lørdag 6. april 2013

የወያኔ አገዛዝ አዲስ አበባ ዉስጥ መኖሪያ ቤቶችን ሆን ብላ ማቃጠል መጀመሩ ታወቀ



ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ አዲስ አበባ ዉስጥ በተለያዩ ቦታዎች መኖሪያ ቤቶችን ሆን ብሎ ማቃጠል መጀመሩን ቤታቸዉ የተቃጠለባቸዉ የከተማዋ ነዋሪዎች ለዝግጅት ክፍላችን በላኩት ዜና ገለጹ።ለዜጎች ምንም አይነት ክብርና ሀላፊነት የማየይሰማዉና የሚሰራቸዉን ስራዎች ሁሉ ሀይልና ተንኮል ቀላቅሎ የሚሰራዉ የወያኔ አገዛዝ አንድ ወር በማይሞላ ግዜ ዉስጥ አዲስ አበባ ዉስጥ ሦስት የመኖሪያ አካባቢዎችን አቃጥሎ በሰዉ ህይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ አደጋ ማድረሱ ታዉቋል። ቤታቸዉ የተቃጠለባቸዉና ሌሎችም ብዙ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች እንደሚናገሩት ወያኔ ቤቶቹን የሚያቃጥለዉ እንደለመደዉ ቦታዉን ለህወሀት አባላትና ለቤተሰቦቻቸዉ ለመስጠት ነዉ ብለዉ ያምናሉ።
ባለፈዉ ረቡዕ መጋቢት 25 ቀን አዲስ አበባ ዉስጥ አባ ኮራን ሠፈር እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ወያኔ ሆን ብሎ በጫረዉ እሳት ከ40 በላይ ቤቶች መዉደማቸዉንና በሁለት ሰዎች ላይ ከፍተኛ የመቃጠል አደጋ መድረሱን የአይን እማኞች ተናግረዋል። በዚሁ ዕለት በተመሳሳይ ሰዐት አውቶቡስ ተራ አካባቢ 32 ቀበሌ ዉስጥ የሚገኙ ቤቶች ለሁለተኛ ጊዜ መቃጠላቸዉን ሁኔታዉን በቅርብ ሆነዉ የሚከታተሉት ዜና ምንጮች ገልጸዋል። አውቶቡስ ተራ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ነዋሪዎች ከዚህ ቀደም አካባቢውን ለቅቀዉ እንዲወጡ የተነገራቸዉ ቢሆንም ነዋሪዎቹ ለመልቀቅ ፈቃደኛ ባለመሆናቸዉ አካባቢዉ ሉለተኛ ገዜ ለእሳት አደጋ ተጋልጧል። ከሁለት ሳምንት በፊት በዚህ አካባቢ በደረሰው የእሳት አደጋ 11 ሰዎች መሞታቸው የሚታወስ ሲሆን የወያኔ መገናኛ ብዙሀን የሟቾች ቁጥር 8 መሆኑን መዘገባቸው ይታወሳል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የእሳት አደጋዉ በደረሰባቸዉ አካባበዎች ሁሉ የእሳት አደጋ መኪናዎች ወደ ቦታዉ የሚድርሱት ቤቶቹ ተቃጠለዉ ካለቁ በሁዋላ መሆኑንና ከቦታው ከደረሱም በሁዋላም ውሀ የለንም እያሉ እንደሚመለሱ ለማወቅ ተችሏል። በወያኔ ድርጊትና በእሳት አደጋ ሰራተኖች ቸልተኛነት የተበሳጩ የአካባቢው ወጣቶች ሁለት የእሳት አደጋ መኪናዎችን በድንጋይ የሰባበሩ ሲሆን ከፌዴራል ፖሊስ ጋርም መጋጨታቸዉ ታዉቋል።

    Ingen kommentarer:

    Legg inn en kommentar