lørdag 11. mai 2013

ወያኔ ባለስልጣናቱን አቶ መላኩ ፈንታን እና ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ 12 ሰዎችን በሙስና ጠርጥሮ ማሰሩን በሰበር ዜና በአሠረ


(ዘ-ሐበሻ) የወያኔ ሥርዓት በኢትዮጵያ ብቻውን ያሸነፈበትን ምርጫውን ሙሉ በሙሉ አሸንፌያለሁ በሚል ከማወጁ አስቀድሞ የሕዝቡን ስሜት ለመቀየር አቶ መላኩ ፈንታ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተርን እና ምክትላቸውን አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ 12 ሰዎችን በሙስና ጠርጥሮ ማሰሩን በሰበር ዜና አብስሯል።
መላው የወያኔ/ኢሕአዴግ ባለስልጣናት በሙስና የተጨማለቁ መሆናቸው በይፋ የታወቀ ሲሆን ስርዓቱ የጸረሙስና ሕጉን የፖለቲካ ልዩነት በሚያሳዩ ባለስልጣናት ላይ ብቻ ተግባራዊ በማድረግ ሲተች ቆይቷል የሚሉ ታዛቢዎች ከዚህ ቀደም አቶ ታምራት ላይኔ በሙስና ሲታሰሩ፣ አቶ ስዬ አብርሃ ከነቤተሰባቸው ዘብጥያ ሲወርዱ፣ አቶ ቢተው በላይ እና አባተ ኪሾም እንዲሁ ከርቸሌ ሲወረወሩ የጸረሙስና አዋጁ ተግባራዊ የሆነባቸው ከድርጅታቸው ጋር የፖለቲካ ልዩነት በማምጣታቸው እንጂ እውን አዋጁን ተግባራዊ ከማድረግ ጋር በተያያዘ አለመሆኑን በአስተያየታቸው ላይ ተናግረዋል።

አቶ ይሁን ተድላ የተባሉ ታዛቢ የዛሬውን የገቢዎችና የጉምሩክ ባለስልጣናት መታሰርን ተከትሎ የሰጡት አስተያየትም ከዚሁ የሚለይ አይደለም። እኚህ አስተያየት ሰጪ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ “አቶ መላኩ ፈንታ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ለእስር የተዳረጉበት ወቅታዊ ምክንያቱ በ አማራው ብሔር ከደቡብና ከቤንሻንጉል ክልል መፈናቀል ጉዳይ ላይ በብአዴን ውስጥ በተፈጠረ የተለያየ አቋም ድርጊቱን በተመለከተ ግለሰቡ ህወሃት ላይ ጣታቸውን በመቀሰራቸው ነው የሚል ጥርጣሬ አለ። ወያኔ ታማኝ አገልጋዮቹን ለክፉ ጊዜ ብሎ ባሰናዳላቸው ወጥመድ በቀላሉ ወንጅሎ ወደ ወህኒ ሊያወርዳቸው እንደሚችል የተረጋገጠ ነው። በመሆኑም የአቶ መላኩ ፈንታ አሁን ተይዘው ወደ እስር ቤት የተወሰዱበት ምክንያት ሁሉም የኢህአዴግ አባላት ንጹህ በማይሆኑበት ሙስና ተጠርጥረው ነው የሚለው ፕሮፓጋንዳ ሚዛን የሚደፋ አይደለም። ከደብረፅዮን ቢሮ ሾልኮ የወጣው ወሬ እንደሚያመለክተው ከሆነ አቶ መላኩ ፈንታ ለጊዜው ወደ አልታወቀ ሀገር ለመኮብለል ሲዘጋጁ ኤሌክትሮኒክ መልዕክታቸው በመጠለፉ ነው።በዚህ ላይ አቶ መላኩ ፈንታ በሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር በሃላፊነት ሲሰሩ የሚያውቁት የደህንነትና የድርጅት ሚስጥሮች ስላሉ የግለሰቡ ከሀገር መኮብለል ተመጣጣኝ ስልጣን እንደነበራቸው አቶ ጁነዲን ሳዶ ኩብለላ በቀላሉ የሚታይ አይደለም በሚል የውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ።አብረዋቸው የተያዙት የህወሃቱ እና ሌሎች ባለስልጣናት ግልፅና ተጨባጭ ከሆነው የባለሥልጣኑ መስሪያ ቤት የሙስናና የአሰራር ንቅዘት አኳያ አቶ መላኩ ፈንታ ለታሰሩበት እውነተኛ ምክንያት ጥሩ የወያኔ ሽፋን እና ማጭበርበሪያ እንደሚሆኑ ታዛቢዎች ይገልፃሉ።” ይላሉ።
የኢቲቪን ዜና ይመልከቱ፦

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar