lørdag 2. mars 2013
ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ
በሚገኘው የወያኔ ቆንስላ ጽ/ቤት ፊት ለፊት ተካሄደ
እ.ኤ.አ. በማርች 01 ቀን 2013 ዓ.ም. በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች
ግንባር ዘብ በጠራው ታላቅ የተቃውሞ ሠልፍ ላይ ከተለያዩ የጀርመን ከተሞች የተሰባሰቡ ቁጥራቸው
ከ400 በላይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን፣ትውልደ-ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የተገኙ ሲሆን
መነሻውን ''ሃውፕትቫኸ'' /Hauptwache/ ከሚባለው የከተማው ክፍል በማድረግ በተለያዩ
መፈክሮችና የኢትዮጵያ ባንድራ በማሸብረቅ ጉዞውን ወደ ወያኔ ቆንስላ ጽ/ቤት አድርጓል።
- ''የህሊና እስረኞች ይፈቱ!''
- ''የፕሬስ ነጻነት ይከበር!''
- ''ሃሳብን በነጻነት የመግለፅ መብት ይከበር!''
- ''ጅሃዳዊ ሐረካት የወያኔ ፈጠራ ነው!''
- ''የሃይማኖት ነፃነት ይከበር!''
- ''በአለም ዙሪያ ያሉ የወያኔ ቆንስላ ፅ/ቤቶች የኢትዮጵያን ህዝብ አይወክሉም!''
- ''የአውሮፓ ህብረት ለአፋኙ የወያኔ አገዛዝ የሚያደርገውን የገንዘብ ድጋፍ ያቁም!''
- ''ከአባይ በፊት ሙስናና ዘረኝነት ይገደብ!'' የሚሉ መፈክሮች በሰፊው የተደመጡ ሲሆን
Abonner på:
Legg inn kommentarer (Atom)
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar