ሽማግሌው ስብሃት ነጋ ከጥቂት ቀናት በፊት በሰጡት ቃለ-ምልልስ አስበውት ይሁን ሳያስቡት “እውነት” አምልጧቸዋል። አጥብቀው ያነሷቸው የሙስና ጉዳዮች ራሱን የቻለ “አላማና ግብ” አላቸው። የመጀመሪያው በፓርቲያቸው ውስጥ ያለው ክፍፍል (የጥቅም) እንደተዳፈነ እሳት ውስጥ ለውስጥ እየተብላላ መሆኑን በግልፅ ያሳያል። ከተናገሩት የሚከተለውን እንመልከት፤ “በጤናማ ሁኔታ የሚገኙ ሰዎችን እንቆርጣለን፣ እናስራለን ወዘተ እያሉ ሲያስፈራሩ የነበሩ የፖለቲካ፣ የመንግስት ሰዎች ነን የሚሉ የፀጥታና የስነ አእምሮ ሁከት ፈጥረዋል። መቶ ሚሊዮን የሰረቁና ያስዘረፉ፣ 10ሺህ ብር የሰረቀውን ሲያገላብጡት ያታያሉ።” ብለዋል። « እንቆርጣለን » ያሉት መለስ ዜናዊ ናቸው፤ መለስ በአደባባይ ይህን ከመናገር አልፈው ሲያስፈራሩም እንደነበር እናስታውሳለን። መለስ ያንን ያሉት በ10ሺዎች የሚገመት ቡና ከመጋዘን ጠፋ በተባለበት ወቅት ነው። ያንን ቡና የሰረቁትና ባህር ማዶ ሸጠው ገንዙቡን ኪሳቸው የከተቱት አዜብ መሆናቸውን ከዚህ ቀደም ምንጭ ተጠቅሶ ይፋ ተደርጓል። እናም ስብሃት “መቶ ሚሊዮን የሰረቁ..» ያሉት አዜብ መስፍንን ሲሆን፣ « ያስዘረፉ» ያሉት ደግሞ ባለቤታቸው አቶ መለስን ነው። « 10ሺህ የሰረቁ..» የተባሉት በቅርቡ የታሰሩት የጉምሩክ ሰዎችን ሲሆን..እነዚህን በንፅፅር ያስቀመጡት የአዜብ (ተላላኪዎች) ስርቆት መጠነሰፊ መሆኑን ለማመላከት ነው። ስብሃት እስካሁን አድፍጠው ቆይተው በዚህ ሰሞን ይህን መናገራቸው ..« አዜብ የከተማዋ ም/ል ከንቲባ ይሆናሉ» የሚባለውን በመስማታቸው ሆን ብለው ያደረጉት ነው፥ ይላሉ ታዛቢዎች። በተለይ ሽማግሌውን በቅርብ የሚያውቋቸው የፓርቲው ሰዎች « ስብሃት ከበረሃ ጀምሮ በቀለኛ ነው። ጥርሱ ውስጥ የገባን ሰው ካላስወገደ እንቅልፍ አይወስደውም፤ ብዙ ሰው አጥፍቶዋል። አሁንም አዜብን እግር በእግር የሚከታተለው ለዚሁ ነው» ይላሉ። በማስከተልም ፥ « ሙስና ከተነሳ ስብሃትም እስከአንገቱ ተነክሮበታል። በገርጂና ሳር ቤት የሚገኘው <ሉሲ አካዳሚ > በአሜሪካ በሚኖሩ ስጋ ዘመዶቹ ስም እንዲሁም በቀድሞ የአየር ሃይል ጄ/ል ሰሎሞን ስም የሚንቀሳቀስ ግን የስብሃት የግል ንብረት መሆኑን የማይታወቅ መስሎት ነው?….ጎንደር -ሑመራ ያለው የሰሊጥ እርሻ የስብሃት አይደለም?…በ10ሚሊዮን ብር በሚገመት በመቀሌ (አፓርታይድ መንደር) ስብሃት ዘመናዊ ቪላ እንደሚገነባ አይታወቅም ብሎ ይሆን?…» ሲሉ እነዚህ ወገኖች የስብሃትን ሙስና በከፊል ይጠቅሳሉ።
ስብሃት በዚህ አላበቁም፤ « ..እስካሁን ከፍተኛ ሙሰኞች ትንሹን ሙሰኛ ከሰው አሳስረው ያስፈርዱና ያሰቃዩ ነበር ይባላል። ከፍተኛ ሙሰኞች ከመርማሪው ጀምረው አቃቤ ሕጉም ዳኛው፣ ምስክሩም ይቆጣጠራሉ። ትንሽ የሰረቀም ምንም ያልሰረቀም ሲሰቃዩና ሲያደኸዩ የነበሩም፤ አሉም ይባላል። ስልክ እየደወሉም ይፈርዱ ነበር ይባላል።» ብለው አረፉት ስብሃት። ትክክል ናቸው!! ዳኛ ብርቱካን ሚዴቅሳ « ይህን ካልፈረድሽ በመኪና ገጭተን ነው የምንገድልሽ » ተብላለች። ያውም ከቤተ መንግስት ተደውሎ። አባተ ኪሾ ከደቡብ ባጀት ተመላሽ የሆነ ሰባ ሚሊዮን ብር (70.000.000) ለመንግስት ተመላሽ ሊያደርጉ ሲሉ …« ወዲህ በል..የምን መንግስት ነው?» በማለት ተቀብለው ኪሳቸው የከተቱት አዜብ መሆናቸውን አባተ ፍ/ቤት ጭምር ያጋለጡት ነው። ስብሃት ነጋና መለስ ዜናዊ ደግሞ ታምራት ላይኔ በውሸት እንዲመሰክር አምስት ጊዜ አግባብተውት እንቢ ሲል ከማስደብደባቸው በተጨማሪ ሌላ ክስ እንዲመሰረትበት አድርገዋል። አቃቤ ሕግ የነበረው ዮሃንስ ወ/ገብርኤል የነስብሃትን የውሸት ክስ ተቀብዬ ተግባራዊ አላደርግም፤ ህሊናዬ አይቀበለውም .. በማለቱ ብቻ ለአምስት አመት እንዲታሰር አላደረጋችሁም?…ብዙ ማስረጃና መረጃ መደርደር ይቻላል።..
አሁን ስብሃት ተናገሩት እንጂ…ህዝቡ ብሎ-ብሎ የታከተው ነገር ነው!! እነ እስክንድር፣መሃመድ አቡበከር፣ አንዷለም አራጌ፣ ርእዮት አለሙ….ወዘተ በርሶ ጓደኞች በስልክ ትእዛዝ የተፈረደባቸው ናቸው!!… «ፍትሃዊ ስርአትና መንግስት አለ..» እያሉ ህዝብን የሚያደነቁሩት እነበረከትና የጋሪ ፈረስ የሆኑት ሃ/ማሪያም እርቃናቸውን የሚያስቀር ነገር ነው በስብሃት የተቀመጠው።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar