ ስብሰባ ሊይ ሀብታሙ አያላው የሚባሌ ወጣት “ሀገር ማሇት ሌጄ” የሚሌ የአንዴ እውቅ ገጣሚ
ግጥም በሰሜት አንብቦ አስሇቅሶናሌ፡፡ ሀገር ማሇት ሌጄ ሇሌጆች የሚተሊሇፍ ታሪክ ያሇው ሲሆን ነው ሌጄ፡፡
በሀገራችን በነፃነት ሇመስራት ያሇመቻሌ ያቀረበሌን አማራጭ ከገዢው ፓርቲ ጋር ተናንቆ ሇውጥ እንዱያመጣ መግፊት ወይም
ሀገር ሇቆ የመስራት ነፃነት እና ዕዴሌ ወዯአሇበት መሰዯዴ ነው፡፡ ምርጫው የግሌ ቢሆንም መንግሰት ግን ዜጎች በዚህን ያህሌ
ዯረጃ ሇስዯት ሲዘጋጁ አሳዲጅ ሆኖ መገኘቱ ሉያሳስበው እና መፍትሔ ሉፇሌግሇት ይገባሌ፡፡ ይህ በምንም መመዘኛ
“የኒዎሉብራሌ”፣ የኪራይ ሰብሰቢ፣ ወይም የህገ ወጥ ዯሊልች ስራ አይዯሇም፡፡ መንግሰት የሚከተሇው የሌማት አቅጣጫ ዜጎችን
የሚያገሌ እና የፓርቲ ዯጋፉዎችና ጥቂት የሚባለ ሇገዢው ፓርቲ ሇማጎብዯዴ የቆረጦ ዜጎች ብቻ ተጠቃሚ የሚያዯርግ ሰሇሆነ
ነው፡፡ ኢትዮጵያ ብዙ የሚሰራባት ሀገር ነች፡፡ እንዯ ዯቡብ ሱዲን ባንሆንም ምንም ከሚባሇው ብዙ ከፍ የማንሌ ሁለ ነገር ሰራ
ሉሆን የሚችሌባት ሀገር ነች፡፡ ይህችን ሀገር በጋራ ሇማሌማት መነሳት ይኖርብናሌ፡፡ ይህ የፖሇቲካ ሹመት ጥያቄ አይዯሇም፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ዜጎች ሳይሸማቀቁ መሪዎቻቸውን የሚመርጡበት የፖሇቲካ ምዕዲር መፍጠር ብቻ ነው፡፡ ሇዚህም
መተማመን እና ሀገራዊ መግባባት ማሰፇን ይቅር ባይነት በሁለም በኩሌ የግዴ ይሊሌ፡፡
ይህ ካሌሆነ ግን ወዯፉት ኢትዮጵያ የምትባሌ ሀገር በውጭ የሚኖሩ የነበሩ በእዯሜያቸው የመጨረሻ ዘመንም ቢሆን
በሀገራቸው ሇመኖረ የቆረጡ እንዱሁም የትም መሄጃ አጥተው በሀገር የቀሩ የሰዴተኛ ወጣቶች ወሊጆች ሁለም የሚያመርቱ
ሳይሆን ጡረተኞች ሀገር እንዲትሆን ሰጋት አሇኝ፡፡ ይህ ከስጋትም ያሇፇ እውነት ነው፡፡ አንዴ ዘመዳ ያሇችኝ እዚህ ጋ መጥቀስ
ተገቢ ነው፡፡ “ምርታማ ዕዴሜን ውጭ አሰሇፈ ሇጡረታ ሀገር ከመሄዴ የከፊ በዯሌ የሇም ነው” ያሇችው በበዲይነት ሰሜት፡፡ቸር ይግጠመን አዱስ ዓመት የመነጋገሪያ የመግባቢያ ዘመን እንዱሆን ሁሊችንም የበኩሊችንን መወጣት ይኖርብናሌ፡፡ ነፃነታችን
በእጃችን ይዘን የላልችን ነፃነት እናክብር፡፡ ፇጣሪ ይርዲን፡፡ አሜን!!!
Abonner på:
Legg inn kommentarer (Atom)
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar