lørdag 29. juni 2013

በአዜብ መስፍን ላይ ምርመራ እንዲደርግ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ጥያቄዎችህ እየቀረቡ ነው::

እነመላኩ ፋንታን ተከትሎ በአዜብ መስፍን ላይ የሚቀርቡ የሙስና አቤቱታዎች ጨምረዋል::
የሙስና ኮሚሽን በአቶ ገብረዋህድ ቤት ባደረገው ፍተሻ እንዲሁም ከኣሁን ቀደም በመርማሪ
ደህንነቶች ክትትል በተደረገ የስልክ ጠለፋ የቀድሞ ሟች ጠ/ሚ ባለቤት እና በአለም ትልቁ
የሙስና አባት ኤፈርት ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ አዜብ መስፍን ከአቶ ገብረዋህድ ባለቤት እና
እህት ጋር በከፍተኛ ደረጃ የቢዝነስ ስራ ይሰሩ እንደነበር እና ከታሰሩት ባለስልጣናት እና
ባለሃብቶች ጋር የንግድ አጋርነት እንዳላት አረጋግጧል::ይህንን የሚጠቁሙ ሰነዶች እና
ከተለያዩ ወገኖች የሚቀርቡ ጥቆማዎች እና አቤቱታዎች ምርመራው ወደ አዜብ መስፍን
አምርቶ ለጥያቄ እንደምትፈለግ ፍንጭ እየሰጠ ነው ሲሉ የሙስና ኮሚጽሽን የውስጥ አዋቂ
ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል::ለሙስና ኮሚሽን ከደረሱት አቤቱታዎች ከፊሎ
ቹ :-ኤፈርትን ተገን በማድረግ የተለያዩእቃዎችን ካለቀረጥ እያስገባች ነው:: ኤፈርት ለመንግስት መክፈል የሚገባውን ህጋዊ የግብርም ሆነ ሌላ ክፍያዎች እንዳይፈጸም አድርጋለች::

ዩዲ ኒሳን ዲዝል ገልባጭ መኪኖችን ካለቀረጥ ነጻ በማስገባት በአቶ ከተማ ከበደ/ኬኬ/ ስም ሸጣለች::

ከዚህ ቀደም እያሱ በርሄ ጋር በኋላም ከኮሎኔል ሃይማኖት ጋር የተከለከሩ የቴለኮሚኒኬሽን ኬብሎችን

እና ቴክኖሎጊካል የመገናኛ መሳሪያዎችን ካለቀረጥ በማስገባት ሰርታለች::በነጻ ትሬዲንግ በኩል የተለያዩ

ዘመናዊ መኪኖችን ካለቀረጥ እያስገባች በአቶ ነጋ ገ/ዝጌር ስም ትሸጣለች::በሰበታ አለምገና አከባቢ

የአበባ ሰፊ እርሻዎች አላት :: በህገወጥ የዶላር እና የኢሮ ዝውውር ውስጥ መሪ ተሳታፊ ናት::

ባንክ ኦፍ ማሌዥያ እና የሲንጋፖር ባልሃብቶችን እንዲሁን ቻይናውያንን በህገወጥ አለማቀፍ

የገንዘብ ዝውውር ተባባሪ አድርጋ እየሰራች ነው::በተለያዩ አረብ አገራት እና በሃገር ውስጥ

ባስቀመጠቻቸው ደላሎች ኢትዮጵያውያን ሴቶችን በሱዳን እና በየመን አድርጋ ወደ አረብ አገራት ትሸጣለች:

:በተለያዩ የቤተሰብዋ አባላት ስም ባወጣችው የኮንስትራክሽን ንግድ ፍቃዶች ጨረታዎችን በጉልበት ከመቀማት

እየሰራሽ ሲሆን ሌሎች ባለሃብቶችን በስማቸው በመጠቀም የተለያየ ቢዝነሶችን እያካሄደች ነው የሚሉ አቤቱታዎች

እና ጥቆማዎች ለሙስና ኮሚሽን የመርማሪዎች ቡድን ደርሷል::

ይህንን ተከትሎ ጠንካራዎቹ የወያኔ አባላት በወይዘሮ አዜብ መስፍን ላይ ምርመራ እንዲደርግ

ግፊት እያደረጉ ሲሆን ወይዘሮዋ በአሁን ሰአት ራሳቸውን በተለያየ ምክንያት ገኖ ለማውጣት

ላይ ታች እያሉ መሆኑን ታውቋል::


http://www.ethiopianreview.com/

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar