
ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ላይ በተሰጠው በዚህ ስልጠና ከ5 ሺ ያለነሱ ከየክልሉ ተውጣጥተው የመጡ የገዢው ፓርቲ አባላት የተሳተፉ ሲሆን ምርጫዉ ከመጀመሩ በፊት ብዙ ተከታታይ ስልጠና ለመስጠት ዝግጅቱ መጠናቀቁን ለማወቅ ተችሏል። ወያኔ/ኢህአዴግ ያለምንም ተፎካካሪ ብቻዉን ወይም ከራሱ ጋር በሚወዳደርበት ምርጫ የመራጩ ቁጥር ጨመረ አልጨመረ ለምን እንደሚጨነቅ ለግዜዉ ማወቅ ባይቻልም እንደ ብዙ ምዕራባዉያንና የአገር ዉስጥ ፖለቲካ ተንታኞች ግምት ወያኔ የሚጨነቀዉ ላልመረጥ እችላለሁ በሚል ስጋት ሳይሆን የመራጩ ቁጥር በቀነሰ ቁጥር ከጌቶቹ ከምዕራባዉያን ሊመጣ የሚችለዉን ጥያቄ በመፍራት ነዉ። ከዚህ በተጨማሪ ወያኔ እንደለመደዉ 99% ድምጽ አገኘሁ ለማለት የመራጩ ቁጥር ከፍ እንዲልለት ይፈልጋል እንጂ የምርጫዉ ዉጤትማ ከአሁኑ የታወቀ ነዉ ሲሉ አንድ ስማቸዉ እንዳይገለጽ የፈለጉ የፖለቲካ ፓርቲ መሪ ተናግረዋል። እኚህ ፓርቲያቸዉ ምርጫዉ እንደማይሳተፍ የነገሩን የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ወያኔን ለመጣል አማራጩ ምርጫ ሳይሆን ህዝባዊ አመጽ ብቻ ነዉ ብለዋል።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar