የወያኔ ታማኝ ሎሌ የሆነዉ ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ባለፈዉ ሳምንት የፓርላማ ዉሎዉ 40 በ 60 የተባለውን የቤቶች ልማት ፕሮጀክት አስመልክቶ ለቀረበለት ጥያቄ የሰጠዉ ምላሽ ከዚህ ቀደም ባልተለመደ መልኩ ከዚህ ቀደም ከሳቅና ጭብጨባ ዉጭ ሌላ መቃወም የሚባል ነገር የማያዉቀዉን የወያኔ ፓርላማ ማስቆጣቱ ተሰማ፡፡ ኃይለማርያም ደሳለኝ ይህ እንግዳ የሆነ ተቃዉሞ የገጠመዉ የ2005 በጀት ዓመት የስምንት ወራት ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት ሲሆን የፓርላማዉ አባላት 40 በ 60 የሚባለው የቤት ልማት መቶ በመቶ የመክፈል አቅም ላላቸው ሰዎች ቅድሚያ ይሰጣል የመባሉን ጉዳይ እርግጠኛ ስለመሆኑ ለጠየቀዉ ጥያቄ አዎንታዊ መልስ በመስጠቱ ወይም መቶ በመቶ የመክፈል አቅም ላላቸው ቅድሚያ እንደሚሰጥ በማረጋገጡ ፓርላማዉ በተቃዉሞ ድምፅ ሲሞላ ተስተዉሏል።
ለወያኔ ፓርላማ ቅርበት ያላቸው ምንጮች የፓርላማዉ አባላት ለምን አለወትሯቸዉ ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ላይ እንዳልጎመጎሙ ተጠይቀው በሰጡት መልስ ቀደም ሲል ፕሮግራሙን በተመለከተ ለፓርላማው በቀረበዉ ሪፖርት 40 በ60 የሚባለው ፕሮግራም መካከለኛ ገቢ ያለውን በተለይም በደሞዝ የሚተዳደረውን የህብረተሰብ ክፍል ይጠቅማል ተብሎ መነገሩንና ሆኖም በዕቅድ ደረጃ ለባለአንድ ክፍል መኝታ ቤት 857 ብር፣ለባለሁለት መኝታ ቤት 1 ሺ 337 ብር፣ ለባለሶስት ምኝታ ቤት ደግሞ 2 ሺ133 ብር ለአምስት ተከታታይ ዓመታት በየወሩ መቆጠብ እንዳለበት መታቀዱ የመካከኛ ገቢ ያለውን የህብረተሰብ ክፍል አቅም ያገናዘበ አይደለም የሚል ቅሬታ በፓርላመዉ አባላት ዘንድ በቅሬታ መልክ በተደጋጋሚ ይነሳ እንደነበረ አስታውሰዋል፡፡
በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ መካከለኛ ገቢ አለው የሚባለው በተለይም የመንግስት ሰራተኞች አማካይ ወርሃዊ መካከለኛ ገቢ ከ2 ሺ 500 ብር እንደማይበልጥ ምንጫችን ጠቅሶ ከዚህ ደመወዝ ላይ ዝቅተኛውን በወር 857 ብር መቆጠብ እንዴት ይቻላል ሲል የወያኔን ግራ የሚያጋባ አሰራር ገና ሳይጀመር ጥያቄ ዉስጥ የገባ አሰራር ነዉ ብሎታል፡፡ በዚህ ምክንያት የ40 በ60 የቤት ልማት ፕሮግራም መካከለኛ ገቢ ላላቸዉ ሰዎች ይዘጋጅ እንጂ እካሁን ድረስ እየጠቀመ ያለዉ ከፍተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ነዉ፤ ይህንን ደግሞ ኃ/ማሪያም ደሳለኝም ፓርላማ ዉስጥ ባደረገዉ ንግግር አረገግጦታል ብሏል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ጠ/ሚኒስተር ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ቢሮ አማካይነት በተደረገው ጥናት ለውጪ ኩባንያዎች ዝግየሆነውን የሸቀጦች ችርቻሮ ንግድ ስራ ለመፍቀድ ወይ ሌሎች አማራጮችን ለማየት መሞከሩን የኢሳት ቴሌቭዥንና ሬድዮ ዘጋቢ ጠቅሶ ይህ ነገር ግን ትልልቆቹ ኩባንያዎች በሸቀጦች የችርቻሮ ንግድ እንዲሰማሩ ቢደረግ የአገር ውስጥ አስመጪዎች በአጭር ጊዜያት ውስጥ ከገበያ ውጪ በማድረግ መንግስት ሊቆጣጠረው የማይችለው ገበያ ሊፈጠር ይችላል የሚል ስጋት በመኖሩ በመንግስት ቁጥጥር ስር ሆኖ ዋጋ የማረጋጋትና አነስተኛ ዋጋ ካላቸው ገበያዎች ሸቀጦችን በመግዛት በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያቀርብ ኢንተርፕራይዝ እንዲቋቋም ውሳኔ ላይ ተደርሶአል፡፡http://www.ethiosun.com/2013/04/
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar