søndag 2. juni 2013

እኛ ያልነው ለፉገራ...



ክንፉ አሰፋ
በሰሞኑ ቀልድ ልጀምር። የአፈሪካ ህብረት ድርጅት 50ኛ አመቱን በያዝነው ሳምንት በአዲስ አበባ
ሲያከብር በነበረው የሻምፓኝ ስነ-ስርዓት ላይ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ብቻ ከመሪዎቹ ተነጥለው ያለ
ብርጭቆ ቆመዋል። ለፕሮቶኮል እንዲመሳሰሉ ቢጠየቁ አሻፈረኝ አሉ። የህብረቱ የወቅቱ ሊቀመንበር
ስለነበሩ ለይሰሙላ እንኳን ብርጭቆዋን ጨብጡ ቢባሉ አይሆንም፣ ሃይማኖቴ አይፈቅድም አሉ።
በመጨረሻ ግን በረከት ስምዖን በጆሯቸው አንዳች ነገር ነገራቸውና የያዘውን ብርጭቆ ሲሰጣቸው
ተቀብለው በደስታ ጨለጡት።
በረከት ለጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ በጆሯቸው እንዲህ ነበር ያላቸው። "ብርጭቆ ውስጥ ያለው
መለስ የጀመረው ወይን ነው።"
አሁን አሁን መቀለጃ እየሆኑ የመጡት ሃይለማርያም ደሳለኝ፤ መለስ የጀመረውን ሁሉ፤ ፉገራም
ቢሆን - ያንን ለመጨረስ ነው የተቀመጥኩት ይሉናል። እየደጋገሙ!

***
ብርኖ በምትባል የቼክ ሪፐብሊክ ትንሽ ከተማ ከነበርኩበት ሆቴል ውሰጥ የተሰቀለ ቲቪ
ካለወትሮው የ'ሕዳሴውን' ግድብ የሚያሳይ ምስል ይዞ ብቅ አለ። የምሽት ዜና ትንተና መሆኑ ነው። በቼክ
ቋንቋ ይተላለፍ የነበረው የዜና ትንተና ባይገባኝም ከምስሉ የመልእክቱን ይዘት ለመረዳት አላስቸገርኝም።
ግን ምን አዲስ ነገር ተገኘ?
የቲቪውን ጣቢያ መቀያየር ጀመርኩ። ሲ.ኤን.ኤን፣ ቢ.ቢ.ሲ.፣ አል ጃዚራ...ቪ.ኦ.ኤ.። የኳታሩ አል
ጃዚራ ጉዳዩን በስፋት ይዞታል። Death on the Nile(በአባይ ላይ ግድያ) በሚለው አምዱ ምሁራንን እና
ባለስልጣናትን እያቀረበ ስለ 'ሕዳሴው' ግድብ ያወያያል። በአሜሪካን መንግስት በሽብርተኝነት የተፈረጀው
የግብጹ ሱኒ 'አል ጋማ አል ኢስላሚያ' ድርጅት ደግሞ ኢትዮጵያን በጦር ለመውጋት ዝግጁ መሆኑን
ባለፈው ረቡዕ አውጇል።
ሂደቱ እንደገና ሌላ ጥያቄ አጫረብኝ። የግድቡ ወሬም ሆነ ስራ ከተጀመረ ሁለት አመት ሊሞላው
ነው። ዓለም አቀፉ ሜዲያና ዘራፍ ማለት የጀመሩት ቡድኖች ዛሬ ያባነናቸው ምስጢር ምንድነው?
አመቱን ሙሉ የት ነበሩ? መልሱን የምናውቀው እኛ ባለቤቶቹ ብቻ ነን። በእርግጥ አቶ መለስ የአባይ
ካርድን ይዘው ይጫወቱት የነበረውን ጨዋታ ግብጾች ጠንቅቀው ያውቁት ኖሮ የ'ሕዳሴው'ን ሽርጉድ
ከቁብ አልቆጠሩትም ነበር።
ከሁሉም ነገር እንግዳ የሚሆነው፣ በየመገናኛ ብዙሃን እየቀረቡ አስተየት የሚሰጡ የፈረንጅ
'ምሁራን' ጉዳይ ብቻ ነው። እነዚህ ተመራማሪዎች ስለ አባይ፣ ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ፣ ስለ ኢትዮጵያ
ፖለቲካ...ወዘተ ሊቅ ሆነው የተሳሳተ ግምታቸውን እያቀረቡ ሌላውንም ግራ ያጋቡታል። ስለ ግድቡ
በአልጃዚራ አስተያየት ትሰጥ የነበረችዋ ኤክስፐርትም ሂደቱን 'ብቀላ' እንደሆነ ገልጻዋለች። ሌላውም
እንዲሁ 'የሕዳሴው ግድብ' ጦርነት እንደሆነ ገልጿል። የአካባቢ ጥበቃ፣ ኤኮሎጂ... ወዘተ ችግር ያስከትላል
1 | ገ ጽየሚሉም አሉ። ሁሉም አስተያየቶች ግን ከኛ ከሃገሬው አመለካከት የራቁና ከመላምት ያለፉ አይደሉም

http://www.ethiomedia.com/abc_text/egna_yalnew_lefugera.pdf






Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar