August 17, 2013
ናደዉ ከዋሽንግተን ዲሲ
በክፍል ሦስት መጣጥፌ ላይ ስለምታዩት ሕንፃ ምንነት በመግለፅ በመንደርደሪያነት እንድጠቀም የምወዳት ኢሠፓዋ ባለቤቴ አሣሠበችኝ። በቅዱስ ኡራኤል ስም የሚጠራዉ ይህ የምርጫዉ ቤተክርስትያን አባል መሆንዋን ባልወድላትም በእርሷ አማካኝነት አልፎ አልፎ እሄድ ሰለነበር እነሆ ዛሬ የዚህን ፀረ ተቃዋሚ የወያኔ ተላላኪ ግለሰብ ትክክለኛ ማንነት ለማወቅ ረድቶኛል።
በዋሽንግተን ዲሲ አስራ ስድስተኛዉ መንገድ ላይ ይገኝ የነበረዉ ይህ የንግድ ቤተክርስቲያን ጥቂት የዋህ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በተለይም እናቶችና እህቶችን በዙርያዉ አሰባስቦ፧በሚገኘዉ መዋጮ ጠቀም ያለ ገንዘብ ኪሱ በማስገባት የሚታወቀዉ ምክትል መቶ አለቃ ምርጫዉ አንድ ቀን ድንገት ይነሳና፥ከቤት ኪራይና ቤተክርስቲያናችን ከአንድ ኪራይ ቤት ወደሌላ ቤት እቃ ከማጓጓዝ ልትድን ነዉ፥ቤት በግዢ አገኘሁ ብሎ የምስራቹን ለምእመናኑ ይናገራል፧በማግስቱ የቤተክርስትያኑን ምስጢራትና መፃህፍት ራሱ በሚያሽከረክራት ታክሲ ጭኖ ወደ ተጠቀሰዉ ባለ ሁለት ፎቅ ቤት ይገባል። ትዝ ይለኛል በዚህ በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የሚገኘዉ የአገር ፍቅር ራዲዮ አዘጋጅና አቅራቢ የወያኔ ተላላኪዉ የቅርብ ጓደኛዉ ንጉሤ ወልደማርያምና እህቶቹ የዚህ የንግድ ቤተክርስቲያን ቋሚ አባል እንደነበሩ ከባለቤቴ ጋር በቦታዉ በተገኘሁባቸዉ ሦስት ጊዜያቶች ለመመልከት ችያለሁ። በየጊዜዉ በሚያሳያቸዉ የስነምግባር ግድፈቶች ምክንያት በደሞዝ የሚያሰራቸዉ ቄሶች ብዙ አይቆዩለትም በአሁኑ ጊዜ በቅርቡ ከአገር ቤት በመጡ በአንድ ቄስና በአንድ ዲያቆን ብቻ ነዉ ስርአቱ የሚካሄደዉ።
በጣም የሚገርመዉ ደግሞ ሌሎች የእምነቱን ተከታዮች ለመሳብ የኢትዮጵያን ባንዲራ በሩ ላይ ሰቅሎ የሰዉን መጨመርና መቀነስ የቅዳሴዉ ስርአት ሲካሄድ እንኳ ሳይቀር ፧እየተንጎራደደ ገበያ እንደቀረባት ኮማሪት ገባ ወጣ እያለ ፧ወጪ ወራጁን በአይኑ ሲያማትር ይቆይና፧የፀሎት ሥርአቱ እንዳበቃ የሆነ የገንዘብ መለመኛ ምክንያት ፈጥሮና በሚስቱ ገንዘብ ተቀባይነት ሰብስቦ በቀጥታ ያለ ደረሰኝ ኪሱ ያስገባል። ይህ አሰራር ለረጅም አመታት የለመደዉ የዘረፋ ትርኢት ነዉ። ይህንን ሁሉ አሳፋሪ ተግባር ሲፈፅም ማንም የእምነቱ ተከታይም ሆነ የሃይማኖቱ አባቶች በቃ ያለዉ የለም፣ ምክንያት፧በራሱ ራዲዮ ላይ ወጥቶ ስም እየጠቀሰ የሚያካሂደዉን ፀያፍና ግልብ ንግግሩን ፍራቻ ብቻ።
በወቅቱ ሕንፃዉ የሚገኘዉ በመኖርያ ሰፈር ዉስጥ ስለነበረ ከጥቂት ግዜያት አገልግሎት በኋላ የአካባቢዉ ነዋሪዎች በቅዳሴዉ ድምፅ መረበሻቸዉን ለመንግሥት አቤት አሉ፧ በዚህ ምክንያት ቄሱም ሆኑ ምእመናን ድምፅ እንዲቀንሱ በቤተክርስቲያኑ ባለቤትና አስተዳዳሪ በሆነዉ በጓድ ምክትል መቶ አለቃ ምርጫዉ ስንሻዉ መመሪያ ተሰጠ ለጥቂት ወራቶችም በጥንቃቄ አገልግሎት ተጀመረ። ነገር ግን ብዙም አልቆየም።
ከእለታት አንድ ቀን እኔና ባለቤቴ በመኪና በዚያ በኩል ስናልፍ በክፍሉ ዉስጥ ያሉት እቃዎች መፅሃፍትና ምሥጢራት በፍርድ ቤት ትእዛዝ ከቤት ውጭ ሜዳ ላይ ሲወረወሩ እንመለከታለን፧የአካባቢዉ ነዋሪዎችም በድል አድራጊነት በሚመስል ስሜት ተሰብስበዉ እየተመለከቱ ስለሁኔታዉ ሲነጋገሩ ተመለከትን ።በዚህ ሰዓት ኢትዮጵያዊቴና ይልቁንም በሃይማኖቱ ተከታይነቴ አፈርኩ፧አዘንኩ። ባለቤቴም ለቅሶዋን አስነካችዉ።
በአንድ ወቅት ከባለቤቴ ጋር በዚህ ጉዳይ ዙርያ ችግሮች እንደነበሩብን አስታዉሳለሁ። የሰዉየዉ ሁኔታ ስላላማረኝ በአካባቢዉም ኢትዮጵያዉያን ማሕበረሰብ ብዙ አስነዋሪ ነገሮች ስለሚወራበት፧ባለቤቴ የዚህ ቤተክርስትያን አባል እንዳትሆን በማሳሰቤና ማሳሰቢያዬን ችላ በማለትዋ በቤታችን ዉስጥ ሰላም መጥፋቱ አልቀረም ነበር። የዛን እለት ሁኔታዉን ካስተዋለች በኋላ ግን ይህን ሰዉ መከተልዋ አግባብ እንዳልነበረ በፀፀት እንባ እየተናነቃት ይቅርታ ጠየቀችኝ። ዛሬ ስለዚህ ወስላታ ካድሬ መስማት ትጠየፋለች።
የሚገርማችሁ ይህ ሰዉ አስነዋሪ የንግድ እንቅስቃሴዉን በዚህ አላበቃም፧ከዚያ በኋላ ሁለት ጊዜ የተለያዩ ቤቶች ተከራይቶ ተመሳሳይ ንግድ ሥራ ላይ ተሰማርቶ ይገኛል በአሁኑ ወቅት እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ አስራስድስተኛዉና ፒ እስትሪት በሚገኝ በአንድ ሕንፃ ሁለተኛ ፎቅ ላይ ከፍቶ ታገኙታላችሁ። ዛሬ ከሱ ጋር ጥቂት የዋህ እናቶችና እህቶች ሲቀሩ በዛ ያሉት አባላቶቹ ከእንግዲህ አይቀለድብንም አንበላም ብለዉ በአስራአራተኛዉ መንገድ የራሳቸዉን ቤተክርስቲያን አቋቍመዉ እየተንቀሳቀሱ ነዉ። እነሱም ዛሬ ስለዚህ ግለሰብ ብዙ ይላሉ።
የእህቱ የምስራቅ ስንሻዉ ባለቤትና የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ይሰራ ከነበረዉ ግለሰብ በሚሰጠዉ መመርያ መሰረት የዳያስፖራዉን ፀረ ወያኔ የትግል አንድነት እንቅስቃሴ ለማኰላሸት ከመቸዉም ግዜ በላይ የሰርጎ ገብ ተላላኪነት እንቅስቃሴዉን በሰፊዉ ተያይዞታል። እኛም የዋሆቹ በየሳምንቱ አራት ሰዓት እየተከፈት የምንሰደብበትን ራዲዮ እናዳምጣለን እዉነቱን እያወቅን ዝም ብለን ቆይተናል፥አሁንስ በዛ በቃህ ማለት ያልቻልነዉ ለምን ይሆን?!
ይህ መሰሪ ጋጠ ወጥ ካድሬ በዚህ አራት ሰአታት ለሚሳደብበት ራዲዮ ጣቢያዉ ማስታወቂያ ለማስተላለፍ የብዙ ንግድ ቤቶችን ባለቤቶች ቢጠይቅ አልተሳካለትም፥ ለብዙ አመታት ዛሬም ድረስ በብቸኝነት የማስታወቂያ የገንዘብ ድጋፍ የምታደርግለት የሸገር መደብር ባለቤት ብቻ ነች። ብዙዎች ስለዚህ ግንኙነት ጉዳይ ብዙ ይላሉ የምክንያቱ መረጃ በጄ ቢኖረኝም ለጊዜዉ ትቼዋለሁ፧ወደፊት እንዳስፈላጊነቱ እሄድበታለሁ።
ብዙዉን ጊዜ ጓደኞቼም ጭምር የሚያነሱት አንድ ነገር አለ ይኸዉም በየሳምንቱ የአራት ሰአት የራድዮ ስርጭት እንዴት ሊከፍል ቻለ? የሚል የጅል ጥያቄ በአግራሞት ሲጠይቁ ይደመጣሉ፧ ወገኖቼ እየነገርኳችሁ አላምን አላችሁኝኮ !የባለስልጣን ቤተሰብና በወያኔ የጥፋት ተልዕኮ በጀት ተመድቦለት ነዉ ስላችሁ አትሰሙም?!
ደግሞ ሰሞኑን አንድ ወሬ አነፍናፊ የምወደዉ ጓደኛዬ ምን አለኝ መሰላችሁ፧ ባለፈዉ ሼኹ ባቋቋሙት አዲሱ ሆድአደር ፌዴሬሽን የእግር ኳስ ክለብ ዉስጥ የምርጫዉ ወንድ ልጁ ተሰልፎ ተጫወተ አለኝ ፧እኔም እንኳን ምን ይጠበስ አልኩት!!እንደ ጓድ ምርጫዉ ፣ አዎ!ምን አለ መሰሳላችሁ፧ባለፈዉ ሳምንት ባልተገራዉ የባለጌ አንደበቱ በራዲዮ ሥርጭቱ ላይ ብስጭት ብሎ፧ የእቁብ ገንዘብ በልተሃል ይሉኛል! አዎ እንኳን በላሁ!ደግ አደረግሁ አለን!!! ምን ያላለን አለ?! እኔም ጓደኛየን እንኳን ልጁ እሱም ይጫወት ደግ አደረገ አልኩታ !!
ጓድ ምርጫዉ ለመሆኑ በዚህ አመት እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ በአፍራሽ ጎራ ተሰልፎ ስለነበረው የእግር ኳስ ፌዴሬሽን አንድ ቃል ተንፍሰሀል? ስለ ወያኔ ተላላኪዎቹ ሆድ አደር ጓደኞችህስ ተቃዉሞ አሰምተሃል? አንተ ሁል ጊዜ የምታላዝነዉ ተቃዋሚ ድርጅቶችና መሪዎቻቸዉ ላይ ብቻ ነዉ። በየትኛውም መመዘኛ እግራቸው እጣቢ እንክዋን ለመድርስ የማትችል ፈረንጆቹ ሪፍ ራፍ የሚሉት መሆንን ውስጠ ውስጥህ ያውቀዋል። የእነሱን ስም በማንሳት በሬ ወለደ በመደራረት አንተ ትልቅ ኢትዮጳያዊ የሆንክ የሚመስልግ በራስህ ውሸት የምትስከር ባዶና ክንቱ ባለጌ ነህ። በሌላ በኩል ደግሞ የዋናዉ ተልእኮህ መስመር የተቀጠርክበት ርካሽ ተግባር ፤ሌላም ጥያቄ አለኝ ጓድ መቶ አለቃ፧ አዎ !እዚህ ዋሺንግተን ዲሲ በዳያስፖራው ትግልና ገንዘብ ሲቀልዱ ከርመዉ በመጨረሻዉ ለወያኔ ፍርፋሪ ለሆዳቸዉ ማደራቸዉን በአደባባይ በግልፅ ነግረዉን እንደሄዱት የትግል ጓዶችህ እንደ አንድ ኢትዮጵያዉ ራዲዮ ተላላኪ ዮሴፍ ግዛቸዉ ፤እንደ ሀገር ፍቅር ራዲዮ ባንዳ ንጉሴ ወልደማርያም፣ እንደሆዳም ግሳንግሱ ሰለሞን ተካልኝና እንደአዉራምባዉ ዳዊት ከበደ፧በግልፅ ነግረኸን ወያኔ ጉያ የምትሸጎጠዉ መቼ ይሆን?! መቼ ይሆን ትክክለኛዉ አንተነትህን የምታበስረን?! ሰዎችን ስብዕና እያነሳህ ፀያፍ ቃላቶች በተካነዉ አንደበትህ የምትዘረጥጥበት የደንቆሮዎች ድፍረትህ ይሄን ለማለት እንዴት ተልፈሰፈሰ!?ምነዉ አቅም አጣ?! ደግሞ እባክህ ወንድሜ ኢትዮጵያዊነት የሚለውን ብዙ የዚያች አገር ዜጎች ውድና ተተኪ የማይገኝለት ህይወታቸዉን ገብረዉለት የሄዱበትን ስም ስትጠቀምበት አታፍርም መልከ ጥፉ በስም ይደግፉ ይሉሀል ይህ ነዉ።
ተሰናበተን! ወግድልን !የሚያዋጣህ ጎዳና ያኛው ነዉና !!!
አሣ ጎርሪ ዘንዶ ያወጣል የሰዉ ፈላጊ የራሱን ያጣል። ይቀጥላል፦፦፦፦ በክፍል 5 እንገናኝ
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar