torsdag 16. mai 2013

ቀን : ግንቦት 5/2005 ዓም ለፌደረሽን ምክር ቤት ህገ መንግስት አጣሪ ጉባዔ


ጉዳዩ፤ ህገመንግሰትዊ የመብት ጥሰት ስለተካሄደብን የቀረበ አቤቱታ
እንደሚታወቀው እኛ ባለፈዉ አመት ከመጋቢት እስከ ሰኔ 2004 ዓም ድረስ ከመኖሪያ ቀያችን ከደቡብ ኢትዮጵያ ስንባረር የነበርን ዜጎች ነን::
የመባርርና የመገፋታችን ጉዳይ ግን እስከ አሁን 2005 ዓም ድረስ ቀጥሎአል:: በቅርቡም የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ከልዩ
ልዩ ቦታዎች በህገወጥ መንገድ እየተፈናቀልን ስላለነዉ አማሮች በፓርላማ ተጠይቀዉ ሲመልሱ ማንኛዉም ዜጋ በየትኛዉም የኢትዮጵያ ክልል
የመኖር ህገ መንግስታዊ መብት እናዳለዉ ገልጸዉ በእኛ ላይ እየተወሰድ ያለዉ እርምጃ ግን ጸረ ህገ መንግስት መሆኑን አስረግጠዉ ተናገረዋል::
ይህን ህገወጥ ድርጊት የፈጸሙትንም ለህግ እንደሚቀርቡ ለፓርላማዉ አስረድተዋል:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህገመንግስቱን ለማስከበር የሚያደርጉትን
ጥረት የምናደንቀዉ ቢሆንም እኛ አማሮች በመሆናችን ብቻ እየደረሰብን ያለዉ በደልን ግን አሁንም ተባብሶ ስለቀጠለና ህገመንግሰትዊ የመብት
ጥሰት እየተካሄደብን ስለሆን ይህን አበቱታ ለፌደረሽን ምክር ቤት ህገመንግስት አጣሪ ጉባዔ ለማቅረብ ተገደናል:: ጠቅላይ ሚኒስቴር ሀይለማርያም
ደሳለኝ በፓርላማ ስለዘጎች በሁሉም ቦታ የመኖር ህገመንግስታዊ መበት ከተናገሩ ብሁዋላ ወደ ቀደመ ቦታችን ለመመለስ ወረዳዉን ጠይቀን ነበር::
ሆኖም ወረዳዉ ደቡብ ኢትዮጵያ ሀገራችሁ አይደለም እያለ በዱላ: በጦርና በጥይት ከዚያም አልፎ በወረዳዉ ሚሊሺያዎች ጭምር እያባረረን
ነዉ::የራሳችን የሆነዉ እና በህጋዊነት የገበርንበት መሬት እየተነጠቅ እየተወሰደ በመሬቱም ላይ ያፈራነዉ ቁዋሚ ሀብት እይተዘረፍ
ይገኛል::የተነጠቅንዉ ሀበት : የተወረሰብን ቤት አሁንም አልተመለሰልንም:: እንዲያዉም ቤታችን እየፈረስ አልፎም በጅምላ እየተቃጠለ ይገኛል::
አሁንም በአካባቢዉ ዝር እንዳንል ከአካባቢዉ እንደ ዝንጀሮና ዱር አዉሬ በጥይት እንባረራለን::በጣም የሚያሳዝነዉ ደግሞ በቅርቡም በወረዳዉ
/ጉራ ፋርዳ ወረዳ/ በቤንች ማጅ ዞን ዉስጥ ነዋሪ የነበርን ሰዎችን የአመቱን ግብር ካስገበሩን ብሁዋላ ከቦታችን እንድነሳ መደረጉ ጭምር ነዉ::
እንዲያዉም በግንቦት 1/2005 ዓም በቤንች ማጅ ዞን በጉራ ፋርዳ ወረዳ በኩጃ ገበሬ ቀበሌ ማህበር ስምንት ሰዎች በጦር ተወግተዉ በአሁኑ ሰአት
በከፍተኛ የሞት ጣር ላይ ይገኛሉ:: እንዲሁም በርካታ ሰዎች አለወንጀላቸዉ እየታስሩ ይገኛሉ:: በአሁኑ ወቅት በጉራ ፋርዳ ወረዳ በኩጃ: በበርጅ:

በአለንጋ: በሰመርታ: በከናን:በ አሮጌ ብርሃን: በኩኪ: በቢቢታ: እንዲሁም በሌሎች ቀ/ገ/ማ ያለን ዜጎችን በማፈናቀልና በማባረር መሬቱንና መኖሪያ
አካባቢውን ከነሙሉ ቆዋሚ ንብረቱ በመዉሰድ ነሃሴ 17/2004 ዓም ለሌሎች መርተዉታል:: ይህ ሁሉ አግባብ ያልሆነ ህገመንግስቱን የጣሰ አካሄድ
ዛሬ ገደብ ያጣ ስልጣን በጥቂቶች እጅ ወድቆ እስከመቼ ይቀጥላል? እኛ ተፈናቃዮቹስ ህልዉናችን እንዲህ የመጨረሻ አዘቅት ዉስጥ ወድቆ እስከመቼ
ነው የሚቀጥለዉ? የህገ መንግስቱ መጣስስ እስከመቼ ይቀጥላል ? የፌደረሽን ምክር ቤት ህገመንግስት አጣሪ ጉባዔስ ይህን ጉዳይ በህገ መንግስት
በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት እንዲቆም የማድረግ ህጋዊና ታሪካዊ ግዴታ የለበትም ወይ?
ይህን ጉዳይ ዘርዘር አድርግን የደረስብንን በደል ሁሉ እንደሚከተለዉ ስናቀርብ የፌደረሽን ምክር ቤቱ በህገመንግስቱ በአንቀጽ 62 (1-2) በተሰጠዉ
ስልጣን መሰረት ፍትሃዊ ዉሳኔ ይሰጠናል ብለን በማምን መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን::
በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል የመኖር መብታችን ይከበር
በህገ መንግሰቱ መሰረት ወላጆቹ ወይም ከወላጆቹ አንዱ ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ነዉ/አንቀፅ 6/1/ ፡፡ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ደግሞ
በህገ መንግሰቱ የተቀዳጃቸዉ መብቶች አሉት፡፡ እነሱም በህግ ይጠበቁለታል፡፡ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ ከፈቃዱ ዉጭ ዜግነቱ ሊገፈፍ አይችልም
(አንቀጽ 33/1 )፡፡ ደግሞም ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ የኢትዮጵያ ዜግነት የሚያስገኘዉን መብት፤ ጥበቃ ና ጥቅም የማግኘት መብት
አለዉ (አንቀጽ 33/2).፡፡ ይህ ጥበቃና መብት ደግሞ ህገመንግስታዊ መብቱ በሚጣስበት ጊዜ ህገ መንግስታዊ ትርጉም የመስጠት አካል ያለዉ
የፌደረሽኝ ምክር ቤትን ጨምሮ ሁሉም ሌሎች አካላት የዜጋዉ መብት እንዲጠበቅ እርምጃ መዉሰድን ይጠቀልላል:: ህገ መንግስቱ ለማንኛዉም
ኢትዮጵያዊ ዜጋ የመዘዋወር ነፃነት በአንቀፅ 32 አጎናፅፎአል፡፡ ሲዳማ ፤ አማራ ፤ ኦሮሞ ወይም ትግሬ ሳይል ስለመዘዋወር ነፃነት እንዲህ ይላል፡-
ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ ወይም በህጋዊ መንገድ ሀገሪቱ ዉስጥ የሚገኝ የዉጭ ዜጋ በመረጠዉ የሀገሪቱ አካባቢ የመዘዋወርና የመኖርያ ቦታ
የመመስረት እንዲሁም በፈለገዉ ጊዜ ከሀገር የመዉጣት ነፃነት አለዉ ፡፡ ሆኖም እኛ አማሮችን የገጠመን ፈተና የመረረ: በቃላት ተዘርዝሮ የማያልቅ

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar