
በትናንትናው እለት በአዲስ አበባ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች “ፍትህ” የሚል ጽሁፍ የያዙ ወረቀቶችን በመያዝ ፍትህን በማለት ሲጠይቁ መዋላቸውን የገለጠው ዘጋቢያችን ፣ ፍትህ አጥተው በእስር ቤት የሚሰቃዩ መሪዎቻቸውን እጃቸውን በማጣመር በድጋሜ ሲያስቡ መዋላቸውን ገልጧል። እንደተለመደው በዚሁ የተቃውሞ ድምጽ አካባቢ በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት ቢታዩም፣ ምንም አይነት ግጭት አለመፈጠሩን የደረሰን ሪፖርት አመልክቷል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት በዘገባው እንዳመለከተው በአዳማ ፍትህ የጠየቁ ሙስሊሞች በፖሊሶች ተደብድበው እንዲባረሩ የተደረጉ ሲሆን በእስር ላይ በሚገኙት ሙስሊም መሪዎች ላይ ምንም አይነት ጠንካራ የሰነድም ሆነ የሰዎች ማስረጃ አለመቅረባቸውን ገልጧል።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar