søndag 2. juni 2013

ኢህአዴግ ከምርጫ በፊት ለአዲስ አበባ

       ኢህአዴግ  ከምርጫ በፊት ለአዲስ አበባ
ከንቲባ መሰየሙ ተጠቆመ
የኢህአዴጋዊያን ከንቱ ጩኸት
28 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ኢህአዴግን
በጋራ ለመታገል የመግባቢያ ስምምነት
ሊፈራረሙ ነው        ፍኖተ ነፃነትን በሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን 
ድጋፍ በቅሩቡ ለህትመት ትበቃለች                                                                                                                                                        ፍኖተ ነፃነት በአጭር ጊዜ ውስጥ
ተወዳጅነትና ተመራጭነት
ካተረፉ ጋዜጦች የምትመደብ
እንደሆነች እናምናለን፤ ጋዜጣችን
በአስቸጋሪው የኢትዮጵያ
የብዙሃን መገናኛ ምህዳር
ውስጥ በቆየችባቸው ጊዜያት እኛ
በምንፈልገው ልክ የሚጠበቅባት
ሁሉ አድርጋለች ባንልም አማራጭ
የህዝብ ድምፅ በመሆን የበኩሏል
አስተዋፅኦ ማበርከቷ እሙን ነው፡፡
ኢትዮጵያን በአምባገነንነትና በማን
አለብኝነት የሚመራው ኢህአዴግ
እራሱ ያፀደቀውን ህገመንግስት
ማክበር ተስኖት ሀሳብን የመግለፅ
ነፃነት ማፈኑ በሀገራችን የነፃ ፕሬስ
ተግባር እንዲጠወልግ አድርጓል፡፡
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ
ፓርቲ ይህን አስቸጋሪ ሁኔታ
በመረዳት ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ
ከልሳንነት ባለፈ በሀገራች
ያለውን የሚዲያ ክፍተት
እንድትሞላ በማሰብ እንደ ነፃ
ፕሬስ እንድታገለግል በመወሰኑ
ጋዜጣዋ ለበርካታ ፓርቲዎች
ሀሳብ ማንሸራሸሪያ፣ ለወቅታዊ
ሀገራዊ ጉዳዮች በወያያ
እንዲሁም የተበደሉና ግፍ
የተፈፃመባቸው ዜጎች ብሶት
ማሰሚያ በመሆን አገልግላለች፡፡
በጋዜጣችን ተጋልጠው በአለም
አቀፍ ደረጃ ትኩረት ከሳቡ ክስተቶች
መካከል በ2004 ዓ.ም ከጉራፈርዳ
እንዲፈናቀሉ የተደረጉ ዜጎችን
ጉዳይ ለአብነት የሚጠቀስ ነው፡፡
መንግስት የፍኖተ ነፃነት ህትመት
እንዲቋረጥ ያደረገውም የጋዜጣዋ
የተፅእኖ አድማስ በማየሉ
ነው እንደሆነ አያጠራጥርም፡፡
ፍኖተ ነፃነትን የሚያስተዳድረው
ኤዲቶሪያል ቦርድ አንድነት
ፓርቲ በኦሮሚኛ ቋንቋም ልሳን
እንዲያሳትም ለማስቻል “ዳንዲ
ቢሊሱማ” የምትል የአሮሚኛ ጋዜጣ
ለማሳተም ዝግጅቱን አጠናቆ ነበር፡
፡ ከዚህ በተጨማሪም በንድፈሀሳብ
ላይ የምታጠነጥን ዳንዲ
የተሰኘች መፅሔትም ለማሳተም
ዝግጅት እየተደረገ ነበር፡፡
ጋዜጣችን በመንግስት በደረሰባት
አፈና ህትመቷ ቢቋረጥም በድረገፅ
www.fnotenetsanet.com ላይ
አሁንም መረጃዎችን በህዝብ
በማሰራጨት ላይ ትገኛለች፡፡
ሆኖም መንግስት በግልም ሆነ
በመንግስት ማተሚያ ቤቶች
ጋዜጣችንን እንዳናሳትም
ቢያደርገንም፣ ተስፋ
ቆርጠን አልተቀመጥንም፡
፡ አሁንም ፍኖተ ነፃነትን ዳግም
አንባቢዎቻችን እጅ ለማድረስ
የሚያስችል የገቢ ማሰባሰቢያ
መርሀ ግብር ተዘጋጅቷል፡፡
ይህ የገቢ ማሰባሰቢያ የሁሉንም
የህብረተሰብ ክፍል አቅም
ያገናዘበ እንዲሆን ጥረት
ተደርጓል፤በመሆኑም በሀገር
ውስጥም ሆነ በውጪ ሀገር
የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሁሉ
ለዚህ ሀገራዊ ጥሪ ቀና ምላሽ
እንደሚሰጡ እናምናለን፡፡ ፍኖተ
ነፃነት በሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን
ድጋፍ ዳግም ለህትመት
እንደምት በቃም እናምናለን፡፡


ከ   http://www.fnotenetsanet.com/wp-content/uploads/2013/02/fnote-newsletter-65.pdf

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar