fredag 5. april 2013

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ የዳላስ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ልኡካንን አነጋገሩ


ከርዕሰ አድባራት ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ከዳላስ ቴክሳስ፤ አራት የቦርድ አባላት ፤ አንድ ካህንና አንድ ዲያቆን ያካተተ ልኡካን  ወደ አትላንታ ጆርጂያ ተጉዞ  ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያን አነጋግሮ ተመለሰ።  በአስተዳደር ቦርዱ ሊቀመንበር የተመራዉ ልኡክ፤
1ኛ አቶ ሙሉጌታ ወልደ ሚካኤል ፤ ሊቀመንበር
Abuna Merkorios (Patriarch and Catholicos of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church)2ኛ አቶ አበበ ንጋቱ ፤ ም/ሊቀመንበር
3ኛ አቶ አብርሃ አሰፋ፤ ዋና  ጸሃፊ
4ኛ አቶ ሙሉዓለም ፈንታሁን፤ ኦዲተር
5ኛ መጋቢ ስርዓት ቄስ ዮሐንስ ሞገስ
6ኛ ዲያቆን አንዷለም ዳግማዊ፤ የቅዱስ ያሬድ ትምህርት ቤት ዴሬክተር በመሆን

ቅዱስነታቸዉ በሚገኙበት በጆርጅያ ክፍለ ሃገር በሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማሪያም ካቴድራል ለአንድ ሰዓት ያህል  ልኡካኑን ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዮስ አነጋግረዋል። ከቅድስት ማሪያም ካቴድራል ከቅዱስነታቸዉ ጋር አብረዉ የተገኙ
1ኛ ብጹዕ አቡነ ያቆብ የጆርጂያ፤የቴነሲ፤ የሰሜንና የደቡብ ካሮላይና ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
2ኛ መምህር ልኡለቃል አካሉ፤ የፓትርያርኩ ልዩ ጸሃፊ  ነበሩ
በአስተዳደር ቦርዱ ለቅዱስነታቸዉ የተጻፈዉ ደብዳቤ  በሊቀመንበሩ አመማካኝነት ተሰጥቶ፤  ቅዱስነታቸዉ ተቀብለዉ ካዩ በኋላ  እስከ አሁን ተለይተዉ በመቆየታቸዉ አዝነዉ፤ ለህዝበ ክርስቲያኑ የወንጌል ማስተማር ሥራ ተጠናቅሮ እንዲቀጥል፤ የአካባቢ ሊቀ ጳጳስ እንደሚመደብ፤ በቅርቡም ምናልባት ከጾሙ በኋላ  የቅዱስ ሚካኤልን ካቴድራልን እንደሚጎበኙ ገልጸዉ፤ ቡራኬ ሰጥተዉ፤ በደስታ መቀበላቸዉን  የሚገልጽ ደብዳቤ ፈርመዉ የመሃተማቸዉን  ምልክት አስቀምጠዋል፤ ልኡካኑ  የሰጧቸዉን ደብዳቤ ይዘዉ ወደ ዳላስ ቴክሳስ በ4/3/2013 ተመልሰዋል፤
ይህ በቴክሳስ ዳላስ የሚገኘዉ የዕርሰ አድባራት ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል በቀደምትነትና በትልቅነቱ የታወቀዉ ብዙወች የሚመሰክሩለት ባለፉት 21 ዓመታት በገለልተኛነት የቆየ ሲሆን በቅርቡ ህዝበ ክርስቲያኑ አባት ያስፈልገናል ብሎ በሰጠዉ ዉሳኔ መሰረት በስደት ላይ የሚገኘዉን በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ  የሚመራዉን ቅዱስ ሲኖዶስ ተቀብሏል።
የርዕሰ አድባራት ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካህናትና ምዕመናን በእግዚአብሄር ቸርነት እንኳን ደስ አላችሁ፤
ወስብሃተ ለእግዚአብሔር
ከድምጸ ተዋህዶ

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar