søndag 2. juni 2013

በአዲስ አበባ የተደረገው የዛሬው የተቃውሞ ሰልፍ በቪድዮ (UPDATE


የዛሬው ተቃውሞ 8 ጭቆና ይጥፋ ወኔ የሌለው የሀገር ሸክም ነው
የዛሬው ተቃውሞ 6 ኢትዮጵያ ሀገራችን
የዛሬው ተቃውሞ 5 መማር ያስከብራል ሀገርን ያኮራል
*የዛሬውን የተቃውሞ ሰልፍ ለማክሸፍ ኢህአዴግ ሌላ ስብሰባ ጠራ! *ለሙስሊሙ ህብረተሰብ አስቸኳይ ማሳሰቢያ ተላከ! EMF – ዛሬ ግንቦት 25 ቀን በጉጉት የሚጠበቅ እለት ነው። ባለፈው ሳምንት በመስቀል አደባባይ ሊደረግ የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ፤ በአዲስ አበባ አስተዳደር እና በሰማያዊ ፓርቲ ድርድር ለዚህኛው ሳምንት እንዲሆን ተደርጓል። እናም ዛሬ አዲስ አበባ በተቃውሞ ሰልፍ ቀውጢ ትሆናለች፤ ተብሎ እየተጠበቀ ነው። ሰማያዊ ፓርቲ የጠራውን የተቃውሞ ሰልፍ አንድነት እና መኢአድም ስለደገፉት የሌላ ፓርቲ አባሎችም ሊገኙ እንደሚችሉ ነው የደረሰን ዘገባ የሚያመለክተው። ሆኖም የተቃውሞ ሰልፉ የተጠራው ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንዲገኝ ስለሆነ፤ ከተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ውጪ ሌላው ኢትዮጵያዊ፤ በተለይም የሙስሊሙ ህብረተሰብ በብዛት እንደሚገኝ ከወዲሁ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
ወያኔ ኢህአዴግ ህዝቡ ወደ ሰልፉ እንዳይሄድ በየቀበሌው ቤት የሚፈልጉ ሰዎች እንዲመዘገቡ በተመሳሳይ ቀን፤ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ስብሰባ ጠርቷል። ይህም ሆኖ ህዝቡ ተቃውሞውን ለማሰማት ምንም እንደማያግደውና የተቃውሞ ሰልፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው፤ ብዙዎች አስተያየታቸውን እየሰጡ ያሉት።
የዛሬውን የተቃውሞ ሰልፍ ለማክሸፍ ኢህአዴግ ሌላ ስብሰባ የጠራበት ደብዳቤ ኮፒ!
የዛሬውን የተቃውሞ ሰልፍ ለማክሸፍ ኢህአዴግ ሌላ ስብሰባ የጠራበት ደብዳቤ ኮፒ!
ይህ በእንዲህ እንዳለ በተቃውሞ ሰልፉ ላይ ለሚወጡት ሙስሊሞች የሚከተለሉት አስቸኳይ መመሪያዎች በጽሁፍ ተላልፈዋል።

በጣም አስቸኳይ ማሳሰቢያ
ኢስላመን ብቻ የተመለከቱ መፈክሮችን ማስወገድ!!!
ነገ እሁድ በሚደረገው የጭቁን ኢትዮጵያውያን ዜጎች ሰላማዊ ሰልፍ ላይ፤ የሁሉም ሃይማኖት ተከታዮች አና የሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች አባላት የሚሳተፉ በመሆኑ፤ ኢስላምን ብቻ የሚመለከቱ ነገሮችን ማንፀባረቁ ምናልባትም የሌሎችን ፍላጎት የማይጠብቅ በመሆኑና የመንግስት ካድሬዎች ይህን በመጠቀም ህዝቡን እርስ በእርስ ለማጋጨት ሙከራ እንዳያደርጉ መንገድ ለመዝጋት፤ ዐረብኛ የሆኑ መፈክሮችን እና ሌሎች ኢስላመን ብቻ የተመለከቱ መፈክሮችን ማስወገድ አለብን፡፡ ነገ መባል ከሌለባቸው መፈክሮች መካከል፡- 1. አላሁ አክበር 2. ኢስላም ሰላም 3. አሻዕብ ዩሪድ ኢስቃጠል መጅሊስ 4. አሃዱን አሃድ 5. ላኢላሃ ኢለላህ እና ሌሎች በዐረብኛ የሚባሉ መፈክሮችን ማስወገድ አለብን በምትኩ ግን የሚከተሉትን መፈክሮች አጥብቀን ማስተጋባት ያስፈልጋል፡፡ 1. ህገመንግስቱ ይከበር 2. ኮሚቴዎቹ ይፈቱ 3. የታሰሩት ይፈቱ 4. ፍትህ ተጠማን፤ ፍትህ ተጠማን 5. መጅሊስ ይውረድ 6. ኢ.ቲ.ቪ ውሸታም 7. አቡበከር ይፈታ 8. አህመዲን ጀበል ይፈታ 9. ያሲን ኑሩ ይፈታ…. 10. መማር አልቻልንም፤ መማር አልቻልንም 11. ባገራችን ሰላም አጣን እና የመሳሰሉትን መጠቀም ያስፈልጋል:: በየአካባቢው ያለን ሙስሊሞች ከላይ በተጠቀሰው መሰረት በወረቀት እና በጨርቅ የየአቅማችንን መፈክሮችን አዘጋጅተን ብንመጣ የተሻለ ይሆናል፡፡ በተቻለ መጠን ይህ መረጃ ያልደረሳቸውን ሰዎች እንዲደርሳቸው በማድረግ፤ የተሳካ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገን፤ ኢስላማዊ አደብን በጠበቀ ሁኔታ አጠናቅን መመለስ ያስገልጋል፡፡ አላህ ያግዘን!!!!
ኢ.ኤም.ኤፍ ከአራት ሰአት በኋላ የሚደረገውን የተቃውሞ ሰልፍ እየተከታተለ ምቅረቡን ይቀጥላል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar