fredag 9. august 2013

ሙስሊም ወገኖቻችንን መግደል፣ ማሰርና መደብደብ ሕገ-ወጥነት እንጅ መፍትሔ አይደለም!

August 9, 201Print Friendly Version of this pagePrint Get a PDF version of this webpagePDF

ንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ  ፓርቲ  (አንድነት) የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ
ፓርቲያችን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ሁለት ዓመት ለመሙላት ጥቂት ወራት የቀረውን  የሙስሊም ወገኖቻችንን ሠላማዊ የመብት ጥያቄ እንዲያከብር፣ መንግሥት በእምነት ጉዳይ ጣልቃ  መግባቱን እንዲያቆምና ያነሷቸውን ጥያቄዎች በአስተውሎት በማየት እንዲሁም ወደ ውይይት በመምጣት ፍፁም ሠላማዊ በሆነ መንገድ ምላሽ እንዲሰጥ ሲያሳስብ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡Unity for Democracy and Justice (UDJ) party
የመንግስት ሚዲያዎችና አንዳንድ የገዢው ፓርቲ አመራሮች ፓርቲያችን አንድነት የሙስሊም ወገኖቻችንን ጥያቄ በተገቢው መንገድ ምላሽ እንዲያገኝ መጠየቁን፤ መንግስት ከመረጠው የሀይል አማራጭ ይልቅ ነገሮችን በእርጋታ በመመልከት ችግሩን መፍታት እንደሚበጅ መጠቆሙን ፓቲያችን በሐይማኖት ጉዳይ ጣልቃ እንደገባ አስመስሎ ፕሮፓጋንዳ መንዛት መጀመራቸው ውሃ የማይቋጥር ውንጀላ መሆኑን እንረዳለን፡፡ አሁንም ያለን አቋም ከጣልቃ ገብነት በፀዳ መልኩ የሙስሊሞች ጥያቄ ይመለስ ነው፡፡
መንግሥት የህዝብ ጥያቄዎችን በኃይል ለመፍታት የሚወስደው ርምጃ ከሰብአዊ መብት ጥሰት ባሻገርም በህግ የሚያስጠይቀው ተግባር  ነው፡፡ ከዚህ በፊት ሲጠቀምባቸው የነበሩት የመፈረጅ፣ ሽብርተኛ እያሉ የማሰር፣ የማዋከብና የመግደል ስትራቴጂዎች ህዝቡ መብቱን ለመጠየቅ ወደ ኋላ እንዲል የሚያደርጉት አይደሉም፡፡ ከህዝብ ለሚነሱ የመብት ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ ከመስጠትና ከመመለስ በስተቀር የህዝብን ጥያቄ በጉልበት ማስቀረት እንደማይቻል ባለፉት ጊዜያት በሠላማዊ መንገድ የተካሄዱ የእስልምና እምነት ተከታዮች ተቃውሞዎች ማሳያ ናቸው፡፡
በዚህ ሂደት ውስጥም መንግሥት ፊት ለፊት የቀረቡ ጥያቄዎችን መመለስ አለመቻሉ ሳያንስ እንደገና ወደ ኃይል ርምጃ መመለሱ ሀገርን አደጋ ላይ የሚጥል፣ አስተውሎት የጎደለው አካሄድ እንደሆነ ፓርቲያችን ይረዳል፡፡ አሁንም ከዜጎች እየቀረቡ ያሉ የመብትና የነፃነት ጥያቄዎች መልስ እንዲያኙ በድጋሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡  ባለፈው ሳምንት በአርሲ ኮፈሌ በሙስሊም ወንድሞቻችን ላይ የተወሰደውን ርምጃ ፓርቲያችን የሚያወግዝ ሲሆን፤ ድርጊቱን የፈፀሙ ኃይሎች በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡና መንግስትም ለህዝቡ በግልጽ እንዲያሳውቅ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
በትናንትናው እለት በተከበረው የኢድ-አልፈጥር በዓል ላይም ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች  ጉዳይ የሚያሳስበን ሲሆን፣ ይህንንም ድርጊት የፈፀሙት በህግ  እንዲጠየቁ ፓርቲያችን ጥያቄውን ያቀርባል፡፡ የሙስሊም ወገኖቻችንን ጥያቄ በኃይል ለመፍታት መሞከር በአስቸኳይ እንዲቆም፣ የእምነት ነፃነት ስለጠየቁ የታሰሩ ዜጎች በአስቸኳይ እንዲፈቱና ተጠያቂዎች ለህግ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን፡፡
ዘላለማዊ ክብር ለኢትዮጵያ!!!
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
ነሐሴ 3 ቀን 2ዐዐ5 ዓም
አዲስ አበባ

Comments

1 comments

Leave a Reply


Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar