mandag 10. juni 2013

አንድነት ፓርቲ የሰኔ 1 ሰማዕታትን በልዩልዩ ዝግጅቶች ዘከረ

ሰኔ 1 ቀን 1997 ዓ.ም በመንግስት ሀይሎች በግፍ የተጨፈጨፉ የሰላማዊ ትግል ሰማዕታትን ለመዘከር አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የአዲስ አበባ ዞን ያዘጋጀው መርሀግብር  ተካሄደ፡፡ቀበና አካባቢ በሚገኘው አንድነት ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት ሰማዕታቱን ለማሰብ በህሊና ፀሎት በተጀመረው በዚሁ መርሀ ግብር ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ሲሆኑ ከሳቸው በመቀጠል የአንድነት ፓርቲ አዲስ አበባ ዞን ሰብሳቢ አቶ ትዕግስቱ አወሉ ዕለቱን የሚመለከት ንግግር አድርገዋል፡፡ ከ300 በላይ ታዳሚዎች በተሳተፉነት በዚህ መርሀግብር ላይ ዕለቱን የተመለከቱ ግጥሞች በገጣሚ መላኩ ጌታቸው ቀርበዋል፡፡ የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ነብዩ ኃይሉ ዕለቱን አስመልክቶ የነበረውን ትዕውስታ ለታዳሚው አካፍሏል:: የመርሀግብሩ አዘጋጆች ሰኔ አንድ በግፍ ከተገደሉ ዜጎች መካከል 42 የሚሆኑትን ስምና የአገዳደል ሁኔታ በመቀንጨብ አቅርበዋል፡፡ የታሳሪዋ ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ አባት አቶ አለሙ ጌቤቦ የመዝጊያ ንግግር ካደረጉ በኋላ በቅርቡ በማዕከላዊ ታስሮ ድብባና እስር ሲፈፀምበት በነበረው ወጣት ብርሀኑ ተክለያሬድ የተመራ የጧፍ ማብራት ስነስርአት ተካሂዶ መርሀግብሩ ተጠናቋል፡፡
DSCN1104[1]
1001470_557749090950511_1006081520_n
7257_557749314283822_937208926_n
576761_557751617616925_1151369897_n
10815_557752310950189_307058353_n
994778_557753037616783_47495989_n
7453_557753630950057_1533403386_n
954844_557753794283374_196247027_n
945129_557753444283409_199810143_n
8508_557753970950023_1070795258_n
942010_557754114283342_2018800660_n
988663_557754417616645_1881988758_n
1003985_557754257616661_1596317244_n

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar