ኢትዮጵያ
የብሪታንያ ፓርላማ በኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ ሲወያይ አመሸ። ሃዉስ ኦፍ ኮመን በመባል የሚታወቀዉ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ትናንት ማምሻዉን የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታና ያለፉት 22ዓመት እንዲሁም ወደፊት እያንዣበበ የመጣ ያለዉን ችግር የዳሰሰ ጉባኤ ተካሂዷል።
ጉባኤዉ ኢትዮጵያን የሚመራዉ መንግስት ህዝብ በማፈን በማሰርና ለስደት በመዳረግ መታወቁ የተገለጸ ሲሆን ከጊዜ ወደጊዜም በዚህ ረገድ መሻሻል እንዳልታየ ተጠቅሷል። በዉይይቱ ማጠቃለያም የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች እንዲሁም ጋዜጠኞች፤ እንዲፈቱ፤ መገናኛ ብዙሃን ላይ ጫና የሚያደርጉ ህጎች፤ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን የሚመለከተዉ ህግ እና የጸረ ሽብር ህጉ ባስቸኳይ እንዲቀየሩ መጠየቁን የሎንደኑ ዘጋቢያችን ድልነሳ ጌታነህ የላከዉ ዘገባ ያስረዳል።
ድልነሳ ጌታነህ
ሸዋዬ ለገሠ
ተክሌ የኋላ
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar