fredag 12. april 2013

የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ምስረታን አስመልክቶ ጥምረት የደስታ መግለጫ መልዕክት አስተላለፈ



ባለፉት አርባ አመታት በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ምስረታና የትግል ሂደት ዉስጥ ጉልህ ሚና የተጫወቱና ግንባሩን ለረጂም ግዜ የመሩ የኦሮሞ ተወለጆች ከዚህ ቀደም ያራምዱት የነበረዉን ከኢትዮጵያ የመገንጠል ጥያቄ በመቀየር አዲሲቱንና ለሁለም እኩል የሆነች ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚደረገዉን ትግል ለመምራት የወሰዱትን እርምጃ በማድነቅ ጥምረት ለነጻነት፤ ለፍትህን ለእኩልነት በኢትዮጵያ ለኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላላፈ። ጥምረት ይህንን የደስታ መግለጫ መልዕክት ያሰተላለፈዉ በላፈዉ ሳምንት ማብቂያ ላይ አዲስ የተፈጠረዉ የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ዋሺንግተን ዲሲ ዉስጥ የመጀመሪያዉን ህዝባዊ ስብሳበ ለማድግ በዝግጅት ላይ በነበረበት ግዜ ነዉ። ይህንን ላለፉት አርባ አመታት የኢትዮጵያን የፖለቲካ ድባብ በአንድነት ኃይሎችና በብሄር ብሄረሰብ ሀይሎች ለሁለት ከፍሎ በአገሪቱ የለዉጥ ሂደት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳደረገ የሚነገርለትን የፖለተካ መስመር ቀይረዉ አዲስ ጉዞ የጀመሩት ሃይሎች እንደዚህ አይነቱን ታሪካዊና  ስር ነቀል እርመጃ መዉስድ የቻሉት ያሳለፉትን የትግል ታሪከ፤ የአሁኑን የኢትዮያ ተጨባጭ ሁኔታና  የወደፊቷ ኢትዮጵያ ምን መምሰል አለባት በሚሉ ግዙፍ ጥያቄዎች ላይ ለረጂም ግዜ ተወያየተዉ የጋራ ግንዛቤ ላይ ከደረሱ በኋላ መሆኑን ከግንባሩ ቃል አቀባይ የተገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ።
እንደ ብዙ የፖለቲካ ተንታኞች ግምት ይህ የአቋም ለዉጥ በኦሮሞ ማህበረሰብና በተለያዩ የፖለቲካ ሀይሎች ተቀባይንትን ካገኘ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ዉስጥ ለረጂም ግዜ ሆድና ጀርባ ሆኑዉ የቆዩትን ሁለት ግዙፍ ሀይሎች በማቀናጀት የኢትዮጵን የፖለተካ ችግር በፍጥነት ይፈታል ብለዉ የሚያምኑ ብዙዎች ናቸዉ። “እኛ የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር መስራቾች ለሁሉም የኢትዮጵያ ህዝቦች ፍትህ፤ነጻነት፤ እኩልነትና የዲሞክራሲ መብት መከበር መታገልን መሰረታዊ አላማዉ ያደረገ አዲስ የኦሮሞ የፖለቲካ ንቅናቄ መመስረቱን በይፋ እናበስራለን” ብሎ ከአንድ ሳምንት በፊት እራሱን ለኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ ያደረገዉ የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር በዚህ መግለጫዉ ላይ ለኦሮሞ ህዝብ፤ ለመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብና ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ ለኢያንዳንዳቸዉ የሚመለከታችዩን መልዕክት አስተላልፏል። የኦሮሞን ህዝብ ሚና በተመለከተ ደግሞ የኦሮሞ ህዝብ ኢትዮጵያን ዲሞክራሲየዊ አገር በማድረጉ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብሏል። ከዚህ በተጨማሪ ኦሮሞን ጨምሮ በሌሎች የአገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦች ላይ የሚደርሰዉ ሰቆቃ፤ ጭቆና፤አድልዎ፤ እንግልት፤ ዉርደትና ብዝበዛ ከምን ግዜዉም በላይ ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ ይገኛል ካለ በኋላ ለሁሉም የአገሪቱ ህዝቦች ነጸነት እኩልነትና ዲሞክራሲ መብት መከበር መታገል የሚያስችለንን አዲስ የፖለቲአ ንቅናቄ የመሰረትነዉም በእንደዚህ አይነቱ የፖለቲካ ንቅናቄ ስር ተደራጅተን ብንታገል ለሁሉም የሚበጅ ዉጤት ለማስመዝገብ አርግጠኛ በመሆን ነዉ ብሏል።
ጥምረት ለኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር የላከዉን የደስታ መግለጫ መልዕክትና የግንባሩን መመስረት ተከትሎ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሂደት ዉስጥ ሊኖር የሚችለዉን የሀይል አሰላለፍና አብሮ መስራት አስመልክቶ ያናገርናቸዉ የጥምረቱ የዉጭ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ኤፍሬም ማዴቦ እንደገለጡት የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር  መመስረትና በተለይም ይህ ግንባርና የዛሬ ሁለት አመት በጄኔራል ከማል ገልቹ የሚመራዉ ኦነግ ያደረጉት ስር ነቀል ለዉጥ በተለያዩ የአገራችን የፖለቲካ ኃይሎች መካከል ለግማሽ ምዕተ አመት የዘለቀዉን ያለመተማመንና የፍርሀት ማነቆ በመስበር ሕዝባዊ ትግሉን ወደፊት ያራምደዋል ብላዋል። በተለይም ኢትዮጵያ ዉስጥ በተባበረ ህዝባዊ አመጽ የወያኔነ ዘረኛ ስርአት ለመደምሰስ የሚደረገዉ ትግል እስከዛሬ ድረስ አጥቶት የነበረዉን አጋር ስለሚያገኝ ይህ የተወሰደዉ የአቋም ለዉጥ ጥቅሙና ፋይዳዉ በስፋቱም በጥልቀቱም እጅግ በጣም ትልቅ ነዉ ብለዋል። አቶ ኤፍሬም ንግግራቸዉን በመቀጠል ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ አንዱን ገንጣይ ሌላዉን አፍራሽኛ የዱሮ ስልጣን ናፋቂ እያለ ካሁን በኋላ ህዝብን ማታለልና መከፋፈል አይችልም ብለዋል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar