torsdag 25. juli 2013
በቃኽኝ
መሠረት አባተ ኖርዌይ ጁላይ 2013
ለሥልጣኑ መሰንበት እንቅልፍ የለሹ የኢህአዴግ መንግሥት የመረጠው ሕዝብ ትዝ የሚለው ¨ሃገር-አቀፍ የምርጫ¨ ጊዜ
ሲደርስ ብቻ ነው። ይህንኑ የኢህአዴግ ባህርይ ባለፉት የተለያዩ ሃገራዊ ምርጫዎች መዳረሻ ጊዜዎች ላይ ተፍ-ተፍ
የሚልባቸውን ሥልቶች ማስታወስ ብቻ በቂ ነው። በ1997 ዓ.ም የምርጫ ወቅት የዜጐች ቁርጠኛ ውሣኔና ቁጣ በምርጫው
ውጤት ላይ ያደረሰውን አሉታዊ ሁኔታዎች ያስበረገገው ኢህአዴግ ከዛ ዘመን ጀምሮ ከተከሰተው ድብቅ ባህርያቱ አንዱ
ፈሪነቱ ነው።
የህዝቡ ቁጣና ውሣኔ ውስጣዊ ድንጉጥነቱን ለአደባባይ ካበቃው በኋላ የኢህአዴግ የማስመሰል ትወና ረቀቅ ማለቱና
ጭካኔው ማየሉ የባሰ ሆኗል፡፡ በከፍተኛ የመኖሪያ ቤት ችግር እየተሰቃየ ያለውን ሕዝብ ቀልብ ለመሣብና የሕዝብ ድምፅ
አይበገሬ ኃይል እንዳለው በተመሠከረበት በ1997 ምርጫ ባለድል ለመሆን የጋራ ቤቶች ተጠቃሚ ላደርጋችሁ ነው በሚለው
ምልጃው በመሣብ የተመዘገበው ዜጋ በጉጉት ካለበት ችግር ለመላቀቅ በማሰብ ተመዝግቦ ቤቱንም ሣያገኝ ስምንት ዓመት
ካለፍ በኃላ ወቅት ጠብቆ ከች የሚለው ኢህአዴግ አዲስ የመኖሪያ ቤት ምዝገባ ብሎ አወጀ ለነባሮቹ ቅድሚያ እሰጣለሁም
አለ ችግር እንዲያምኑት ያስገደዳቸው ዜጐች የምዝገባ ካርዳቸውን ይዘው ነባር ተመዝጋቢ ነኝ ብለው ቢቀርቡም ከመረጃ
ቋቱ ውስጥ ስምህ ስምሽ የለም ተብለው በእነርሱ የምዝገባ ቁጥር የሌሎች የሥርዓቱ አፋሽ አጐንባሾች ስም ተተክቶ
ሲያገኘው ዜግነቱን ጠልቶ በምሬት አቤቱታውን በግልም በህብረትም ቢያቀርብ ከፈለክ በአዲሱ ምዝገባ ተመዝገብ
(ተመዝገቢ) ከሚል የንቀት ምላሽ ባሻገር ጉዳዬ ብሎ የሚጥፈው ሹም አላገኘም።
በአሁን ወቅት ፖለቲካው የበላይነቱን ጠብቆ ለማቆየት ድርጅቱን በገንዘብ አቅም ለማፈርጠም በእራሱ ሥር ካሉ ግዙፍ
የንግድ ተቋማቱ ዝርፊያ ተጨማሪ ለቤት ቁጠባ በሚል ሰበብ ዜጐች ከዕለት ጉርሣቸው እየነጠቁ በሚያስረክቡት ገንዘብ ነዶ
ቋቱን በመሙላት ላይ ይገኛል። ‘ሌባ እናት ልጇን አታምንም’ እንዲሉ በሥሩ ካለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውጭ የዚህ
ተግባር ተሣታፊ እንዳይሆኑ በሩን በመዝጋት የግል ባንኮችን ህልውና ከስጋት ውስጥ ከቶታል። በዚህም የእነርሱን ሃገራዊ
የዕድገት ድርሻም በማቀጨጭ ላይ ይገኛል።
ለረዥም ጊዜ በአንድ አካባቢ የኖሩ ዜጐችን እንደ አረብ ዓለም አብዮት በእኔም ላይ መክረውና ዶልተው ሊነሱብኝ
የሚችሉበት ቀን ሊኖር ይችላል። ስለዚህም በጋራ ቤቶች (Condminum) አብሮነታቸውን አፍርሶ በተለያዩ የከተማዋ
ጠርዞች መበታተን ዋንኛውና የኢህአዴግ ድብቁ ዓላማ ከመሆኑም ባሻገር ይሄው የጋራ ቤቶች ሥርዓቱ አቀንቃኞች ብቻ
ከየወረዳው እየተመረጡ የዕጣው ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚደረግበት ስለመሆኑ ተመዝግበው ከመረጃ ቋት ውስጥ ስማችሁ
የለም የተባሉ ወገኖች ላይ የተፈፀመው በደል ጉልህ አስረጂ ነው ወደፊትም ከዚህ የተለየ አፈፃፀም ይኖረዋል ማለት ከእባብ
የእርግብ እንቁላል የመጠበቅ ያህል ነው።
ዛሬ ነጋዴው ሃገሬ ብሎ በፍፁም እምነት የማይነግድባት ሃገር ኢትዮጵያ ብቸኛዋ የአለማችን ሃገር ናት ለማለት ይቻላል።
በነጋዴው የእህዋት መንግሥት ከመዋጥ የተረፉ ነጋዴዎች የንግድ ቤታቸውን ሸጠው ለመገላገል ያከራይዋቸዋን ሰዎች
እየተማፀኑ ይገኛሉ። ምክንያቱም ከልጅነት እስክ አዛውንትነት ሜዳ ተራራውን አቋርጠው የነገዱ ወገኞች ትላንት ቤሣ-
ቤስቲን ያልነበራቸው የአንድ ጐሣ ተወላጆች በአጭር ጊዜና ፍጥነት የናጠጡ ቱጃር እየሆኑ ሲታዩ ከጀርባቸው ያለው ምን
እንደሆነ አመላካች ነውና ሥጋቱ ከሃብት ወደ ሕይወት መሸጋገር እንዳይሆን ከመንገዱ እርቆ በመውጣት በገዛ ሃገራቸው
ሁለተኛ ዜጋ ሆነው የበይ ተመልካች ከመሆን የተሻለ ዕድል የላቸውም።
በተለያዩ የገንዘብ መሰብሰቢያ ዘዴዎች ሽንኩርት እና ቃሪያ ጉሊት ተቀምጠው ከሚቸረችሩ ምስኪኖች መቀነት እየፈታ
በመንጠቅ ሕዝቡ የእኔ የሚለው ሃብት የለሽ ያደረገው የወያኔ መንግሥት ከሃገሪቱ ገጠርማ ክፍሎች በማዳበሪያ ግዥ
ጀርባው የተላጠው ገበሬ የእርሻ በሬውን እየሸጠ ከ14 እና 16 ዓመት እድሜአቸው ያልዘለለ ህፃናት ሴቶች በመላክ እየፈለሱ
በመምጣት በመዲናችን ሲንከራተቱ ከመኪና አደጋ ከተረፉት ዜጐች ፓስፖርት በመቸርቸር ለስደት ከመዳረግ ባለፈ
በሚሄዱበት ሃገሮች የሚፈፀምባቸውን ህገወጥ የአካል እና የሥነልቦና ጉዳት በሃገራቱ ባሉ የመንግሥት ተጠሪዎች
ከመከላከል ይልቅ የሚደርስባቸው የግፍ ሰቆቃ እና በየበረሃው የወደቀው አስክሬናቸው እስኪጠራቀም ጠብቆ የሕዝብ
Abonner på:
Legg inn kommentarer (Atom)
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar