mandag 20. mai 2013
የምዕራብ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ በቅዱስ ሲኖዶሱ ታገዱ
--- እግዱ ከሙስና ጋር የተገናኘ ነው
---- ‹‹ሙስናው በአንድ ሀገረ ስብከት ብቻ አይደለም›› አገልጋዮች
ፀረሙስና ኮሚሽን የባለስልጣናትን የሀብት
ዝርዝር ላለማሳወቅ እያንገራገረ ነው
ብፁዕ አቡነ ሕዝቄል
የፌደራል ስነ ምግባርና የፀረ ሙስና
ኮሚሽን የባለስልጣኖችን የሀብት በዝርዝር
ይፋ ለማድረግ ማመንታቱ በፓርላማ
መነጋገሪያ ሆነ፡፡
የፌደራል ስነ ምግባርና የፀረ ሙስና
ኮሚሽን ኮሚሽነር አሊ ሱሌማን ባለፈው
ሳምንት ግንቦት 6 ቀን 2005 ዓ.ም
ለፓርላማ ባቀረቡት የ2005 በጀት
የአስር ወር የዕቅድ አፈፃፀም ባቀረቡበት
ወቅት የመንግስት ባለስልጣናትን ሀብት
በዝርዝር ይፋ ለማድረግ ማመንታታቸው
አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ ኮሚሽነሩ ባለፈው
አመትም ተመሳሳይ ሪፖርት ሲያቀርቡ
“በቅርቡ የመንግስት ባለስልጣናትን ሀብት
በዝርዝር ይፋ እናደርጋለን” ቢሉም
በያዝነው አመትም ይፋ አለመደረጉ
ጥያቄ አስነስቷል፡፡ ኮሚሽነሩ ሲመልሱም
በአስደንጋጭ ሁኔታ “የሚገለፅና
የማይገለፅ አለው” ብለዋል፡፡
ብቸኛው የተቃዋሚ ወኪል የሆኑ አቶ
ግርማ ሰይፉ “የተሽዋሚዎች ሀብት
የሚገለጽና የማይገለፀው ምንድነው?”
የሚል ጥያቄ ቢያቀርቡም በቂ ምሳሽ
እንዳላገኙ ለፍኖተ ነፃነት ተናግረዋል፡፡
ጨምረውም “ፀረ ሙስና ኮሚሽን አሁንም
የመንግስት ባለስልጣናትን ሀብትና መረጃ
ይፋ ለማድረግ ተጨማሪ ጊዜ መውሰድ
የለበትም” ካሉ በኋላ፣ ባለስልጣናቱን
በሚመለከት የሚገለፅና የማይገለፅ መረጃ
ሊኖር እንደማይገባ አሳስበዋል፡፡
Abonner på:
Legg inn kommentarer (Atom)
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar