mandag 22. juli 2013

“ጥቁሩ ሰው” ይናገራል!


Obang O Metho
November 16, 2012 10:49 am By  6 Comments (Edit)
 
“ጥቁሩ ሰው” ይሉታል። ኢትዮጵያዊያን ለሚያሽከረከራት አስፈሪ ፈተና መፍትሄው ሰብአዊነትን ማስቀደም ብቻ ነው የሚል የጸና እምነት አለው። “ከጎሳ በፊት ሰብዓዊነት” በሚል መሪ ዓላማ ከሚመስሉት ጋር በመሆን ድርጅት አቋቁሞ መሥራት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ባከናወናቸው ሥራዎች ከፍተኛ እርካታ እንደሚሰማው ያምናል። ኢትዮጵያዊያን ችግር ደርሶባቸዋል በሚባልበት ሁሉ ቀድሞ ደራሽ እንደሆነ ብዙዎች ይመሰክሩለታል። በዚህና በሰብዓዊ መብት ጉዳይ በሰራቸው ስራዎቹ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ደጋፊዎችና አድናቂዎች ለማፍራት ቢችልም “ከጀርባው ድብቅ ዓላማና አጀንዳ አለው፣ ብቻውን ይሮጣል” የሚሉትን ጨምሮ በግል አቋሞቹ ዙሪያ ነቀፌታ የሚሰነዝሩበትም አሉ።

የወደፊት ዕቅዱና የሚነቅፉት እንደሚሉት መቼ ፖለቲካ ፓርቲ መስርቶ ይፋ ያደርጋል? በሚሉትና በተመሳሳይ ጉዳዮች ዙሪያ ኦባንግ ሜቶ ከጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ጋር ቃለ ምልልስ አድርጓል። ኦባንግ ሜቶ (ጥቁሩ ሰው) የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን ጋምቤላ ተማረ። ከዚያም ሁለተኛና የዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን ካናዳ ተከታትሎዋል። በመጀመሪያ የጋምቤላ ልማት ኤጀንሲ (GDA) የሚባል ድርጅት አቋቁሞ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ነበር፡፡ በኋላም በጋምቤላ የዛሬ 9ዓመት አካባቢ ከ400 በላይ አኙዋኮች ሲጨፈጨፉ ህይወቱ ተቀየረ፡፡ ሁኔታው በአመለካከቱ ላይ ብቻ ሳይሆን በግል ህይወቱ ላይ ከፍተኛ ለውጥ አመጣ፡፡ ሁሉንም ትቶ ድምጽ አልባ ለሆኑት ድምጽ ለመሆን የአኙዋክ የፍትሕ ምክርቤትን በማቋቋምና በኃላፊነት በመሥራት የመለስ አገዛዝን እና የወንጀሉን ተዋናዮች በዓለምአቀፍ ፍርድርቤት ሊያስከስስ የሚችል ተግባር አከናወነ፡፡ ሆኖም ችግሩ የአኙዋክ ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያ መሆኑን በጥልቅ ከተረዳ በኋላ ኢትዮጵያ ነጻ ሳትወጣ አኙዋክ ብቻ ወይም ሌላው እንዲሁ በግሉ ነጻ ቢወጣ ችግሩ ፈጽሞ ሊቃለል እንደማይችል በተረዳበት ጊዜ ትግሉን ቀየረ፡፡ አዲሲቷ ኢትዮጵያ ብትመሠረት የሁላችንም ችግር መፍትሔ እንደሚያገኝ በማስተዋል ከበርካታ ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄን (አኢጋን) (http://www.solidaritymovement.org/) በማቋቋም የትግሉን መስመር አሰፋው፡፡ “ሁላችንም ነጻ ካልወጣን ማንም ብቻውን ነጻ መሆን አይችልም” የሚለውን መሪ መፈክር በማንገብ “ከጎሣ ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ” እንዲሰጥ በመታገል ዓመታትን አስቆጥሯል – ኦባንግ ሜቶ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር! ([ሙሉውን አስነብበኝ / read more])
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++

ኢህአዴግ በፖለቲካ ወለምታ ውስጥ!!

አባተ ኪሾን መልሶ ለመሾም ውስወሳ ተጀምሯል
eprdf
November 14, 2012 08:59 am By  Leave a Comment (Edit)
 
ኢህአዴግ በ“ፖለቲካ ወለምታ” ውስጥ እንደሚገኝ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የኢህአዴግ ዲፕሎማት ለጎልጉል ተናገሩ። በከፊል ኢህአዴግን የተለዩ የሚስሉት ዲፕሎማት በጎልጉል የቅርብ ሰው አማካይነት ድምጻቸው ሳይቀረጽ ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳሉት የተፈጠረው የፖለቲካ ወለምታ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል አመልክተዋል። የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት በመካከለኛ አመራሩ ውስጥ የመጠራጠር ስሜት መፈጠሩን በፓርቲ ግምገማ ላይ በግልጽ መናገራቸው የዲፕሎማቱን አስተያየት የሚያጠናክር ሆኖ ተገኝቷል።
የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች የአቶ መለስን ሞት ደብቀው በመያዝና ማስተባበያ በመስጠት ጊዜ የወሰዱት ይኸው የተባለው የፖለቲካ ወለምታ እንዳይፈጠር ለማድረግ በማሰብ እንደነበር ዲፕሎማቱ ያስታውሳሉ። ይሁን እንጂ አቶ መለስ ሁሉንም ጉዳይና ሃላፊነት ብቻቸውን ይዘውት ስለነበር በድንገት ማለፋቸው ፓርቲው ውስጥ አሁን በየደረጃው የሚታየው የመተርተር አደጋ መከላከል ግን አልተቻለም።[ሙሉውን አስነብበኝ / read more]
&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&&

“ኦባማ መጀን” ወይስ “በእውቀት” መደራጀት?

obama back to w h
November 10, 2012 03:57 am By  9 Comments (Edit)
 
የአሜሪካ ምርጫ ሲጠናቀቅ ተሸናፊው ሚት ሮምኒ ደጋፊዎቻቸው በተሰበሰቡበት አዳራሽ ምስጋና ካቀረቡ በኋላ እንዲህ አሉ፡- “… ሁለታችንም ለምንወዳት አገራችን የምንመኘውን ለማድረግ በተለያየ አቅጣጫ ሞከርን፤ … ሕዝባችን ደግሞ የሚፈልገውን መሪ መረጠ፤ … ስለዚህ ፕሬዚዳንቱን ደውዬ አነጋሬያቸዋለሁ፤ ባገኙትም ድል እንኳን ደስ አለዎ ብያቸዋለሁ፤ … በተለይ ለእርሳቸው፣ ለቀዳማዊ እመቤት እና ለልጆቻቸው ሁሉ መልካሙን እመኛለሁ፤ … አገራችን ከባድ ፈተናዎች ተጋርጠውባታል፤ … ባለቤቴና እኔ ለፕሬዚዳንቱና ቤተሰባቸው ከልብ እንጸልያለን፤ በሥራቸው ስኬት እንዲያገኙና ታላቋን አገራችንን በመምራት የሚያከናውኑት ሁሉ የተሳካ እንዲሁን እመኛለሁ፡፡” ይህንን ካሉ በኋላ ወደተለመደው ህይወታቸው ሄዱ – የፖለቲካ ገዳም ገቡ፡፡ ይህ ንግግር ወደራሳችን እንድንመለከት የሚያደርግ ነው፡፡ የእኛስ ፖለቲከኞች ዕድሜ ልካቸውን የፖለቲካ አክሮባት እየሰሩ አንደ ፓርቲ ሲያቋቁሙ፤ ሌላ ሲያፈርሱ፤ አንዱን ሲጠልፉ ሌላውን በሾኬ ሲሉ … ከመቆየት ይልቅ የሚሞክሩትን ሞክረው አልሆን ሲል በክብር ለተከታዩ ቦታ ለቅቀው ወደ ፖለቲካ ገዳማቸው የሚገቡት መቼ ይሆን? [ሙሉውን አስነብበኝ / read more]
********************************************************************************

ከፖለቲካ ተሃድሶ በፊት [የእውቀት] ተሃድሶ በአስቸኳይ!!

(ርዕሰ አንቀጽ)
reform
November 9, 2012 10:55 am By  3 Comments (Edit)
 
ከሰው ልጅ መሰረታዊ ባህርይ በመነሳት ሲታይ ሃያ ዓመት በአንድ ድርጅት መተዳደር በራሱ ይሰለቻል። አቶ መለስ “ሳያርፉ ሞቱ” እየተባለ እንደተነገረን መሪውን ያታክታል፡፡ የአገዛዙን ማሽን ጥርስም ይሰብራል፡፡ የሰው ልጆች ሁሌም አዲስ ነገር ይሻሉ። በተለይም እንደ ኢህአዴግ ካለ መንግስት ጋር የኢትዮጵያ ህዝብ ለሁለት አሰርተ ዓመት መዝለቁ አስገራሚ ነው። አንዳንዶች “አስማት” እንደሚሉት፤ “ኢህአዴግ ሃያ አንድ ዓመት መንበር ላይ የተቀመጠው በራሱ ጥንካሬ ሳይሆን በሌሎች ድክመት ነው” የሚሉ ቢኖሩም ኢህአዴግ በቀላሉ ሌሎች እንደሚስሉት ተገፍትሮ የሚወድቅ ድርጅት አይደለም በሚል የሚከራከሩም አሉ። በኛ እምነት ግን ችግሩ የሚቀድመውን ተሃድሶ አለማወቁ ላይ ነው።
በኢትዮጵያ ባለፉት ሃያ አንድ ዓመታት የድርጅት እጥረት አላጋጠመንም። ለቁጥር የሚታክቱ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ተቋቁመዋል። ከመንደር እሳቤ ጀምሮ እስከ ብሄራዊ ደረጃ ከተዋቀሩት የተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ምን ያህል እንደተሳካላቸው በውል ባይታወቅም ህዝብ አደራጅተናል የሚሉ አሉ። መቋቋማቸው ሳይሰማ “እንደወጡ” የቀሩ ብዙ ናቸው። እንደው ለወጉ ያህል ስያሜያቸውን እያሰሙ በመግለጫና በዘለፋ “አልጠፋንም” የሚሉም አሉ። ለዓመታት ጎረቤት አገር መሽገው ከዛሬ ነገ “መጣን” የሚሉን አሉ። መኖራቸውም መሞታቸውም ልዩነት በሌለው መልኩ የሚንከላወሱ “ሙት” ነዋሪ ፓርቲዎችም አሉ። የፖለቲካ ዓላማቸው ሌሎችን በሾኬ መጣል፤ የኢኮኖሚ ፕሮግራማቸው ሌሎቹን ማክሰር፤ የማኅበራዊ ፖሊሲያቸው ማበጣበጥ፤ የሃይማኖት አመለካከታቸው “እኛ ካልባረክነው ዉጉዝ ነው” የሚል ፕሮግራም ያላቸው የሚመስሉም አሉ፡፡ ኢህአዴግ ጥብቆ አልብሶ ያደራጃቸው “ተለጣፊ” የሚባሉትም አሉ። ቤተሰብ ሰብስበው ቃለ ጉባኤ እያጸደቁ አገርና ህዝብ ነጻ እናወጣለን የሚሉም አሉ። አጋነናችሁ ካላላችሁን ከእቁብና ከእድር ባነሰ አደረጃጀት አገር ለመምራት ተነስተናል የሚሉ እፍረት ያልፈጠረባቸውም አሉ። እየተሰነጠቁና እየተሰነጣጠሩ ኤ፣ ቢ፣ ሲ፣ ዲ፣ ኢ፣ ኤፍ፣ … የሚባሉትና ሌላም ሌላም ዓይነት፡፡ ለምን እንዲህ ይደረጋል ሲባሉ “ለአንድ ኢትዮጵያችን ብለን ነው” ይሉናል! [ሙሉውን አስነብበኝ / read more]

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar