torsdag 9. mai 2013

ዴሞክራሲያ


ዴሞክራሲያ ልዩ ዕትም መጋቢት /ሚያዚያ 2005 
ቀን የሰጠው ቅል ድንጊያ ይሰብራል፤
የወያኔ የክፍፍል ፖሊቲካና መዘዙ
በቅርቡ ከቤኒሻንጉልና መተከል ክልል የአማራ ብሔር ተወላጆች በወያኔ ባለሥልጣናት በግፍ
መባረራቸውን ተከትሎ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፤ የውጭ መንግሥታትና
የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ከፍተኛ ተቃውሞና ወገዛ ሲያደረጉ መቆየታቸው ይታወቃል። ይህ በአማራ
ዜጎቻችን ላይ የደረሰው ግፍና በደል ብዙ ቁጣና ቁጭት የቀሰቀሰ ከመሆኑ ባሻገር ወያኔ ሥልጣን ከያዘ
ጀምሮ እየተከተለ ያለው የክፍፍልና ሀገር የማጥፋት ፖሊሲ በኢትዮጵያዊነት ላይም ሆነ በአገር
ሉዓላዊነትና በሕዝብ አንድነት ላይ እየፈጠረ ያለው ጠንቅና መዘዝ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን
የሚያመላክት ሆኗል። ባለፉት 20 ዓመታት ወያኔ በፈጠረው የጎሳ ፖለቲካ እንዲሁም ቋንቋንና
ብሔረሰብን መሠረት አድርጎ በተዋቀረ ክልል ምክንያት በብዙ መቶ ሺ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን
ህይወታቸውን ማጣታቸው፤ ከቤት ንብረታቸውና ከቀያቸው መፈናቀላቸውና መሰደዳቸው ታሪክ
የመዘገበው ነው። ሁሉንም መዘርዘር ባይቻልም የተወሰኑትን ለአብነት መጥቀስ ይቻላል። በአርባጉጉ ፤
በበደኖ፤ በአሰቦት፤ በአሶሳ አማሮች ተጨፍጭፈዋል፤ ከቤት ንብረታቸው ተባረዋል። ከባሌ ከአርሲና
ከሐረር የአማራውም ሆነ የሌሎች ብሔረሰብ አባላት ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። ከጋምቤላ አማሮችን
ለማስወጣት ሙከራ ተደርጓል።
ደቡብ ውስጥ በጉጂና በጌዲዮ፣ በጉጂና በቦረና ፣ በቦረናና በገሪ መካከል
ግጭቶች ተፈጥረዋል፤ የሲዳማ ብሔረሰብ በደቡብ ክልል ውስጥ መጠቃለሉን ተቃውሟል፤ የስልጢ
ብሔረሰብም ጉራጌ አይደለንም በማለት የመገንጠል እንቅስቃሴ አድርጎ ተግባራዊ ሆኗል፤ ከደቡብ ክልል
ቢንች ማጂ ዞን ከጉራፈርዳ ወረዳ አማሮች ተባረዋል፤ ሐረር ውስጥ በሐረሪና በኦሮሞ መካክል ግጭት
ተፈጥሯል ፤ በአሶሳ በበርታ፣ በኦሮሞና በአማራ ብሔረሰቦች መካከል በተለያየ ጊዜ ግጭት ተቀስቅሶ
በርካታ ስዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ወዘተ… ወዘተ….። ለዚህ ሁሉ ምስቅልቅል ሁኔታ ምክንያትና
ምንጩ የወያኔ የክፍፍል ፖለቲካና አለተቀናቃኝ በሥልጣን ላይ ለረጅም ጊዜ ለመቆየት የቀየሰው ቋንቋንና
ብሔረሰብን መሠረት ያደረገው የክልል ፌዴሬሽን ነው። ይህ የክፍፍል ፖሊሲ የኢትዮጵያን የረጅም ጊዜ
ታሪክ የሚክድ ሲሆን አገሪቷ በ1982 ዓ.ም. የተለያዩ ብሔረሰቦች አድቦልቡለው የሠሯት ግን በማናቸውም

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar