onsdag 5. juni 2013

ኢሕአግ በአውስትራሊያ


PDFPrintE-mail
Written by Administrator   
Tuesday, 04 June 2013 09:36
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በአውስትራሊያ ሜልበርን ሕዝባዊ ስብሰባ አካሄደ።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በውጭ አገር ካቋቋማቸው ቻፕተሮች መካከል የአውስትራሊያ ሜልበርን ቻፕተር አንዱ መሆኑ ይታወቃል።
ቻፕተሩ የኢሕአግን ሁለንተናዊ የአርበኝነት ትግል በማጠናከር በኩል ትልቅ ሚና እየተጫወተ የሚገኝ ከመሆኑም ባሻገር በአገረ አውስትራሊያ እና በሌሎች አገራት በሚገኙ ሚዲያዎች ተሳትፎ በማድረግና በፓልቶክ የግንባሩ ሰራዊት ለአገራችን ኢትዮጵያና ሕዝቧ እየከፈለ የሚገኘውን መስዋዕትነት በማስተዋወቅ ብሎም የቻፕተሩን አደረጃጀት ለማስፋት ለግንባሩ የሚደረገው እገዛ መሻሻል እንዲያሳይ ትልቅ ድርሻም ነበረው።
በግንቦት 25-2005 ዓ.ም በተካሄደው ስብሰባ የግንባሩን እንቅስቃሴ የሚያሳይ ፊልም ቀርቧል። የቀረበው ፊልም በተለይም በቻፕተሩ ሥር ሆነው ሲረዱ ለነበሩ አባሎች ትምህርት ሰጪና በውጭ አንድ አንድ ግለሰቦች ኢሕአግን አስመልክቶ ለሚያቀርቡት ማደናገሪያ ሐሳብና ውዥንብር ማስረጃ እንደነበርና በፊልሙም የተካተተው የግጥም መልዕክት ቀስቃሽና ለትግል የሚያነሳሳ እንደነበር ተሰብሳቢዎቹ አሥታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የውጪ ጉዳይ ሃላፊ የሆኑት አርበኛ መንግስቱ ወ/ሥላሴ የቻፕተሩ አመራሮች ካደረጉት ገለፃና ከቪዲዮ ፊልም ጎን ለጎን ግንባሩ በአሁኑ ወቅት እየሰራቸው ሥለሚገኙ ሥራዎች ማብራሪያ ከሰጡ በኋላ ከተስብሳቢዎቹ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል።
ተሰብሳቢዎቹ ኢሕአግ በተነሳበት ዓላማና ዓላማውን ለማሳካት እየተከፈለ የሚገኘው የጊዜ፣ የጉልበት፣ የእውቀት፣ የደም፣ የአጥንት እንዲሁም የሕይወት መስዋዕትነት ኢትዮጵያ አሁንም ጀግኖች አርበኞች እንዳሏት የሚያሳይ ታሪካዊ ተግባር መሆኑን ገልፀው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የውጪ ጉዳይ ሃላፊ የሆኑት አርበኛ መንግስቱ ወ/ሥላሴ ለተነሱ ጥያቄዎች የሰጡት ምላሽ አጥጋቢ እንደነበር ተሰብሳቢዎቹ አሥታውቀው፦ በመጨረሻም ወያኔ በልማታዊ መንግስት ሽፋን አገራችን መቀመቅ ውስጥ ለመክተት እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ለመግታትና አገዛዙን ለማስወገድ በዚሁ ሥብሰባ ዕለት የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።
ያደረጉት እገዛ ሕይወቱን እየከፈለ ከሚገኘው አርበኛ አንፃር ሲታይ እጅግ አነስተኛ መሆኑን ገልፀው ለወደፊትም ለግንባሩ የሚያደርጉት እርዳታ የሚጠናከር መሆኑንና ሌሎችም ለዚህ ታሪካዊ ኢትዮጵያን የመታደግ አካል የሆነው ድጋፋቸው ሌሎች ቻፕተሮችና ዜጎች እርዳታ እንዲታከልበት ከመቸውም ጊዜ በላይ በርትተው እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar