Content View Hits : 117948
Tuesday, 08 January 2013 18:43 |
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ጠገዴ በተለያዩ ቦታዎች
ወታደራዊ ጥቃት ፈፀመ።
የኢትዮጵያን ሕዝብ ከጎጠኛውና ከአሸባሪው የወያኔ አምባገነናዊ ስርዓት ለማላቀቅ የትጥቅ ትግልን አማራጭ አድርጎ ለሀገርና ለወገኑ መስዋዕትነት ለመክፈል ቆርጦ የተነሳው የኢትዮጵያሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት የፀረ- ወያኔ ትንቅንቁንና ፍልሚያውን አጠናክሮ በመቀጠል በተሰለፈባቸው አውደ- ውጊያዎች በጠላት ላይ ወታደራዊ የበላይነትን በመቀዳጀት የሐገርና የወገን አለኝታነቱን እያስመሰከረ ይገኛል።
በዚህም መሰረት በታህሳስ 28 ቀን 2005 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ጠገዴ ሳርና በተባለ ቦታ ከልዩ ሃይል ታጣቂ ቡድን ጋር ከጧቱ 1፡00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ባደረገው ውጊያ 5 የጠላት ወታደሮችን በመግደል 13 ያቆሰለ ሲሆን በዝያው እለት ጠገዴ ጎርሶ በሚባል ስፍራ ከ11፡00 ሰዓት እስከ 12፡30 ባደረገው ውጊያ 3 የጠላት ወታደሮችን ገድሎ 5 አቁስሏል የግንባሩ ሰራዊት በዚሁ እለት ባደረገው ውጊያ በድምሩ 8 ገድሎ 18 በማቁሰል በጠላት ላይ አንፀባራቂ ድል አስመዝግቧል።
ጠገዴ በተለያዩ አካባቢዎች ተመድቦ እና መሽጎ የነበረው የስርዓቱ ዋነኛ ተንከባካቢ የልዩ ሃይል ታጣቂ ቡድን ሕብረተሰቡን በማንገላታትና በማስፈራራት እኩይ ተግባር ላይ ተጠምዶ የነበረ ሲሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊትም በዚህ አፋኝና ሰው በላ የልዩ ሃይል ታጣቂ ቡድን ላይ ባደረሰው ድንገተኛ ማጥቃት በጠላት ላይ ከፍተኛ የሕይወትና የንብረት ኪሳራ በማድረስ አኩሪ የአርበኝነት ጀብድ ፈፅሟል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በያዝነው 2005 ዓ.ም በዓይነቱ ልዩ የሆነ የውጊያ እቅድና ዘመቻ ነድፎ በሀገራዊ ሞራልና ወኔ በመንቀሳቀስ በሰሜኑ የሐገራችን ክፍል በተለያዩ ቦታዎች የጠላትን ሰራዊት በማደባየት የተለመደውን አኩሪና አንፀባራቂ ድል እያስመዘገበ ይገኛል።
|
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar