torsdag 25. juli 2013

ብሶትሽ ብሶቴ!

!
ቁጥር ፪ውርድ ንባብ ሳይቀር - እንድማር አድርገሽ፣
ቃለን ተማርልኝ - ጨዋ ሁንልኝ ብሇሽ፣
ብርሃን ከጨሇማ - እንድሇይ አድርገሽ፣
ታሪኬን እንድማር - ትምሕርትቤት ሰደሽ፣
ደፋ ቀና ብሇሽ - ፍዳ አበሳ አይተሽ፣
ሲገለት ልጅሽን - ባዶ ሲሆን ሕልሙ፣
ሇአዞ እየተጣሇ - ከባሕር መስጠሙ፣
በፍጅት አሇቀ - ከንቱ ሆነ ሕልሙ።
ደነዝ ነው ዲጂኖ - የገደሇኝ ልጅሽ፣
ከጠላት አብሮ - ላንቺ ሳይሳሳልሽ።
ምጣዱን አስምተሽ - እንጀራውን ጋግረሽ፣
በመንደሩ ዞረሽ - በሰው ቤት ተቀጥረሽ፣
እፍ እፍ ብሇሽ - ትንፋሽስን ተንፍሰሽ፣
በጭስ እየታፈንሽ - እሳት እያነደድሽ፣
እሳት አቀጣጥሇሽ - ጉልቻ ጎልተሽ፣
አንተ ብቻ ተማር - እደግልኝ ብሇሽ፣
አይኖችሽ ሞጭምጮ - አይናር ብቻ ሆኖ፣
መታከሚያ ጠፍቶ - ድህነቱ ሰፍኖ ፣
ማየት እስኪሳንሽ - እምባ እያቀረሩ፣
ካፍንጫሽ የሚወጣው - አመዱ አፈሩ።
አንቺ ሳይመችሽ አንተ- ይመችህ ብሇሽ፣
አንዴ ሳያምርብሽ የረባ - ጨርቅ የሇሽ፣
ውሃ እንኳን ሳይነካው - ሳሙና ተወዶ፣
ዓመት በዓል ሲከበር - በሬ ዶሮ ታርዶ፣
አንቺ ከእሳት ውስጥ- ከረመጥ ውስጥ ሆነሽ፣
እንጀራ እየጋገርሽ- ትታገይዋሇሽ፣
እሱም ኑሮ ሆኖ- ተመስገን እያልሽ፣
ሮሮ ሳታሰሚ - ደግ ቀን ጠበቅሽ፣
በጀርባሽ አዝሇሽኝ - ባንቀልባ ጠፍረሽ፣
Most of Ethiopians died from Yemen boat 
accident!!
 by ocean
 January 6, 2011 
ይህ ግጥም ከወያኔ አስጨናቂ ስርዓት ሲሰዱ 
ሇሕልፈተ ሕይወት ሇበቁት ኢትዩጵያዊን 
ወንድሞቼ እና እህቶቼ መታሰቢያ ይሁን!! እንደ ሕጻን ልጆች - ጫወታ ሳያምረኝ፣
እድሌ ከሆነ - እኔን ከዛ ያኖረኝ፣
ከሳቱ ዳር ሆነሽ - እኔን ከዛ አኑረሽ፣
እንጀራ እየጋገርሽ - ክቡን እየሰራሽ፣
አመዱን እየቃምኩ - አመድ እያበነንኩ፣
እሪ ብዬ ሳሇቅስ - ሃዘኔን በገሇጽኩ፣
አፌን በውሃ እያበስሽ - ካፈሩ እያጸዳሽ፣
ልክ እንደብርጭቆ - የምሰበር መስሎሽ፣
ከግምባሬ ስመሽ - ምርቃት መርቀሽ፣
በመሳሳት አይተሽ - እንትፍ እደግ ብሇሽ፣
ወፌ ቆመ ብሇሽ - እልል ብሇሽ ጮኸሽ
ምንድ ነው ተብሇሽ - ልጄ ቆመ ብሇሽ።
የኔ ብርቱካኔ - የኔ ሙዳይ ነሽ፣
የኔ ጨረቃዬ - ክዋክብቴ ነሽ፣
ሁሌ የማልረሳሽ - ከልቤ ያሇሽ፣
ብሶትሽ ብሶቴ ፣ ጭንቀትሽ ጭንቀቴ፣
ከተራራው ጀርባ ፣ ያሇሽው እናቴ::
መይሳው ከምድረ ስዊድን 
2013-07-15

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar