አቶ ኣስገደ ገ/ስላሴ ወ/ሚካኤል የቀድሞ የህወሃት አባል ነበሩ። ከክፍፍሉ በኋላ የህወሃት ተቃዋሚ ሆነው፤ በአረና ትግራይ ፓርቲ ውስጥ በስራ አስፈጻሚነት በመስራት ላይ ናቸው። ብስራት አማረ የተባለውን የቀድሞ ደህንነት አባል ስም አጥፍተሃል” ተብለው ለሁለት አመታት ሲታሰሩና ሲፈቱ ቆይተው፤ ከጥቂት ወራት በፊት ፍርድ ቤት በነጻ ለቋቸዋል። አሁን ደግሞ ልጃቸው ታስሮ እየተሰቃየ ነው። ወላጅ አባቱና የቀድሞው የህወሃት አባል አቶ ኣስገደ ገ/ስላሴ ወ/ሚካኤል እንዲህ በማለት የሆነውን ሁሉ ይገልጻሉ – ከመቐለ።
“መከራው ከእኔ ኣልፎ ልጄም ስቃይ ወራሽ ሆነ” በማለት ይጀምራሉ አቶ ኣስገደ ገ/ስላሴ ወ/ሚካኤል።
የ26 አመቱ ወጣት ልጄ ኣሕፈሮም ኣስገደ ገ/ስላሴ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምሩቅ ሲሆን ስራው ደግሞ ኮምፕዩተር “ኔትወርክ” እና “ሃርድዌር ሜንተናንስ” ያጠቃልላል።
ይህ ልጅ ከ 4ወር በፊት በኣንድ ካፌ ቡና እየጠጣ እያለ ሁለት ሲቪል ሰዎች እንፈልግሃለን ኣሉት። እሱም ሰላማዊ ሰዎች መስለዉት ተነስቶ ሲሄድ በማይስማ መንገድ ቀጥ ብለሀ ወደ ወሰድንህ ሂድ ብለው ወደ ትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ወስደው ለኣንድ ቀን ኣስረው ደብቀዉት ዋሉ።
ማታ በጨለማ በመቀሌ ምስራቃዊ ኣቅጣጫ ከ ባሎኒ ኣለፍ በሎ የሚገኘው ጎድጓዳ ኣካባቢ ከእንዳየሱስ ቤተክርስትያን በስተ ምዕራብ ከኣሪድ ዩንቨርስቲ ግርጌ የሚገኝ ድብቅ እስርቤት ወይም በመቀሌ ህዝብ ኣነጋገር ቤርሙዳ እይተባለ የሚጠራ በትግራይ ባለስልጣኖች ደሞ 06 (ባዶ ሽዱሽተ) የሚባል ስም ያለው ለኣራት ቀን ያህል ገርፈው ጀርባውን በምን እንደመቱት የማይታወቅ ቆስሎና በስብሶ መጣ።
በዛን ወቅት “ምን ሆንክ?” ብለን ብንጠይቀው ወድቄ ነው ኣለ። እኛም ግርፋት ወይም ቶርች እነደሆነ ተረድተናል። የኋላ ኋላ ግን ቀስ ኣድረገን ጠይቀነው ግን የደረሰብኝ እንዳልነግራችሁ መርማሪዎቹና ሃላፊዎቹ ገርፈዉኛል በለህ ከተናገርክ ህይወትህን እናጠፋታለን እንዳሉትና ለወላጆቹ ኣለመናገሩ ሰግቶ መሆኑ ገልፆልናል። እኛም በግልፅ ኣቤት ለማለት ግዜ ኣልፏል ብለን ችላ ብለን ቆየን፤ መሆን ግን ኣልነበረበትም ልጄም በሰላም ስራው እየሰራ ነበር፡፡
የኣሁኑ ይባስ ልጄ በ 16/8/2005 ዓ.ም ዕለተ ሮብ በኣምስት ሰኣት ላይ ከስራ ወጥቶ ቡና እየጠጣ እያለ ፖሊሶች መጥተው ኣስረው በቀዳማይ ወያኔ ወረዳ ፖሊስ ጣብያ ኣስገቡት፤ መታሰሩ ሰምተን ስንጠይቅ መጀመርያ የለም ኣሉን። ቆየት በለው ግን ኣለ ግን ልታገኙት ኣትችሉም ኣሉን። የምወስድለት ምግብም ፖሊሶች ተቀብለው ይወስዱታል፤ ይብላው ኣይብላው ኣናውቅም። በህገመንግስት ድንጋጌ መሰረት ኣንድ ተጠርጣሪ በፖሊስ ሲያዝ የፍርድ ቤት ትእዛዝ መኖር ኣለበት። 2ኛ ከፖሊስ ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ በ48 ሰኣት ውስጥ ወደ ፍርድ ቤት መቅረብ ነበረበት ይህ ግን እስካሁን በ120 ሰኣታት ፍርድ ቤት ሳይቀርብ ለምን ልጃችን አታገናኙንም? ከጠበቃም ይገናኝ እያልን ስንጠይቅ ኣናሳይም በማለት ከልክለውን ሰንብተዋል። ኣሁን ግን ልጃችን ከዛ ህጋዊ ህዝብ የሚያውቀው ፖሊስ ጣብያ ኣውጥተው ደብቀዉታል። ወደ ህጋዊ ያልሆነ ድብቅ እስርቤት ወስደው የስቃይ ምርመራ ይፈፅምበታል የሚል ጭምጭምታ ሰምተን ወደ ታሰረበት ወረዳ ፖሊስ ጣብያ ሄደን ስንጠይቅ ታችኞቹ ፖሊሶች “የለም ከዚህ ልቀቁ” ኣሉን። እኛም ተስፋ ሳንቆርጥ የወረዳ ፖሊስ ጣብያ ዋና ኣዛዠ ኮሎኔል ኣንድነት “ልጄን የት ወሰዳችሁት?” ብየ ስጠይቀው “ወደ 06 ሄዷል” ይላል። “የት ነው 06?” ስለው ለክልል ፖሊስ ኮሚሽን ጠይቅ፤ ብሎኛል ሃይለ ቃል በተሞላው።
“ለመሆኑ በመቀሌ ከሚገኙት 7 ወረዳ ፖሊስ ጣብያ ውጭ 06 የሚባል እስር ቤት ህጋዊ የመንግስት እስር ቤት ኣለ እንዴ?” ብየ ጠየቅኩት። ኮሎኔል ኣንድነት ግን እጅግ በመናደድ “ስማ እስገደ ለራስህ ባያዝድ ሆነህ /ተበክለህ/ በዚህ ላለው ሰው ኣትበክልብን! ተጠንቀቅ” ኣለኝ፡፡ ለዚህ ኣባባል ብዙ ማስረጃዎች ባሉበት በኮሎኔል ኣንድነት የደረሰብኝ ማስፈራራትና ዛቻ ነው ጉዳዩ እንደዚህ እያለ ልጄ ምክንያቱ ባልታወቀ ከከተማ ወጣ ያለ ድብቅ እስርቤት ተወስዶ ሁኔታው ባለማወቃችን በጭንቀት ላይ እንገኛለን።
የተከበራችሁ ሃገር ወዳጅ ዜጎች እኔ ህውሓትን በመቃወሜ፤ በተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ ተደራጅቼ በመታገሌ የህውሓት የትግል ታሪክ ጋህዲ አንድ፣ ጋህዲ ሁለት እና ጋህዲ ሶስት እንዲሁም ሌሎች ፅሁፎች በመፃፌ በስም ማጥፋት ሰበብ ተከስሼ ለሁለት ኣመት እየታሰርኩ እየተፈታሁ እስካሁን እየተንገላታሁ እንደምገኝ ሁሉም የሚያውቀው ነው፡፡
በጣም የሚያሳዝነኝ ግን የህውሓት ኢህአደግ ስርኣት መሪዎች የሚወስዱት እርምጃ ከወላጆቹ ኣልፎ ለልጅ የሚያልፍ ቂም በቀል መስራታቸው ነው። የዚህ ልጅ መታሰር ከኣሁን በፊት ኣስረው የገረፉበት ምክንያት “የኣስገደ ፀረ-መንግስት የሆኑ ፅህፎች የምትሰራ ኣንተ ነህ” በሚል እንደገረፉት ልጄ ራሱ የሚያረጋግጠው ነው፡፡
በመጨረሻ ልለው የምፈልገው ይህ ተግባር የሃገራችን በሚሊዮኖች ዜጎች መስዋእት የተረጋገጠ ህገመንግስት መናድና የህግ የበላይነት ኣለመኖሩ በተጨባጭ ያረጋገጠ እኔ ስለ ልጄ ኣሁን በደረሰብኝ ችግር ብቻ ኣይደለም እየተናገርኩት ያለሁት በኣጠቃላይ ልክ እንደ ልጄ በሌሎች ዜጎች እየደረሰ ያለው ሰቆቃም ይቁም እላለሁ፡፡
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar