torsdag 23. mai 2013

የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባኤ የአቋም መግለጫ


ግንቦት ፲፩/ ፪ሺ፭ (19th May 2013)
የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላላ መንፈሳዊ
ጉባኤ፤ ከእዚህ በፊት የቤተ ክርስቲያኗን አስተዳደር አቋም፣ የውስጥ መተዳደሪያ ደንብና ትረስት ዲድ በሚመለከት
ያሳለፋቸው ውሳኔዎችና መግለጫዎች ሙሉ በሙሉ እንደተጠበቁ ሆነው፤ የቤተ ክርስቲያናችንን ችግር ለመፍታት
በሚደረገው ጥረት ውስጥ የተከሰቱ፣ የተሳሳቱ መረጃዎችንና መግለጫዎችን ለማስተካከል፤ ጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባኤው
የሚከተለውን የአቋም መግለጫና ማብራሪያ አውጥቷል።

1) የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ
ግንኙነቷ አዲስ አበባ ከሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ሲሆን፤ አስተዳደሯ ግን በቃለ ዓዋዲው፣ በ2006 ባወጣችው
ደንብ፣ በተሻሻለው ትረስት ዲድና በእንግሊዝ ቻሪቲ ሕግ መሰረት (አስተዳዳሪን ጨምሮ) በምትመርጣቸው
የሰበካ አስተዳደር ጉባኤ አባላት ወይም ባላደራዎችና ልዩ ልዩ ንኡንስ ኮሚቴዎች አማካኝነት/መሰረት ብቻ፤
ያለማንም የውጪ አካል ጣልቃ ገብነት ራሷን ችላ ትተዳደራለች። የቤተ ክርስተያኗም ንብረት አስተማማኝ በሆነ
መንገድ ለመጪው ትውልድ ለማቆየት በሚያስችል መንገድ፤ የቤተ ክርስቲያኗ አባላት ብቻ በሚያጸድቁት
ደንብ/ሕግ መሰረት ይያዛል፣ ይጠበቃል።
2) የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የአስተዳደር መሰረቶች፤ በ2006 ዓ.ም.
የጸደቀው፤ የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ፣ ትረስት ዲድና ከእዚህ በፊት የጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባኤው ያወጣቸው
የአቋም መግለጫዎችና በእዚህ ሰነድ በተራ ቁጥር አራት ላይ በተጠቀሰው መሠረት ተሻሽለው፤ በጠቅላላ
መንፈሳዊ ጉባኤው የሚጸድቁ የውስጥ መተዳደሪያ ደንቦች፣ የትረስት ዲድስ፣ የአቋም መግለጫዎችና ውሳኔዎች
ብቻ ናቸው።
3) የመንበረ ጵጵስና ሀገረ ሰብከትን በሚመለከት፤ ቤተ ክርስቲያኗ ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ የምትመራበትና
የምትተዳደርበት የውስጥ ደንብ በሚያዘውና ቤተ ክርስቲያኗ ባወጣችው የአቋም መግላጫ መሠረት በመሆኑ፤
አሁን ተቋቁሟል በተባለው “የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት” ውስጥ፤ የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ
ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ምንም ዓይነት ተሳትፎና ግንኙነት ስለሌላት፤ ለሀገረ ስብከቱ እውቅና
አትሰጥም። ለወደፊት ከሀገረ ስብከት ጋር የሚኖራት ግንኙነት የቤተ ክርስቲያኗ አባላት ተነጋግረው የሚወስኑት
ጉዳይ ነው።
4) የቤተ ክርስቲያኗ የውስጥ መተዳደሪያ ደንብና ትረስት ዲድ፤ ጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባኤው በ 14/04/2013
ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት፤ አሁን ባሉት አርቃቂ ኮሚቴ አስረጅነትና በተቋቋመው ገለልተኛ አወያይ ኮሚቴ
መሪነትና ሊቀ መንበርነት፤ በአዲሱ የሰበካ አስተዳደር ጉባኤ አስተነባባሪነት፤ ተጠናቆ ሲጸድቅ ሌላ አዲስ የሰበካ
አስተዳደር ጉባኤ (ባላደራዎች) ይመረጣል።
5) አሁን በቤተ ክርስቲያናችን ውሰጥ የተከሰተው ችግር፤ የሃይማኖት/እምነት ችግር ሳይሆን የአስተዳደር ችግር
ስለሆነ፤ ከላይ በተራ ቁጥር አንድ በተጠቀሰው መሠረት ለችግሩ መፍትሔ የሚሰጡት የቤተ ክርስቲያኗ አባላት
ብቻ ስለሆኑ፤ ቅዱስ ሲኖዶሱም ሆነ ቤተ ክርስቲያኗ እውቅና የማትሰጠው “ሀገረ ስብከት” ችግሩን ለአባላቶች
በመተው የቤተ ክርስቲያኗ አባላት በውስጥ ደንባችንና በእንግሊዝ ሀገር የቻሪቲ ሕግ መሠረት እንድንፈታው
ይሆን ዘንድ በትህትና እያሳሰብን፤ ጸሎታቸውና ቡራኬአቸው ግን እንዳይለየን እንጠይቃለን።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar