‹‹ዳኞቹ እናንተ ናችሁ እኛ?›› ከዳኞቹ መካከል አንዱ ለአቃቤ ሕጎቹ ከተናገረው!
የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የክስ ሂደትን ታክኮ በአቃቤ ሕግና በዳኞች መካከል አለመስማማት መፈጠሩ ተነገረ፡፡ አለመስማማቱ የተፈጠረው አቃቤ ሕግ ለተደጋጋሚ ጊዜ በችሎት ውስጥ ከዳኞች ጭምር የበላይ መሆኑን ለማሳየት ጥረት በማድረጉ ነው ተብሏል፡፡ በዚሁ እያገባደድነው ባለው ሳምንት ተሰይሞ ምንም ሳያከናውን ተበትኖ በነበረው ችሎት ላይ አቃቤ ሕግ ቀድሞ ለፍርድ ቤት ሪጂስትራ ገቢ ማድረግ የነበረበትን ሲዲ እዚያው ለችሎቱ ገቢ ለማድረግ መሞከሩና ሲዲውን ገቢ ማድረግ የነበረበት ክሱ በተመሰረተበት ወቅት ማለትም (ከስድስት ወራት በፊት) ሆኖ ሳለ እስከአሁን ሳያስገባ መቆየቱ በዳኞቹና አቃቤ ሕጎቹ መካከል ፍጥጫ ጭምር እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል፡፡
ባለፉት ስድስት ወራት በነበሩት የችሎት ትእይንቶች በዳኞችና በአቃቤ ሕጎች ግንኙነት እንዲሁም የዳኞችን ሚና በመጫወት ላይ የሚገኙት አቃቤ ሕጎች መሆናቸውንና ይህም ምንም አይነት ፍትሀዊ አያያዝም ሆነ ፍርድ ከፍረድ ቤቱ ልንጠብቅ እንደማንችል በምንሰራቸው የችሎት ዘገባዎች ስንገልጽ መቆየታችን የሚታወስ ሲሆን አሁንም ይህ የአቃቤያን ሕጎች ከማንም በላይ ሆኖ በችሎት ለመታየት የሚያደርጉት ጥረት ዳኞችን ብስጭት ውስጥ ከትቶ ጠንካራ ቃላት እንዲሰነዝሩ ምክንያት ሆኗል፡፡ እንደ ፍረድ ቤት ምንጮች ዘገባ በእለቱ ችሎት መጀመር የነበረበት ከማለዳ 2፡30 ቢሆንም ዳኞች ፍረድ ቤት የደረሱት ከረፋዱ 4 ሰዐት ነበር ሆኖም አቃቤ ሕጎች ከዳኞች ጭምር በአንድ ሰዓት በመዘግየት ከቀኑ አምስት ሰአት መድረሳቸው የውዝግብ መነሻ ሊሆን ችሏል፡፡ ይህን መነሻ በማድረግም አንዱ ዳኛ ‹‹ዳኞቹ እናንተ ናችሁ እኛ?›› የሚል ንግግር የሰነዘሩ ሲሆን አቃቤ ሕግ የበላይ ሆኖ ለመታየት የሚያደርገውን ጥረት እንዲያቆምም ጠይቀዋል፡፡
ይህ አጋጣሚ በችሎቱ ውስጥ እንዲሁም በአጠቃላይ በፍትህ ስርአቱ ውስጥ ያለውን የአድልኦ አሰራር አመላካች የነበረ ሲሆን መንግስትም ንጹሀን ሰዎች ላይ የፈጠራ ወንጀሎችን በመደርደር ለማስወንጀልና ለማስፈረድ የማይቸገር መሆኑን አመላካች ነው፡፡ የአቃቤ ሕጎቹ በቂ ማስረጃ ሳይዙ በልበ ሙሉነት በፍርድ ቤቱ የበላይ ሆኖ ለመታየት የሚያሳዩት እብሪትም ከዚህ የመነጨ መሆኑን መታዘብ ይቻላል፡፡ ያለ አሳማኝ ምክንያት ችሎቱን በዝግ (ማንም እንዳይገባ በማድረግ) ማስኬድ፣ ለፍረድ ቤቱ ገቢ ሊሆኑ የሚገባቸውን ሰነዶች ገቢ አለማድረግ፣ የፍረድ ሂደቱን ማጓተት፣ ተከሳሾችን ማሳቀቅ፣ ከዳኞች የበላይ ሆኖ መታየት፣ ችሎት ላይ አርፍዶ መድረስ፣ የጠየቀውን ሁሉ ዳኞች እንዲቀበሉት ማድረግ እና የመሳሰሉት ከአቃቤ ሕግ በኩል ሲታዩ የነበሩ የፍትህ ስርአቱን አንካሳነት በጉልህ አመላካች የነበሩ ሂደቶች ናቸው፡፡
አላሁ አክበር!
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar